በሲኖዶስ ስም ሲወጡ የነበሩ መግለጫዎች ሚስጢርና ጠላፊዎች ዳግም ያስጀመሩት ግብግብ

  • ሚስጢሩን ራሱ የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው መድሃኔዓለም ይፋ ያደርገዋል

ዛሬ አዲስ ወሬ ተስምቷል። ” ራሱን አዲስ ሲኖዶስ” ቀደም ሲል “የኦሮሚያና ብሄር ብሄረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል ስያሜ ራሱን ገልጾ ተቃውሞ ያሰማው አካል ዛሬ ምንም የተለወጥና አዲስ ነገር የለም ሲል ስምምነቱን መጣሱን ይፋ አድርጓል። ቅዱስ ሲኖዶስም ባስቸኳይ መግለጫ አውጥቷል። መግለጫውን በስተግራ ከጎን ያንብቡ።

ይህ ከሁለቱም ጎን በፖለቲከኞችና ልዩ አጀንዳ ባላቸው የተገዙ ሃይሎች እንደተጠለፉ የሚነገርባቸው ክፍሎች በውይይታቸው ክፍል አንድና ሁለት እንደተደመጠው የዕመንት፣ የቅድስና፣ የጽድቅና የበጎቻቸው ችግር አሳስቧቸው ሳይሆን በጥቅምና እዚህ ግባ በማይባል አስተዳደራዊ ችግር መቋሰላቸውን ህዝብ ከራሳቸው አንደበት ግንዛቤ ወስዶበታል።

ቀና አባቶች፣ ደግ አባቶች ያሉበትን ያህል ፖለቲካው የሚገፋቸውም ስለላሉ ነገሮች በሚገርም ፍጥነት ወደ አስጊ ደረጃ መድረሳቸው ዜጎችን ሁል አስጭንቆ ነበር።

ከመጨረሻው የሲኖዶስ መግለጫ በቀር ሌሎቹ መግለጫዎች በሲኖዶስ አባቶች እጅ የተጻፋ እንዳልሆነና እምነትን ተንተርሰው አጋጣሚውን ለመጠቀም ሲኖዶሱን የጠለፉ የፖለቲካ ሃይሎች ያዘጋጁት እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ይህ እውነት ጊዜውን ጠብቆ በአባቶች አንደበት ለህዝብ ይፋ እንደሚሆንም እየተጠቆመ ነው። በተመሳሳይ የኦሮሞና ብሄር ብሄረሰቦች ሲኖዶስ በሚል የተሰየመውም ቡድን በሌላ ጎራ ቢጠለፍም፣ ጠላፊዎቹ በመናበብ የሚሰሩ መሆናቸው የሚያሳዩ ምልክቶችና መረጃዎች እየወጡ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው ሁለተኛው ውይይት ” በፖለቲካው ያልተሳካላቸው እናንተም ውስጥ ገቡ እኛም ውስጥ ገቡ” ሲሉ አቡነ አብርሃም መናገራቸው ከላይ ለተገለጠው የዜናው አንኳር ጉዳይ ማስረገጫ ሆኖ ተወስዷል። ስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ የተሰማው ዳግም የመግለጫ ጦርነትም የዚሁ የጠላፊዎቹ አሳብ ባለመሳካቱ የተነሳ ለመሆኑ የዳግም ክፍፍሉ ዜና መሰማቱን ተከትሎ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት በቅብብሎሽ እንዲጎን መደረጉ፣ አለመግባባቱን ለማክረር የተኬደበት ፍጥነትና ጉዳዩ በፖለቲከኞች መጠለፉን የሚያሳይ መሆኑንን ጠቅሰው ሰፊ ትንተና ሲቀርብባቸው የነበሩት መግለጫዎች በአባቶች እጅ አለመዘጋጀቱን የገለጹት ጉዳዩን ቅርብ ሆነው ከሚከታተሉት መካከል ናቸው። እነዚህ አካላት የሰላም አሳቡን በሚጻረር መልኩ የመሄድ ወይም መልክን ቀይሮ የመስራት አዝማሚያ ሊኖር እንደሚችል ቀደም ሲል አመልክተዋል። እንዳሉትም ሆኗል።

See also  “ሱዳን ምንጊዜም የሚቆጫትን ስህተት ሰርታለች”

ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ ከዚያም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አጫጭር መግለጫዎች እርዕስና ንዑስ ርዕስ፣ ቃል በቃል በመስንጠቅ፣ ቃላትን በማመንዥግ ሲቀርብ የነበረው መግለጫ ይዘቱ፣ አቀራረቡና አንባቢዎችን ወደ አንድ ጽንፍ ስሜታዊ አድርጎ ለመውሰድ፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ለሚካሄደው የስም ማቆሸሽ ዘመቻ በሚያመች መልኩ እንዲሆን መደረጉ የአዘጋጆቹን ማንነት ግልጽ አድርጎ እንደሚያሳይ እንደሆነ እነዚሁ ክፍሎች አመልክተዋል። ይህ ዘመቻ የሳይበሩን የትህነግ ዘመቻ አካሄድ የተከተለና ” እረኛውን ግደል፣ መንጎቹ ይበተናሉ” የሚለውን መርህ የተከተለ ሆኖ ታይቷል። ይህን የሚጠራጠር ካለ መለስ በማለት ዳግም “በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ተዘጋጁ” የተባሉትንና ለወቅቱ ተንታኞች የተራቡትን መግለጫዎች መመልከቱ በቂ እንደሆነም የዜናው ሰዎች ፍርዱን ለአንባቢው ይተዋል።

