አቡዳቢ ውብ ቤተክርስቲያን እየተገነባ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝተዋል፡፡ አብይ አሕመድ ለስብሰባ ወደ ስፍራው ማምራታቸውን ተንተርሰው ነው ጉብኝታቸውን ያደረጉት።

“ዛሬ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝቻለሁ። 17682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት ተሰጥቶናል። ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናቸዋለሁ” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለጥምቀት በዓል አከባበር ከአገሪቱ የሚመለካታቸው አካላት ጋር ተነጋገርው ሁሉም ዓይነት ትብብር እንደሚደረግ አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን እየተጠናቀቀ ነው። የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል ተገብቶልናል” ብለዋል። “ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትእምርቶች ናቸው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

See also       የስኳድ ሰነድ - ፩

Leave a Reply