ETHIOREVIEW

ኦርቶዶክስ ሰላም ማውረዷን አወጀች፤ ጥላቻንና መለያየትን የሚያሰራጩ አክቲቪስቶች፣ሚዲያዎች፣ አባቶችና መምህራን አወገዘች

ኢትዮጵያ እንደለመደችው ትልቁን የዕልቂት ድግስ አሸንፋለች። በኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተከስቶ የነበረው አለመግባባት ፈውስ ማግኘቱን ተከትሎ ” “የዕርቅ መብረቅ ልዩነትንና የጸብ ጠማቂዎችን ሴራ መታ” ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ አሳባቸውን የገለጹ ብዙ ናቸው። ቤተክርስቲያን ራሷ የማህበራዊ ሚዲያዎችና የዩቲዩብ መገናኛዎች ሸብ መስበክና ማሰራጨት እንዲያቆሙ በይፋ ጠየቀች። ከዚህ ተግባር የማይመለሱትን በገሃድ አወገዘች። ባለ አስር ነጥብ መግለጫ አወጣች። ሙሉ መግለጫውና ቪዲዮው ከስር ቀርቧል።

በመግለጫው ጥላቻን የሚያባባሱ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ በሚለው የተራ ቁጥር ዘጠኝ አሳብ ስር “ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራንና አባቶች ፍቅርን ከሚያጠፉ፣ ጥላቻን ከሚያበዙና መለያየትን ከሚያሰፋ ነገር ሁሉ እንዲታቀቡ በእግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን” ሲል ተማጽኖ አሰምቷል። አያይዞም ” ይህንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉትን እናወግዛለን” ብሏል። በመገለጫው መሰረት ልዩነትን፣ ጥላቻን፣ ፍቅርና አንድነት እንዲከስሙ የሚሰብኩና የሚያሰራጩ ቤተክርስቲያን ባለት ሃዋሪያዊ ስልጣን ውግዝ አድርጋለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ” ይህ በመሆኑ፣ ይህን በማየቴ ከማንም በላይ ደስተኛ እኔ ነኝ” ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም ” ይህንኑ ሰላማችሁን ጥበቃችሁ ኑሩ። እኛን የሚያስደስተን ይህ ብቻ ነው” ብለዋል። አብይ አህመድ ከውጭ እንደሚወራው ሳይሆን መላካም አባቶች እንዳሉ መረዳት መቻላቸውና፣ ከሲኖዶሱ ጋርም የቅርብ ትወወቅ ለማደረግ በመቻላቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ስምምነቱ እየተካሄደ ሳለ “የሲኖዶስ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አባረው ራሳቸው ተስማሙ” ሲል ዘመድኩን የሃሰት ቅሰቀሳ ያሰራጨ ሲሆን በፊልም ተደግፎ በታየው መግለጫና የዕርቅ አካሄድ ላይ ተባረሩ የተባሉት ሁሉ በክብር ታይተዋል። ከኦሮሚያ ወገን ህዝብ ላቀረበው ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ምላሽ ምላሽ እንደሚሰጥ ያረጋገጠው መግለጫ በኦሮምኛና አማርኛ በተነበበና ሰላም መስፈኑን ቤተክርስቲያን ባስታወቀችበት ቅጽበት፣ “ለምን ሰላም ወረደ?” በሚል የተለያዩ የብስጭት መረጃዎች ተሰራጭተዋል። ማስፈራራትም እየተሰነዘረ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ዘመድኩን የሚባለውና በመረጃ ቲቪ እለት ዕለት እየወጣ ጥላቻን በማሰራጨት የሚታወቀው ዘመድኩን እርቁ ይፋ ሊሆን ደቂቃዎች ሲቀሩት ይህን ዜና አሰራጭቶ ተከታዮቹ እንዲያሰራጩ አሳቧል።

ከጅምሩ በመላቀስ፣ በሃዘንና ከልብ በሆነ መወቃቀስ እንደተጀመረ የተነገረለት የቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት፣ በማብቂያው ላይ አቡነ ማቲዎስ ” ግድ ሆኖብን፣ የቀኖና ነገር ሆኖ እንጂ እናንተን በማጣጣታችን ልባችን አዝኖ ነበር” ካሉ በሁዋላ “እግዚአብሄር ያብርክልን፣ የስራ ዘመንዎንም ይባርክልዎት” ሲሉ ችግሩ እንዲፈታ ታላቅ አስተዋጾ ያደረጉትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን አመስግነዋል።

አማትቦና የአምላክን፣ የቅድስት ድንግል ማሪያምን በመጥራት ሰበካ የሚጀምረው ዘመድኩን፣ በፈጣሪ ስም ጀምሮ እጅግ ጸያፍና ለመስማት የሚከብድ ስድብ ሲሳደብ መስማትና፣ እሱ ትዳር፣ ልጅ፣ አባት፣ እናት፣ ሴት ሳይለይ ሲያዋርድ ኮምፒውተር ስር ቁጭ ብለው የሚሰግዱለት በርካታ መሆናቸውን ራሱ በፎቶ ማሳየቱ ይታወሳል።

ስድቡን ሲጭርስና የማባላት ሴራውን ሲቋጭ ” አበሌን፣ የደንቧን አትሩሱ፣ አምጡ” እያለ እርጥባን ዕለት ዕለት የሚጠይቅ ነው። ከቀለም ጋር ህብረት እንደሌለው የሚነገርለት ዘመዴ የመረጃ ቲቪ ባለንብረቶች ምን ያህል እየከፈሉት እንደሚሰራላቸው አይታወቅም።

ሚዲያውን የከፈቱት ሰዎችም ዓላማቸው ግልጽ አይደለም። የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ጠንቅቀው የሚያውቅ ምን ፈልገውና ምን ተመኝተው በዚህ ተግባር ላይ ለመሳተፍ እንደወሰኑ በተደጋጋሚ የሚጠይቁ ሲሆን፣ ባለቤቶቹ አንድም ቀን መልስ ሰጥተው አያውቁም።

ችግሩ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እምነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲጠናከሩ እና ቤተ እምነቱን ለትውልድ ለማሻገር መፈታት ያለባቸው ሥራዎችን ለማከናወን መግባባት ላይ መደረሱን መግለጫው ያስረዳል።

Exit mobile version