ይህን ችግር ለማራገብ የተመረጠበት ወቅት፣ ችግሩን በማጦዝ ውይይትና ንግግር እንዳይደረግ የተቀሰቀሰበት አውድ፣ ከተደበቁበት በመውጣት ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳካት ቅስቀሳ የጀመሩትን አካላት ማንነትና የጅምላ ዘመቻ ቅንብር፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች በመናበብ ሲደረግ የነበረው ውትወታና ተራብተው የተሰጡ ማሰሪያ ሃረጎች ወዘተ የቅዱስ ሲኖዶስ ችግር መጠለፉንና፣ ” አማኝ ነን” በሚል ካባ አባቶችን በማዋከብ ወደ አደገኛ ቁልቁለት የገፏቸው አካላት እንደነበሩ ለመረዳት አዋቂ መሆን እንደማያስፈልግ ያስረዱት ክፍሎች ” አባቶች በቅጽበት ከቁልቁለቱ መንገድ ወጡ፤ ፖለቲከኞችን ወግዱ አሉ። ጉዳዩ የዚያኔ አበቃለት፤ ውሃ ተደፋበት” ይላሉ።

ከስምምነቱ ዜና በሁዋላ በስምምነቱ ቦታ ሆነው አስተያየት የሰጡ ሽማግሌ ” እሳቱ የጠፋው ዓርብ ነው” በማለት ስለሆነው ሁሉ ምስጋና ሲያቀርቡ ተደምጧል። ” የቅዱስ ሲኖዶስ የሰማዕትነት ጥሪ” የሚል ታግ ተለጥፎለት እሁድ እንዲካሄድ የተጠራው ሰልፍ መክሸፉ የፈጠረው ንዴት ክፉኛ ብስጭት የፈጠረውም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።

ችግሩ እንዲጎን ከአንደኛው ወገን ኦኤምኤን በሌላ ወገን ሌሎች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አውደኞች በመናበብ ሲያራግቡና ነዳጅ ሲከልሱበት የነበረው የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች አለመግባባት ከቁጥጥር ውጭ እንደሚወጣ፣ ቤተክርስቲያን ቀንና ሰዓት ወስና መንግስትን ማዘዝ ስትጀምር ” አባቶቻችን የሚያዙንን እናደርጋለን” የሚል መፈክር በስፋት ተሰምቶ ነበር። ይህ መፈከር ግን ስምምነቱ ይፋ ሆኖ አባቶች በምስጋና ዜናውን ሲያበስሩ ለተላፊዎቹ መንደር ሃዘን ነበርና ” አብቶቻችን ብቻ እንሰማለን” የሚለው የማደናገሪያ መሃላ ተሻረ።

See also  "አፍሪካ ኒውክለር ሀይል መገንባት አለባት"

እዚህ ችግር ውስጥ በክፍያ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማሳካት የተሰገሰጉ በየአቅጣጫው ” የሽግግር መንግስት ሰነድ አዘጋጅተን ጨርሰናል” ብለው አስቀድመው በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር ያስታወሱት የዜናው ሰዎች፣ ” ቤተመንግስት ስለመውረርና መንግስትን ስለመገልበጥ እያወጉ ባለበት ቅጽበት አባቶች ታጠፉ” ሲሉ በቅርብ የታዘቡትን ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች አሁንም እንደማያርፉና ሌላ መልክ ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል።

” መታጠፍ ብቻ ሳይሆን ዓርብ ዕለት ወጥተው ከስምምነት ደርሰናል። ፍርድ ቤትም በፍለግነው ደረጃ ውሳኔ ሰጥቷል። ደስ ብሎናል። ነገ ቀዳሚት ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን” ማለታቸው አዋራ ማስነሳቱ ፖለቲከኞችና የባዕዳን ጉዳይ አስፈጻሚዎች በጉዳዩ እጃቸውን በደንብ ማስገባታቸውን እንደሚያመለክትም ተጨማሪ ማስረጃ ይጠቅሳሉ።

