“ጠንካራ መከላከያ ስንገነባ እንከበራለን” ሲሉ ይህ ደረጃ ይደረሳል ያሉ አልነበሩም። ኢትዮጵያ የተንኮታኮተውን አየር ሃይሏን አመድ አራግፋ በአጭር ጊዜ በዚህ ደረጃ ጠላትን የምታስፈራ ትሆላች ብሎ ያሰበ አልነበረም። አብይ አህመድ ግን ያሉትን ያደረጉ ይመስላል።

በአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት አየር ሃይልና በሜካናይዝድ ክፍለጦሩ በአንድነት ተቀናጅተው በጥምር ጠላትን እንዴት አመድ እንደሚያደርጉ አሳይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥና ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት በዚህ ወታደራዊ ትዕይንት የሰራዊቱ ብቃት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ የታጠቀችው መሳሪያም አፍ ያስያዛል።

“አየር ሃይልና ሜካናይዝድን በማዘመን ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሳሪያና በውስን የሰው ሀይል፣ በፍጥነት የመጨረሰ አቅም እንገነባለን” ብለው ቀደም ሲል የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተእይንቱን ካዩ በሁዋላ የደገሙት ይህንኑ ንግግራቸውን ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ

እንደተባለውም በአጭር ጊዜ፣ በቴክኖሎጂ በመጠቀም በአነስተኛ መስዋዕትነት ግቡን እንዲመታ ተደርጎ የተሰራው ይህ የአገር አለኝታ በታጠቀው መሳሪያ፣ በጣምራ ጠላትን እንዴት ተናቦ እንደሚወቅጥ ሲያሳይ የመከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጇላ፣ ምክትል ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ፣ የአየር ኃይል አዛዥ ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የፌደራል ፖሊሲ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤልና ሌሎችም የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና መኮንኖች መገኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

” የምንሰራውና የምናስበውን ጠላቶቻችን ናቸው በደንብ የሚረዱት” ሲሉ ደጋግመው ዜጎች በፕሮፓጋንዳ እንዳይጠለፉ ሲወተውቱ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ለማኝ የተደረገውን፣የተከዳውንና የታረደውን የኢትዮጵያ አለኝታ የአገር መከላከያ ሰራዊት እዚህ ደረጃ መድረሱን የተረዱ እንደማይቻል አውቀው ከመነገዳቸው ለመመለሳቸው ማስረጃ ነው።

በብዛት፣ በጥራት፣ በዘመናዊ ትጥቅና በቅለም ትምህርት የበለጸጉ መኮንኖችን የያዘው የኢትዮጵያ ጦር የቀጠናው ልዩ ሃይል ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ሩቅ በማሰብ ባህር ሃይሏን አደራጅታ ዝግጁ የሆነችው ኢትዮጵያ በሚመጥናት ደረጃ ደጀኗ ስለመሰራቱ የአየር ሃይል ውጤታማነት፣ የእግረኛው ጦርነትን በአጭር ጊዜ የመከውን ብቃትና ውስጡ ” ኢትዮጵያ” በሚለው ቀለም የተዋበ ከመሆኑ ጋር ልዩ ደስታ የሚሰጥ ነው።

በዚህ የጥምር ሃይል ትዕይንት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቢሾፍቱ አየር ኃይል ዋና መምሪያ ተገኝተው በዝግጁነት ላይ የሚደረጉትን ማሻሻያዎች መጎብኘታቸውም ታውቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም report

ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሣሪያ እና በውስን የሰው ኃይል የመጨረሰ ዐቅም እየተገነባ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

አየር ሃይልና ሜካናይዝድን በማዘመን ወጊያን በመሳሪያ ቴክኖሎጅ እና በውሰን የሰው ሀይል የመጨረሰ አቅም እየተገነባ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒሰተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በአዋሽ አርባ ወጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በአየር ሃይልና ሜካናይዝድ ተቀናጅቶ የተካሄደውን የጥምር ጦር ወታደራዊ ትርኢት ተመልክተዋል፡፡

በዚሁ ወታደራዊ ትርዒት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና የመከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

መከላከያ እንደግብ አስቀምጦ ካከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል የመከላከያ ሠራዊቱን አቅም በክህሎት እና ዘመኑ ባፈራቸው ትጥቆች አዘምኖ ሠራዊቱ ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ አንዱ ሲሆን አሁን ላይ መከላከያ የደረሰበትን አቅም በሚያሳይ መልኩ የሜካናይዝድ እና የአየር ሃይል ጥምር ቅንጅትን የሚያሳይ ወታደራዊ ትርኢት በአዋሽ አርባ ውጊያና ቴክኒክ ማሰልጠኛ ማዕከል ቀርቧል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዬ ዘመናት ያጋጠሟትን ፈተናዎች ሁሉ በድል መወጣት የቻለችው በጀግኖች ልጆቿ መሰዋዕትነት ነው። ይህ የጦርነት ታሪክ ደግሞ በአብዛኛው ብዙ የሰው ሃይል በመጠቀም ሰለነበር ጀግኖቿ አላሰፈላጊ መሰዋዕትነት ከፈልዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አሁን ላይ ግን መንግሰት በወሰደው የፀጥታ ተቋማትን የማደራጀትና የመገንባት ሰራ መከላከያ ዘመኑ ያፈራቸውን ዘመናዊ የጦር መሳሪዎችን በማስታጠቅና እሱን መጠቀምና መምራት የሚችል በተግባር ተፈትኖ ያለፈ በቂ የሰው ሃይል ተገንብቷል ብለዋል።

አሁን ላይ አየር ሃይልና ሜካናይዝዱን በማዘመንና በማቀናጀት ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሳሪያ አካሃድ በትንሽ የሰው ለመጨረስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል ።

ዛሬ የታየው ትርዒትም ጠላቶቻችን ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርግና ጦርነትን በሩቁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆኑንም አመላክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰልጣኞችን ብቃት ከፍ የሚያደርጉ የምሰለ ተሸከርካሪ /ሲሙሌተር/ ጉብኝትም አድርገዋል።
ሰልጠናቸውን አጠናቀው በትርዒቱ የተሳተፉ የሰራዊት አባላትም ዘመናዊ መሳሪያዎችን ታጥቀናል ፣ በሚገባም ሰልጥነናል ሀገራችን ከየትኛውም ጠላት መከላከል የሚያስችል አቅም ፈጥረናል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአካል ተገኝተው ሰላበረታቷቸው ደግሞ ትልቅ የሞራል ሰንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply