በመጨረሻ ትህነግ “አልገዛልህም” ላለው ብልጽግና መሪዎቹ ሪፖርት አቀረበ፤

ስም እየጠሩ የውስጥ እጃቸውን በማማታት፣ ያለቀ የደቀቀ ጉዳይ እንደሆነ ሲያስረዱ “አብይን ጆባይደን፣ ኤርዶጋን፣ ፑቲን፣ ሳዳሙሴን አያድነውም። ምናልባትም ካዳነው ጆ ባይደን ነው” ነበር ያሉት። ለዚህ ንግግራቸው “ጀጋኑ” እየተባሉ የፌስቡክ አበባ ሲረጭላቸው የነበሩት አቶ ጌታቸው በተለያዩ ምስሎች እንደታየው አብይ አሕመድን በሙሉ አይናቸው ማየት የቻሉ አይመስልም። ” ያ ሁሉ ቀረርቶ” ውሃ በልቶት፣ በሙሉ ኪሳራ ትህነግ በጆን ባይደን ምልጃ “ሽንፈቱ አምሮለት” ሪፖርት ለማቅረብ አዲስ መንደር መገኘቱ ተሰምቷል።

የመንግስት መገናኛዎች በምስል አስደግፈው እንዳስታወቁት “የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት” የሚባሉት አካላትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ያገኟቸው ሐለላ ነው። ሐለላን የትህነግ ወኪሎች በስልጣን ዘመናቸው እንደማያውቁት ቀደም ብሎ ተመልክቷል።

ትህነግ “ብልጽግናን አልቀላቀልም” ብሎ የፌደራል ሃይሎችን በማሰብሳሰብ አዲስ መንግስት መስርቶ ዳግም ወደ አራት ኪሎ ለመመለስ እንቅስቃሴ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ ዘመቻ ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል። ይህም ዘመቻ “ዲጂታል ወያኔ” በሚባለው የደረጀና ከአንድ ምንጭ ተጠንቶ በሚለቀቅ የሚዲያ ወረራ ኢትዮጵያዊያንን ማህበራዊ ዕረፍት የነሳና አገሪቱን የማወክ አቅም ፈጥሮም ነበር።

“ለአብይ አልገዛም” በሚል ሃይል አሰልጥኖ፣ መከላከያ ላይ የክህደት ቃታ ስቦና የአገሪቱን መሳሪያ ታጥቆ ተደጋጋሚ ወረራ የፈጸመውንና ከፍተኛ ወነጀል የፈጸመውን ትህነግን የሚመሩት አካላት በሚሊዮን ህዝብ ካስጨረሱ በሁዋላ ነው ዛሬ ለአብይ አህመድ ሪፖርት ለማቅረብ ሐለላ የገቡት። የገበታ ለአገር ፕሮጀክት አንዱ አካል በሆነው በዚህ ድንቅ ፕሮጀክት ውስጥ ትህነግ ለብልጽግና ሪፖርት ሲያቀርብ የሚያሳዩ ምልስሎች የራሳቸው መልዕክት ከማስተላለፋቸው በቀር፣ ስለ ውይይቱ ዝርዝር የተሰማ ወሬ የለም።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አደረጉ” ከሚለው ዜና በቀር ምንም ዝርዝር መረጃ ያልተሰጠበት ውይይት ለበርካቶች አስገራሚ ሆኗል።

በምድር ላይ የተፈጠሩ የማቆሸሺያ ቃላቶችና ሃረጎች አንድም ሳያስተርፉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲሳደቡና ሲያወግዙ፣ እንዲሁም እስር ቤት ሲያማርጡና የፍርድ ሂደት ቡፌ ሲደረድሩ የቆዩት አቶ ጌታቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአይን ሲያዩ ምን እንደተሰማቸው ለማወቅ ነጮቹ እንደሚሉት ” ምነው የግድግዳ ላይ ዝንብ በሆንኩ” ብሎ ከመመኘት ውጪ የሚባል ነገር የለም። ይሁን እንጂ አብይ አህመድ አቶ ጌታቸውን የሚያዩበት፣ መላው ሪፖርት ለማድመጥ የተገኙት የብልጽግና ሰዎች የቅንድብ አጣጣል የራሱ ትርክት አለው።

See also  "ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ"

“ጦርነትን እንሰራዋለን፣ ባህላችን ነው፤ እኛን ሊገጥም የሚችል የለም። ገሃነምም ቢሆን ወርደን …” ሲሉ የነበሩት የትህነግ መሪዎች ከዚህ ጦርነት ምን እንዳተረፉ በውይይቱ ስለመነሳቱ፣ ሲመከሩና ሲለመኑ እምቢ ብለው ሚሊዮን ሰዎችን አስጨርሰው ለሪፖርት መምጣታቸው፣ ለዚያውም ” አንገዛልህም” ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሪፖርት ሲያቀርቡ መታየታቸው ” ካድሬዎች ከላይ ባዶ ናቸው” የሚለውን ብህል የሚያጸና እንደሆነ በስፋት አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ለምስኪኑ ህዝብ ሲባል ሰላም መውረዱ ቢደገፍም፣ በርካታ ዜጎች የሽግግር ፍትህ ሂደቱ ጎን ለጎን መጀመሩን ተከትሎ ውጤቱን እየተበቁ ነው። በውይይቱ እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ እንደተቀመጠ ተገልጿል።

በትግራይ የየትኛውም አገር ሰራዊት እንደሌለ መንግስት ሰሞኑንን ማስታወቁ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎም ቀደም ሲል ጫና ሲያደርጉ የቆዩ አገራት ድጋፍና አድናቆት ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ወደ ግንባታ ለመመለስ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጥሪ እየቀረበ ነው።

አብይ አህመድ ትህነግ ሃያ ሰባት ዓመታት ስልጣን ላይ እያለ እንደተፈጠረች እንኳን በማያውቃት ሐለላ ወስደው ሪፖርት መስማታቸው፣ ከሰላም አማራጩ ውይይት ዜና በላይ “ቦታውን ለምን መረጡት” የሚል ጥያቄና ግርምት እንደገነነ ባህበራዊ ሚዲያዎች ምስክር ናቸው። አንዳንዶች የሚያስፈግጉ አስተያየት የሰጡ ሲሆን ” የት ነን ኬንያ” ሲሉ የትህነግ ሰዎች በቀስታ እንደጠየቁ የገለጸው አስተያየት ሰጪ አንዱ ነው። ቦታው ወደፊት ቱሪስት በስፋት ይጎርፍበታል ተብሎ የሚታሰብና በልዩ ክትትል ገነት ሆኖ የተሰራ ለመሆኑ የጎበኙት እየመሰከሩ ነው።

ሲያወድም ከርሞ ልዩና ውብ የቱሪስት ከተማ ያዩት የትህነግ ሰዎች ከዚህ በሁዋላ “ጦርነትን እንዳይመጩም ያስችላቸው ዘንድ ታስቦ ነው እዛ የተወሰዱት” ያሉም አሉ።

ለመሆኑ ሀላላ ኬላ የት ነው ሀላላስ ማነው?

ከሰሞኑ በሚዲያ በተደጋጋሚ ስሙ የሚነሳው ሀላላ ኬላ የሚገኘው በዳውሮ ዞን ስሆን “ሀላላ ኬላ” ማለት የሀላላ ካብ ማለት ነው። ሀላላ ኬላ ወይም የንጉሡ ሀላላ የድንጋይ ካብ የጥንት ዳውሮ ስልጣኔ ማሳያ የሆነ የደረቅ ድንጋይ ካብ ነው።

Leave a Reply