ዓለም ባንክ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረ

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ745 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ745 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ዑስማን ዳዮኔ ፈርመዋል።

በድጋፍ የተገኘው ገንዘብም ለጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ለጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ተግባር የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል።

በዚህም 445 ሚሊየን ዶላሩ በተለይም በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች መሰረታዊና ፍትሕዊ የጤና አገልግሎት የሚውል ሲሆን ቀሪው 300 ሚሊዮን ዶላር ደግም የጎርፍ አደጋን የመከላከል ፕሮጀክቶች ይውላል ተብሏል።

ድጋፉ በጤናው ዘርፍ ፕሮጀክት ከ22 ሚሊየን በላይ ዜጎች እንዲሁም ለጎርፍ አደጋ መከላከል ፕሮጀክት በአየር ንብረት ተፅዕኖ ተጋላጭ የሆኑ 34 ሚሊዮን ዜጎች በተለይም ሴቶችና ህፃናትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የዓለም አቀፍ ልማት ማህበር በሚል ማዕቀፍ ድጋፉ የተደረገ ሲሆን በሶስኛ ወገን ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲዎች በኩል ይፈፀማል ተብሏል።

See also  "ግብጽ የአረብ ሊግ መሪነቷን በመጠቀም የዓባይ ግድብ ላይ ያላትን ኢፍትሃዊ ፍላጎት ለማሳካት እየሞከረች ነው"

Leave a Reply