ጅብ ፈርቶ የጮኸው ነብሰ ገዳይ ተያዘ

ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው የድረሱልኝ ጥሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ ዐ1 ልዩ ቦታው ፖራዳይዝ ሆቴል ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ጫካ በመግባት ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው ጩኸት በቁጥጥር ስር መዋሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቡ ከጅማ ዞን ሊሙ ሰቃ ወረዳ የአቃቢ ህግ ባለሙያ መሆኑንና ቴዲ ድሪባ እንደሚባል የመምሪያው የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዮሀንስ በየነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ የ4ኛ አመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነችውን ፍቅረኛውን ለመጠየቅ ወደ ደብረማርቆስ መምጣቱ ተነግሯል።በሰዓቱ ተጎጂ የሆነችው ግለሰብ ከዚህ በኋላ አንድ ላይ መቀጠል እንደማይችሉ ስትነግረው በጩቤ ወግቶ በጫካ አድርጎ ሲያመልጥ ከምሽቱ 5:00 አካባቢ ጅብ አግኝቶት አላሳልፈው ሲል ባሰማው የድረሱልኝ ጩኸት የመንቆረር ኮንስትራክሽን ጥበቃዎች ደርሰው ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ግለሰቧ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተደረገላት መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዮሀንስ በየነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

Via: ዳጉ ጆርናል

See also  የፌዴራል አቃቤ ህግ በአቶ ደመላሽ አድማሱ ታምር በሁለት ጉዳዳዮች ላይ ክስ መሰረተ

Leave a Reply