“የወደቁት ተማሪዎቻችን  ብቻ ሳይሆኑ የወደቅነው እንደሃገር ነው”

50 በመቶ በታች ያመጣ ማንኛውም ተማሪ ዩንቨርስቲ አይገባ ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ

በቀጣይ በቀረበው የመፍትሄ አቅጣጫ የተዳከውሙባቸውን ትምህርቶች በዩንቨርስቲ ዳግም እንዲማሩ ተደርጎ በአመቱ መጨረሻ እንዲፈተኑ በማድርረግ ያለፉት የዩንቨርስቲ ስርዓቱን እንዲቀላቀሉም ይደረጋልም ብለዋል ።

ሚኒስትሩ ጨምረው የወደቁት ተማሪዎቻችን  ብቻ ሳይሆኑ የወደቅነው እንደሃገር ነው ያሉ ሲሆን ተማሪዎች በሚገባው ስነ ምግባር ትምህርታቸውን አለመከታተላቸው  ሁሉም ተጠያቂ ነው እንዲሁም በመንጋ ደረጃ እንደፖለቲካ አስቦ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳችን ያሳዝናል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። 

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አደርጓል!

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አድርጓል።የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች  መሰጠቱን አስታውሰው ይህ አዲስ አካሄድ ቀጣይ እርምጃዎቻችንን የሚለኩ ነበሩ ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ!…
በዘንድሮው ውጤት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት በቀጥታ ዩንቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ይጀምራሉ።
ከ50 በመቶ በታች ያመጡት ደግሞ እንደየነጥባቸው ተመርጠው ዩኒቨርስቲዎቻችን የሚችሉትን ያህል ዩንቨርስቲ ገብተው አንደኛ ዓመት ሳይሆን የቅድመ ዩንቨርስቲ ትምህርት ይማራሉ።
ከዚያም በዓመቱ መጨረሻ ላይ ይፈተኑ እና ካለፉ ዩኒቨርስቲ አንደኛ ዓመት ይገባሉ። ከወደቁ ወደቤታቸው ይገባሉ።

ሀቀኛ እና ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ክህሎት በመለካት  የፈተና ሂደቱ ከኩረጃ፣ የፈተና ስርቆት የፀዳ ነው ተብሏል።በዚህ ፈተና ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሚኮሩበት ነው ተብሏል።

በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 3354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92.2 % 908ሺ ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል።

በደንብ  ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

በ2014 የትምህርት ዘመን 899ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30.2 እንዲሁም ሴቶች 28.09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

See also  ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደብረብርሃንን ባዶ ማድረግ- የትህነግ የዳግም ወረራ ምኞት! "በትግራይ ኑሮ ርካሽ ነው"

በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቢ ሲሆን  የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዮነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሀረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤  666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች።በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

Via- sheger_press

Leave a Reply