“ወድቀናል ፣ተሸንፈናል” ትህነግ እየተፍረከሰ ወይስ እያታደሰ ? የዕግድ ዜና ተሰማ

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሲል የሚጠራው ትህነግ፣ ወዴት እያመራ ነው? ወዴት ሊያመራ ይችላል? ቀጣይ ዕድል ፈንታውስ ምንድን ነው ? በሚል ከየአቅጣጫው አሳብ እየተሰጠ ቆይቷል። ራሱን አግዝፎና ጦርነትን ሰሪ አድርጎ ሲያቀርብ የኖረው ትህነግ በቅርቡ ” ምንም ወሬ ማብዛት አያስፈልግም ተሸፈናል” ሲሉ ኮሎኔል ቢኒያም ይፋ እንዳደረጉት አሁን ላይ የትህነግ መሸነፍ ሳይሆን አነጋጋሪ የሆነው ቀጣይ እጣ ፈንታው ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አቅም ገና ከጅምሩ መስክረው ወደ ትግራይ ከገቡ በሁዋላ ለመንግስት ለውጥ ወደ ትግሉ የገቡት የቀድሞው የኢንሳ አባል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ከTPM ጋር በነበራቸው ቆይታ ” ወድቀናል ተዋርደናል ተሸንፈናል።ከዚህ ሃቅ መሸሽ አንችልም።አሸንፈናል ገለመሌ ብንል ራሳችንን ከማታለል ያለፈ ፋይዳ የለውም።የሰላም ስምምነቱንም ቢሆን ምንም የተለየ ነገር ስለፈጠርን የሆነ ነገር አይደለም ፤ ወደን ሳይሆን ተገደን ነው የፈረምነው” ብለዋል። ይህን በተሰማ ማግስት ውስጥ ውስጡን ሲሰማ የነበረው ወሬ ይፋ ሆኖ የትህነግ አመራሮች ስብሰባ መቀመጣቸው የተሰማው።

” በቅርቡ ጦርነትን እንጠብቃለን። አንድ ነገር ይሆናል። በዚህ መልኩ መቀተል አይቻልም..” ሲል ለራይድ ደንበኛው ትህነግ በድል አዲስ አበባ እንደሚገባ ተስፋውን የገለጸውን ወጣት በማስታወስ በማህበራዊ ገጻቸው ከወር በፊት የጻፉ ” የትግራይ ተወላጆች አብዛኞቹ ጦርነት በሚባል ነገር ራሳቸውን ልዩና የማይሸነፉ አድርገው መቀስቀሳቸውን ያረጋገጥኩበት ቀን ነበር” ሲሉ ሾፌሩ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ሆኖ የነገራቸውን ያስታውሳሉ። አይይዘውም “ውጭ አገር ያሉትን የትህነግ ደጋፊዎች ደግሞ እነሱ የሚያደርጉት ጦረነት አክተሩ የማይሞትበት የአክሺን ፊልም እስኪመስል ድል አድራጊነታቸውን ቅንጣት አይጠራጠሩም። ግን የሆነው ሁሉ ሆነ። ለወደፊቱ ታላቅ ትምህርት ይሆናል”

“… ድርጅታቸው ትህነግ ቢወድቅ የሚነሳ ግን ያማይሰበር፣ ቢደክመው የማይዝል፣ ቢጠማው የማይቆም፣ ቢርበው የማይበገር፣ ተራራን ሜዳ አስመስሎ የሚከንፍ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ ተፈጥሮን ጭምር የሚሰግዱለት፣ ከታንክና ድሮን፣ ከሚሳይልና ሮኬት ጋር እጅ በእጅ የሚፋለምና የሚረታ ታርዛን … አድርገው ያዩ የነበሩ አሁን ድረስ አይናቸውን፣ ጆሯቸውን፣ ቀልባቸውን መሰብሰብ አልቻሉም” ብለው የግል ሃዘናቸውን የጻፉ እንደሚሉት ዛሬ በትግራይ ሁሉም ነገር እየተቀየረ ነው።

See also  “በወሎ ህዝብ ውሎና ክራሞት ዙሪያ ግምገማ ይደረጋል፤ የቃለ-መሃላ ማረጋገጫ ይዘጋጃል”

የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መቀመጡና አዲስ አመራር ለመሰየም ሲተጋተግ መሰንበቱን የትግራይን ጉዳይ በቅጡ የሚያውቁና ለራሳቸው በሚያመቻቸው መልኩ የሚያስተላልፉ እንዳሉት የትግራይ ክልልን ለመምራት ዶክተር ደብረፂዮን፣ ሌተናለ ጄነራል ፃድቃንና ታደሰ ወረደ ፉክክር ላይ መሆናቸውን ዘግበው ነበር። በዘገባቸው ትግራይን በጊዚያዊነት ለመምራት ቢሉም በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት አዲስ የሽግግር አስተዳደር እንደሚቋቋም፣ ይህም ስምምነት ያደረጉት ምርጫም ህገወጥ እንደሆነ በማመናቸው ስለሆነ አዲስ ምርጫና አመራር ቢሰየምም አዲስ አስተዳደር ሲሰየም ሌሎችም እንደሚሳተፉ መንግስት ማስገንዘቡ ተሰምቷል። ምርጫ ቦርድም ይፋ አይናገር እንጂ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ታውቋል። በዚህ ምርጫ ትህነግ አንድ ተወዳዳሪ እንጂ እንደ ቀድሞ አራጊ ፈጣሪ እንደማይሆን ግምቱ ከፍተኛ ነው። ለዚህም ይመስላል ” ትህነግ በትግራይ ብቸኛ ድርጅት መሆኑ ካሁን በሁዋላ ማክተም አለበት” በሚል በሰፈራቸው ተሰሚነት ያላቸው ይፋ እየተናገሩ ነው።

ይህ እየሆነ ባለበት ወቅት ነው ኢሳት እምኞችን ጠቅሶ “የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አምስት ከፍተኛ አባላቱን አገደ”ሲል ያስታውቀው። ከትህነግ በኩል ምንም ዓይነት ዜና ባይሰማም፣ ስብሰባው ምርጫ ለማድረግ እንደሆነ ማስተባበያ ሊቀርብ አይችልም።የትህነግ ማእከላዊ ኮሚቴ በነበረው ስብሰባ “ተጠያቂነት እሰከሚረጋገጥ” በሚል ዕግዱን እንደጣለ ነው ኢሳት የገለጸው። በዚህ መሰረት

  1. ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
  2. ፈትለወርቅ ገብረዝጊሔር
  3. ጌታቸው ኣሰፋ
  4. ኣለም ገብረዋህድ እና
  5. ጌታቸው ረዳን ከማዕከላዊ ስራ ኣሰፈፃሚ አባልነታቸው አግዷል። ኮሚቴው ከጥር 7 እስከ 10/2015 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ስማቸው ከላይ የተጠቀሰውን አባላቱን ከተጠያቂነት ጋር በተያያዘ አግዷል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ያገዳቸው በጦርነቱ ለደረሰው ኪሳራ ሁሉ ተጠያቂ እናንተ ናችሁ በሚል እንደሆነም የመረጃ ምን ጮቻችን አረጋግጠዋል ሲል ኢሳት ዘግቧል።

መንግስት የፍትህ ማስፈጸሚያ ሰነድ አዘጋጅቶ ለውይይት ማቅረቡን ተከትሎ፣ ማንም ይሁን ማን በሰራው ወንጀል ስፋትና ክብደት አንሳር በፍትህ አግባብ እንደሚዳኝ የመወያያ ህግ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ከዳበረ በሁውላ እንዲጸድቅ ሂደቱ በተጀመረበት ቅጽበት ትህነግ ይህን አቋም መውሰዱ ” ነገሩን ወዴት ወዴት እየወሰዱት ነው” የሚል ጉጉት ፈጥሯል።

ጦርንቱ የተጀመረበት ጭብጥ ምክንያትም ሆነ መከራከሪያ ማቅርበ እንደማይቻል በርካቶች ሲናገሩ ነበር። በተለይም በትግራይ ሁለት አስርት ዓመታት በዋሻ ውስጥ ሆኖ ህዝብና አገር ሲጠብቅ በኖረ የአገር መከላከያ ላይ የተፈጸመው ክህደት በምንም መስፈርት ማጣፊያ ሊቀርበበት እንደማይችል የሚናገሩ፣ ” በድርድር እርቅ ማውረድ መልካም ነው። ግን ዕርቅ ያለፍትህ ቋሚ አይሆንም” በሚል ሲተቹ ነበር።

See also  እነ 360 የሃሰት ዘገባቸው ይፋ ሆነ፤ ፖሊስ በድጋሚ ቪዲዮ ይፋ አደረገ

በትግራይ አንድ ሚልዮን የሚጠጉ ታጣቂዎች ህይወታቸው እንዳለፈ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን፣ ለዚህ ሁሉ ውጣት ዕልቂት ምክንያት ለማቅረብ ትህነግ ስለማይቻለው ውሎ አድሮ ከህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሳበት አስቀድሞ ሲገለጽ ነበር። በተለይም መንግስት በሚቆጣጣራቸው የትግራይ አብዛኛው ክፍል ህዝቡ በቂ መረጃ ማግኘቱ ለትህነግ ቀጣይ ህልውና አደጋ እንደሆነ እየተሰማ ነው።

የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨትና የሃሰት ቅስቀሳ በማድረግ ስማቸው ሲነሳ የነበረው አቶ ጌታቸው ረዳን ጭምሮ ትህነግ አገዳቸው የተባሉት አመራሮች መጨረሻ ምን እንደሚሆን ከጊዜው ባይታወቅም ” ትህነግ ቢያንስ ለሁለት ይከፈላል” የሚለውን የቆየ ግምት እውን ሊያደርገው እንደሚችል እየተገለጸ ነው።

“የትግራይ መከላከያ ሃይል” ሲሉ የሚጠሩት ተዋጊ አመራሮች፣ በትህነግ ቀደም ሲል የተገፉና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ እንደሆነ የሚገልጹ ምን አልባት ይህ ቡድን ትህነግን ይዞ ስሙን በመቀየር ከብልጽግና ጋር የስምምነት አሳብ ሊያቀርብ እንደሚችል የሚገምቱ ” ወታደራዊ ሃይል የያዙ ናቸው ስምምነቱን እየተገበሩ ያሉት፣ ነገሩን የሚጨርሱትም እነሱው ናቸው። ሌሎቹ አጃቢዎች ናቸው” እያሉ ነው። እንደ ምሳሌ ሲያነሱም በፕሪቶሪያ ስምምነት የተሳተፉት ድርጅቱ ያሰናበታቸው ነጋዴዎች የተካተቱበት ነው።

“ትህነግ እየተፈረከሰ ወይስ እየታደሰ” በሚል የሚጠይቁ በበረከቱበት ወቅት የተሰማው ዜና አጓጊ አድርጎታል። ምንም ይሁን ምን ትህነግ ከአሁን በሁዋላ የትግራይን ህዝብ ልብ የሚገዛበት አቅም እንደማይኖረው ግን ስምምነት አለ።

Leave a Reply