“ጥያቄው የቀኖና ነበር። በውይይት ምላሽ አገኘ። የጉዳዩ ባለቤቶች በውይይት ተስማማን አሉ” በማለት በአመክንዮ አሳባቸውን የሚያስደግፉት ክፍሎች፣ ” ሲከርና ሊፈነዳ ሲቃረብ አባቶቻችንን ብቻ ነው የምንሰማው ሲሉ የነበሩ ለምን ዛሬም የአባቶቻቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ዛሬ ምን አለ በሚለው ዓምዳቸው አያቀርቡትም ቢባል፣ ምላሹ ዓላማው ግቡን አልመታም ነው” ሲሉ ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ጊዜ ከሚያባክኑ ቀጣዩ የትርምስ አጀንዳቸው ቢዛወሩ እንደሚሻል በምጸት ገልጸዋል።

” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሁለቱም ጋር እውነት አለ፤ በውይይት ፍቱት አሉ። እርግማንና ስድብ ወረደባቸው፣ እሳቸው እንዳሉት አባቶች አንድ ላይ ሆነው በመነጋገር ችግራችንን ፈትተናል። በእውነት ክርስቶስ ያለበት፣ የታየበት ነበር” ብለው ምስክርነት እንደሰጡ በማውሳት “ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አደረጉ” ያሉት ወገኖች ” ለጠላፊዎች ፖለቲከኞችና ሚዲያዎቻቸው “ጸብን፣ ጥላቻን፣ መለያየትን ከመስበክ እንድትታቀቡ በእግዚአብሔር ስም እንማጸናለን፣ ይሄንን የማታደርጉትን እናወግዛለን” በሚል ምላሽ ነገሩን መዝጋታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ በተለይም ለኦርቶዶክስ ቤተሰቦች ታላቅ ትምህርት የሰጠ ስለመሆኑ አመልክተዋል።

” የመጨረሻውን የሲኖዶስ መግለጫና ቀደም ሲል ሲወጡ የነበሩትን መግለጫዎች በማጤን እነማን በቤተክርስቲያን ስም አዋጅ ያውጁ እንደነበር ነገሮች ሲሰክኑ ለሁሉም ትምህርት ይሆን ዘንድ፣ ለንስሃም ይረዳ ዘንድ በዝርዝር እናቀርባለን። በውይይቱም ወቅት ምን እንደተነሳ በይፋ ማንም ሊያስተባብለው በማይችል መልኩ እናቀርባለን” ያሉት የመረጃው ሰዎች፣ “እሁድን እንዲፈስ የተፈለገው ደም፣ እንዲያልቅና እርስ በርስ እንዲጫረሱ የተፈረደባቸው የድሃ ልጆችን ህይወት ያተረፉ ሁሉ ታላቅ ገድል እንደፈጸሙ አምኖ መቀበል፣ ሽምግልናውን በብረሃን ፍጥነት ላከናወኑ ዋጋቸውን ማሰብ እጅግ ተቃሚ ነው። የጽንፈኞቹ አሳብ ሰምሮ ቢሆን ዛሬ ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ ትገኝ ነበር?” በማለት ሁሉም ረጋ ብሎ እንዲያስብ አስጠንቀቀዋል።

See also  የወንጀል ክስ እና የዋስ መብት

ራሱን የኦሮሚያ ሲኖዶስ የሚለው ወገን ምሎና ጎንበስ ብሎ በወጉና ደንቡ መሰረት እርቅ ማውረዱን ካስታወቀ በሁዋላ፣ ያቀረቡት ጥያቄ ሁሉ ምላሽ ማግኘቱ በአቋም መግለጫ አስር ነጥብ ይዞ ከቀረበ በሁዋላ ውሉን ማፍረሳቸው ምንም ምክንያት እንደማይሰጠው የሚገልጹ ” ጠላፊዎቻቸው አይሆንም በሚል የመገንጠሉን እጀንዳ እንዲገፉበት፣ ይህ አጀንዳ ደግሞ በኦሮሚያ ቀውስ እንደሚያስነሳ እርግጠኞች ስለሆኑና ብልጽግና ውስጥ ያሉትን የተጠለፉ ተጠቅመው የሚያደርጉት ነው” ብለዋል። ክልሉ በአስቸኳይ አቋም ሊይዝ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አባ ማትያስ ስምምነቱ ሲበሰር በሚያሳየውና የተለያዩት አባቶች ዳግም እጅ በመንሳት በክብር ዕርቅ ሲያደርጉ በተላለፈው ቪዲዮ ” የቀኖና ጉዳይ ሆኖብን እንጂ ” በማለት የሆነውን ሁሉ ቃል በቃል መናገር ተናንቋቸው ” እንዲህ ያልነው” ብለው ነው ያለፉት። ግን የወረደውን ሰላም አስመልክቶ ሲሰደቡና ሲወገዙ የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ደጋመው በማመስገን ” ስራዎትን እግዚአብሄር ይባርክልዎ” ብለዋቸዋል። ከዛ በፊት ግን ” እውነት ለመናገር ዛሬ የተሰማኝ ልክ አቡነ መርቆሪዮስ ሲመጡ የተሰማኝ ዓነት ስሜት ነው …” ሲሉ እርቁን አግንነው አሳይተዋል።

ይህ በተባለና እርቃቸውን ