ሚኒስትር የነበሩት ታከለ ኡማ ” አክቲቪስ ሆኑ”

– 2 ቢሊዮን በርሜል የነዳጅ ድፍድፍ መኖሩ ተረጋግጧል ዜናና የታከለ ኡማ ተማጽኖ …

የቀድሞ የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ሳይሆን ከተነሱ በሁዋላና መነሳታቸው ይፋ ሊሆን ሰዓታት ሲቀሩት የሰጡዋቸው መረጃዎች ” ወደ አክቲቪዝም እየተምዘገዘጉ ነው” የሚል ትችት እያስነሳባቸው ነው። በተለይም አሁን ላይ “አሜሪካ ልሂድ፣ ትምህርቴን ልቀጥል፣ አመቻቹልኝ” ሲሉ መማጸናቸው ከተሰማ በሁዋላ “አክቲቪስት” የመሆን እዳላቸው ሰፊ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

በስልጣን ወንበራቸው ላይ በነበሩበት ወቅት የሰሩትን ስራ ከህግና ድንብ ማነቆ በቀር በከፍተኛ የብቃት ደረጃ ማከናወናቸውን በቢሯቸው ሪፖርተሮችን ጋብዘው ባስተላለፉ ማግስት ስንብታቸው የተሰማው ታከለ ኡማ፣ በማህበራዊ ገጻቸው “በአማራ ክልል የአባይ ተፋሰስ አካል በሆነው ወረኢሉ በተደረገ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት ከ2  ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት ተረጋግጧል” ማለታቸው “ለምን ይህን አሉ? ምን ለማስተላለፍ ፈልገው ነው?” በሚል የተለያዩ አስተአየቶችን እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል።……………………

“ስለ ወሎ ነዳጅ አንዳንድ ነገሮች ” ሲል ኢስለማን የአባይ ልጅ ቅድሚያ ወስዶ ኩርኩም የጀመረው “ሲሾሙ ሸሽገውን ሲሻሩ ውዥንብርን የነዙብን ኢንጅነር ታከለ ኡማ” ብሎ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን በርካቶች ተመሳሳይ ጥያቄ አንስተዋል። እስሌማን ይህን ሲል ነጥቦችንም አንስቷል።

  • ወሎ የነዳጅ ሀብት እንዳላት በጥናት ከተረጋገጠ ዓመታት ተቆጥረዋል።

በወረኢሉ የሚገኘውን ነዳጅ ሀብት አጥንቶ ወደ ምርት ስራ ሊገባ የነበረው ፋልካን የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ በ 2018 ስራው እንዲቆም ነው የሆነው። በወቅቱ ኩባንያው ለምን ስራ ያቋረጠበት ምክንያትም ሆነ በጥናቱ የተገኘው የነዳጅ ሀብት መጠን ሚስጥር ነበር የተደረገው።
https://radiohormuud.dk/news/ethiopia-auction-second-crude-oil-production-site

  • “አዲስ የነዳጅ ግኝት የተገኘ በሚመስል አቀራረብ ትላንት ኢ/ር ታከለ ኡማ የለጠፉት መረጃ፣ ስህተትም ብዥታም ያለበት ነው። በራሳቸው ልጥፍ ላይ ብቻ ተመስርተን ብንመለከት ይህንኑ እናረጋግጣለን።
  • ሁለት ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ የተገኘው በደብረሊባኖስ እንጂ በወረኢሉ አይልም፤(በፓወርፖይንት የቀረበው የኢ/ር ታከለ መረጃ)።
  • ይህንኑ ነዳጅ ለማውጣት የሚያስፈልገው ግምታዊ ገንዘብ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ዶላር ዋጋ ራሱ የዛሬ 10 አመት የተጠና ነበር። ይህም በፈረንጆቹ 2013 ላይ መሆኑ ነው። የጥናቱ ግኝት ከተጠናቀቀ ከሰባት አመት በኋላ በማዕድን መስሪያ ቤቱ የተሾሙት ኢ/ር ታከለ ሶስት ያህል አመት በስልጣን ሲቆዩ ይህን ለምን አልነገሩንም። ሲሰናበቱ ደሞ የተምታታ መረጃ መስጠት ለምን ፈለጉ? ችግሩስ ከማን ላይ ይሆን?
See also  መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታወቀ


በዚህ ማስፈንጠሪያ (ይንብቡት ወይም ከስር እንዳለ በእንግሊዝኛ ቀርቧል)የኢትዮጵያ ሄራልድ እሳቸውን ጠቅሶ መዘገበው ዜና ላይ፣ አቶ ታከለ ስለ ወረኢሉ ያሉት ነገር የለም።

(ENA) Ministry of Mines and Petroleum revealed today that it has opened 22 mining and 5 petroleum sites as well as 3 service areas for investors.

Briefing journalists, Mines and Petroleum Minister Takele Umma said the potential areas for mining and petroleum have passed exploration stage.

Laboratories, drilling and refinery services are the other potential investment areas currently opened to market, he added.

The potential areas in mining sector include deposits of iron ore, gold, phosphate, potash, marble, coal, gemstone, limestone, chlorine, sodium chlorine, among others.

Identified petroleum potentials in Ogaden, Gambella, South Omo and Rift Valley are under concession, negotiation and open for oil and gas exploration, it was learned.

The minister called on businesspersons to invest in the mining and petroleum extraction potential areas and services.

According to Takele, the ministry has been working in collaboration with the relevant ministries to create conducive environment for investors by amending policies and laws that hinder the development of the sector.

የወረኢሉ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን በዚህ ዙሪያ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከአመታት በፊት “ፋልከን” የተባለ የውጭ ድርጅት አካባቢው ላይ ተስፋ ሰጭ ጥናት ማድረጉን አስቀድሞ ማስታወቁ እንዳለ ሆኖ፣ ታከለ ኡማ እንዲህ ያለ ታላቅ ዜና በፌስ ቡክ ለማሰራጨት ለምን ወደዱ? የሚለውን ጥያቄ ቃል በቃል የመለሱ የሉም። ግን በኦሮሚያ ምክትል የቢሮ ሃላፊ ሆነው እንዲመደቡ አሳብ ስላለ ” ይህ ያህል ስራ የሰሩ ሚኒስትር ወደ ወረዳ ቢሮ ዝቅ ማድረግ አግባብ አይደለም” የሚል ገበያ ፈልገው ሊሆን እንደሚችል የገመቱ አሉ።

See also  "ውድ ወገኖቼ...ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ" አብይ አህመድ

በብሄር ፖለቲካ ያደጉና የገነገኑ ሰዎች ምን ግዜም ይህን አጀንዳ እንደሚያመቻቸው ከመጠቀም የዘለለ ሌላ ልምድ ስለሌላቸው አቶ ታከለም ይህን ሊያደርጉ አስበው ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩ ” አሜሪካ ልሂድ ብለው አማላጅ ልከዋል። ያው የተለመደውን የአክቲቪዝም ስራ የጀመሩት ለዚህ ነው” ብለዋል።

Leave a Reply