የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር?

ኃያላን በአፍሪካ ስለሚያደርጉት ሽኩቻ አፍሪካ የአለም አቀፍ ሽኩቻ መድረክ መሆን የለባትም ሲሉ የተናገሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ገንግ፤ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉት ጉብኝት መጀመሪያ ላይ አዲሱን የአፍሪካ CDC ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።

ቻይና ባለፉት አስር በላይ አመታት የአፍሪካ ትልቋ የንግድ አጋር ሆና የቆየች ስትሆን፤ በአህጉሪቱ ብሎም በአለም ኃያልነት ግስጋሴዋ ባለፈው ወር 49 የአፍሪካ መሪዎችን ካስተናገደችው ከአሜሪካ እንዲሁም ከቀድሞ ቅኝ ገዥ አውሮፓውያን በተለይም እንደ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ካሉ የአሜሪካ አጋሮች ጋር ትፎካከራለች።

ቺን ገንግ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “አፍሪካ ለዓለም አቀፍ ትብብር ትልቋ መድረክ እንጂ ለጉልበተኛ ሀገራት የውድድር መድረክ መሆን የለባትም” ብለዋል።

የፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ታማኝ ረዳትና በዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ አምባሳደር ቺን፣ ባለፈው ወር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ሀገሪቱ የመጀመሪያ የባህር ማዶ ጉብኝቷን በተከታታይ በአፍሪካ ስታደርግ ይህ 33ኛ ዓመቱን ያስቆጠረ ሆኗል።

የቻይና ዕዳ ሥረዛ ቺን ማክሰኞ እለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተገናኙ ሲሆን ከሁለቱም ወገኖች ዝርዝር መረጃ ባይሰጥበትም ቤይጂንግ ለአዲስ አበባ ከፊል የዕዳ ስረዛ ማድረጓን አስታውቀዋል።  

ይህ የቻይና ርምጃ ለኢትዮጵያ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የሚመታ ነው። የዕዳ መጠኑን ከመቀነስ ባሻገር ተጨማሪ ድጋፍ የመቀበል ደረጃዋን ከቀይ ወደ ቢጫ ምናልባትም ወደ አረንጓዴ ከፍ ለማድረግ የሚረዳ ነው።

በሌላ በኩል ይህ ዜና ለምዕራባዊያን እጅግ የሚያናድድ ሲሆን በIMF በኩል ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ በእጃቸው ለማድረግ የሰነቁትን ምኞት የሚያጠፋ ነው። መሰሉን የቻይና ድጋፍ ዋሽንግተን ስታወግዝ የቆየች ስትሆን ርምጃውንም የቻይና “Payday Loan Diplomacy” ስትል የዳቦ ስም ያወጣችለት ነበር።

በተለይም በፈረንጅ 2019 በአውስትራሊያ የተመደቡት የአሜሪካ አምባሳደር Arthur Culvahouse ቻይና ቶንጋ ላይ በሚኖራት ትብብር ላይ ተፎካካሪዋ የነበረችውን አውስትራሊያን መና ያስቀረ ብድርና ርዳታ ማቅረቧን ተከትሎ ነበር ይህን ወቀሳ አዘል የዳቦ ስም ለቤይጂንግ ብድር ሲሰይሙት ተስተውለዋል። (እስሌማን አባይ – #የዓባይልጅ)

See also  የግል ባንኮች ሰባ ከመቶ የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ገቢ እንዲያደረጉ ታዘዘ

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Leave a Reply