መንግስት ትህነግን ” እረፍ” ሲል አስጠነቀቀ

መንግስት በትህነግ በኩል የሰላም አማራጭ ስምምነቱን በሚጎዳ መልኩ የተደረጉ ያሉ እንቅስቅሴዎች መልካም ጅምሮችን እንዳይጎድዱ ስጋት እንዳለው ገልጾ አስቸኳይ እርምት እንዲወሰድ ማሳሰቡን አመለከተ።

የ፣መንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ እንዳሉት ትህነግ በአመራቹ ጭምር የሰላም ስምምነቱን የሚጎዳ ተግባር እየፈጸመ ነው። በሰላም አማራጭ ስምምነቱ መረሰት አንዱ ወገን ሌላውን የሚያቆሽሽና የሰላም ሂደቱን የሚያውክ ቅስቀሳ ለምቆም ውል መታሰሩን በማስታወስ ነው መንግስት ለትህነግ ” እረፍ” የሚል ማስጠንቀቂያ የሰጠው።

የተለያዩ የትግራይ ከተማዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰላም መምጣቱ እንዳስደሰታቸውና ከዚህ በሁዋላ የጦርነትና የግጭት ድምጽ መስማት እንደማይፈልጉ እየተናገሩ ባለበት፣ ስለ መልሶ ግንባታና ማቋቋም በስፋት እንደሚሰራ በሚሰማበት፣ የቆሙ ፋብሪካዎች እንዲጀምሩ ሩጫ መጀመሩና መሶበ ሲሚንቶ ምርት መጀመሩ ተስፋ ሆኖ በቀረበበት፣ የትግራይ ነዋሪዎች ዓመት በዓለን ከሶስት ዓመት በሁዋላ በሰላምና በደስታ ማክበራቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት መንግስት ” ስምምነቱን ተጥሷል” ሲሉ ማስታወቁ ድንግጤን ፈጥሯል።

መንግስት ውሉን አክብሮ የሚቆጣጠራቸውን ሚዲያዎች በሙሉ እንደሚከታተልና ይህ ነው የሚባል ጉድለት እንዳላገኘ ዶክተር ለገሰ አመኦክተዋል። በትህንግ በኩል ግን ” አንዳንድ” ሲሉ ስማቸውን ያላነሷቸው አመራሮች ሳይቀሩ ስምምነቱንመጣሳቸውን አስታውቀዋል።

አንዱን ጨፍጫፊና ገዳይ፣ ሌላውን ነጻ የሚያደረግ ቅንብር ከትግራይ እንደሚተላለፍ ጠቅሰው፣ ” ይህ አካሄድ የሰላም አማራጩን እንዳይጎዳው” መንግስት ስጋት እንደገባው አመልክተዋል። አያይዘውም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ለአመራሮቹ ተነግሯቸዋ። ብለዋል። በዚሁ መሰረት እርምት ይወሰዳል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።

ዘግይቶም ቢሆን በደፈናው አያያዙ ደግ እንዳልሆነ በመንግስት በኩል ይገለጽ እንጂ የተለያዩ አካላት ጉዳዩን ሲተቹበት ነበር። መንግስት አቋም እንዲወስድ የጠየቁም አሉ። መንግስት ከማስጠንቀቁ ውጭ በቀጣይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ይፋ አላደረገም።

የኤርትራና የአማራን ስም በማንሳት በስፋት የጥላቻና የጨፍጫፊነት ማዕረግ በመስጠት ማውገዝ የተለመደ መሆኑ ይታወሳል። ከትህነግ ካራ ተርፎ ራሱን ያደራጀውና ከአፍሪካ ሃያል ለመባል የቃውን የአገር መከላከያንም የመክስስ ስሜት ያላቸው ዘገባዎችም በትግራይ ሚዲያዎች ይተላለፋሉ።

በትግራይ የፖለቲካው አካሄድ በቅርቡ ሊቀየውር እንደሚችል የትግራይ አንዳንድ አካባ ቢዎች ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ትህነግ ቅሬታ እንዳደረበት እየተሰማ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ህዝብ ” ልጆቻችንስ” የሚል ጥያቄና ” ለምን ተዋጋን? ምንስ አገኘን?” የሚል ጉምጉምታ እየሰፋ በመሄዱ ይህንኑ ለማስታገስና ሌሎችን ተጠይቂ በማድረግ ራስን ነጻ የማውጣት ፕሮፓጋንዳ ስለመሆኑም የሚናገሩ አሉ።

See also  "በትግራይ ክልል ከኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ውጭ በግዳጅ ላይ ያለ ሌላ የፀጥታ ሀይል የለም"

ይህ እስከተጻፈ ድረስ ትህነግ ለመንግስት ማስጠንቀቂያ የሰጠው ምላሽ የለም።

Leave a Reply