በብሄር ስም ተንጠላጥለው የተደራጁ ጽንፈኛና ዘራፊዎችን ለመምታት ስምምነት ተደረሰ

አሁን አሁን የብሄር ስምን ከፊት አድርጎ መዝረፍ፣ መግደል፣ ማስገደል፣ ህገወጥ ተግባር መፈጸም የተለመደ ሆኗል። ከዚሁ መረን የለቀቀና ውንብደና በተጨማሪ ከፍተኛ ሃብት የሚፈስበት አገርን የማፈራረስ አጀንዳ ያላቸው አካላት ህዝቡን ማህበራዊ ዕረፍት ነስተውታል። አፈናቅለውታል። ሃብቱንና ህይወቱን አጥቷል።

ይህንኑ ተከትሎ በአማራና በኦሮሞ ብልጽግና ውስጥ መሻከርና ፍጹም የሆነ አለመግባባት ተፈጥሮ ቆይቷል። አንዱ ሌላውን ሆን ብሎ ሽፍታ እንደምኪያደራጅ በማሰብ፣ አንዱ የሌላውን ድንበርና ስልጣን ባለማክበር፣ ስር እየሰደደ የመጣው ልዩነት መልኩን የሚቀይርበት ደረጃ ደርሶ፣ ጋላቢ ለሚባሉት ሃይሎች የተመቸ ሁኔታ መፍጠሩ ተገልጾም ነበር።

ሁለቱ ፓርቲዎች በየግዜው የሚያገረሸውን ልዩነታቸውን ለህልውናቸው ሲሉ ለማስወገድ ባህርዳርና አዳማ ላይ በዝግ ሲመክሩ ከርመዋል። ለዚህም ይመስላል ዛሬ ላይ በግልጽ ዝርዝር ባይቀርብም “ፅንፈኛ ኃይሎችን በጋራ ለመታገል ተስማምተናል” ሲሉ የኦሮሚያና አማራ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ይፋ ተናግረዋል።

አንዱ ሌላኛውን እየገፋ መሄዱና ከጀርባ በልዩ አላማ የሚመሩ ሚዲያዎች ” ከውስጥ አገኘን ” እያሉ የሚረጩት መረጃ፣ በገቢር ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና በደል ፈጻሚዎቹን በሚዛን የሚያጋልጥ ባለመሆኑ ልዩነቱን አግሞት ስንብቶ ነበር። ምን ያህል አሁን በደረሱበት ውሳኔ እንደሚዘልቁ ባይታወቅም የአማራና ኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች በብሄር ታርጋ ህግ እየጣሱ ሲነኩ የሚለቀስላቸውን ሊመቱ መስማማታቸውን ስብሰባን ሲከታተሉ የነበሩ ገልጸዋል።

ሁለቱም ክልሎች አሁን መከላከያ በጀመረው ጽንፈኞችን የማጥራት ዘመቻ ተባባሪ እንደሚሆኑ፣ ከአማራ ክልል ተነስተው ኦሮሚያ ክልል የገቡ በሙሉ የፈጸሙት ድርጊት ስህተት መሆኑንን ተማምነዋል። ዘርን ለይቶ የአማራ ተውላጆች ላይ ሲፈጸም የነበረውንንና አሁንም ሊፈጸም ስለሚችል ግድያ መስመር አስመረው ለመስራት መወሰናቸው ተሰምቷል።

“ፅንፈኛ ኃይሎችን በጋራ ለመታገል እንደሚሰሩ የኦሮሚያና አማራ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አስታወቁ” በሚል የመንግስት ሚዲያዎች ግድርፍ ዜና የሰሩለት ይህ ስምምነት ይፋ የሆነው፣ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማና የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ናቸው። ይህን ያሉትም በአዳማ ሲካሄድ የቆየውን የፓርቲዎቹን የከፍተኛ አመራሮች ውይይት አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ ነው። አመራሮቹ በባሕርዳር የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ በአዳማ በተካሄደው መድረክ ላይም የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል ተብሏል።

See also  የአፋር ክልል ምክር ቤት ከሕወሓት የሽብር ቡድን ጋር ያበሩ የቀድሞ የክልሉ አመራሮችን በአሸባሪነት ፈረጀ

ትህነግን በህብረት ማስተንፈሳቸውን አንስተው አሁንም በህብረት ለህልውናቸው ሲሉ መተባበር እንዳለባቸው ተማነዋል። ኢትዮጵያ ባለፈችበት ፈተና ሁሉ በሕዝብ ትብብር በተገኘ ድል ሀገርን ማዳን በትልቅ ስኬትና ተምሳሌት በማንድሳት ነው በተባበሩ አስፈላጊ መሆኑንን ያወጁት፡፡ “በአንድነትና ወንድማማችነት መሥራቱ ይበጃል” በሚል አብሮ የመቀጠሉን አስፈላጊነት በማንሳት በግልጽ መወያየታቸውን አድምተውም ባይሆን መናገራቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ካሰራጩት ዜና ለመረዳት ተችሏል።

ባለፈው ሳምንት ከኦሮሚያ በኩል ” ከአማራ ብልጽግና ጋር ይብቃን ” የሚሉ ወገኖች ጥቂትም ቢሆኑ መሰማታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ለዚህም ይመስላል ” አብሮ ከመስራት ውጭ የሚያዋጣ ነገር የለም” በሚል ሲስማሙ ያገኙትን ድል አንስተው መነጋገራቸውን አመራሮቹ ገልጸዋል።

በሁለት ቀናቱ ውይይት በጦርነቱ የደረሰውን ከባድ ጉዳት ከግምት በማስገባት አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግና የመልሶ ማቋቋም ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወያየታቸውም ተነስቷል። እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በጋራ መሻገር የሚቻለው በአንድነትና በወንድማማችነት መሆኑ መነሳቱንም አመራሮቹ እንደገለጹ ፋና ከስፍራው ዘግቧል።

በአገሪቱ ለሰላም መጥፋት ዋና ችግር እየሆነ የመጣውን ፅንፈኝነት እንደሆነ ተማምነዋል። ይህንኑ ጽንፈኛነት ለመታገልና በምፈለገው አግባብ ከህዝብ ነጥሎ እርምጃ ለመውሰድ፣ ይህንንም በጋራ ለማከናወን ለመቆም መክረው መወሰናቸው ተግልጿል። የህግ የበላይነት ማረጋገጥ የጋራ አቋም ስለመያዛቸው ሁለቱም በመግለጫቸው ይፋ አድርገዋል። ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም፣ ህግ ማስከበሩ ህግ በሚጥሱት ላይና ህግ እየጣሱ ያሉት እነማን እንደሆኑ ስለሚታወቅ አካሄዱ ጠንካራ እንደሚሆን አመላካች ሆኗል።

ህግ የሚጥሱ ጽንፈኞችን በጋራ ለማጽዳት መስማማታቸውን ሲገልጹ ጎን ለጎን “መገናኛ ብዙኃን ከአላስፈላጊ ድርጊቶች ተቆጥበው የሀገር ግንባታ ስራዎች ላይ እንዲያተኩሩም ጥሪ አቅርበዋል” ተብሏል።

በጽንፈኛነት የሚንቀሳቀሱትንና ሰላማዊ ህዝብ ጤና የነሱትን ወገኖች “የአማራና የኦሮሞ ሸኔዎቼ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ መናገራቸውን ተከትሎ ” አማራ ሸኔ መባሉ ቅሬታ አስነሳኤ በሚል የተለያዩ የዩቲዩብ አውዶች ጉዳዩን ሲያራግቡ እንደነበር ይታወሳል። እነዚህ ወገኖች ሙሉ ምስራቅ ወለጋ በወረራ ተይዞ፣ ህዝብ ሲገደልና ሲዘረፍ ፣ምንም አለማለታቸው ድርጊቱ በመናበብ እንደሚሰራ አመላካች መሆኑ ጎን ለጎን ሲገለጽ ሰንብቷል። አሁንም የአምራና ኦሮሞ ብልጽግና ህገወጦችን ለማጽዳት መስማማታቸው ተመሳሳይ የሚዲያ የተቃውሞ ዘመቻ እንደሚጠብቀው ይጠበቃል።

See also  " ከጎናችን " ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ ሳምንታዊ መግለጫ

መንግስት ከሶስት ሳምንት በፊት ባሳለፈው ውሳኔ መከላከያ ጽንፈኞች በተባሉት ላይ የእርምት እርምጃ እይየወሰደና በጽንፈኞች ስር የነበሩ ወረዳና ቀበሌዎች እያጸዳ መሆኑ ታውቋል። ይህ እርምጃ ከምወሰዱ በፊት ጉቲን ላይ መከላከያ ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ሃይሎች እንደነበሩና መከላከያ ሃይል ጨምሮ እርምጃ እንደውሰሰደባቸው አውዱ ተቀይሮም ቢሆን ሲገልጽ ነበር። መከላከያ ላይ የተተኮሰው በስህተት ሲሆን ገበሬርዎች እንደሆኑ ተድርጎም ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ማስተባበያ ቀርቦም ነበር። እዚህ ጉዳይ ላይ የተሳተፉትን አስመልክቶ ልዩ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ዝግችት ክፍላችን አረጋግጧል።

Leave a Reply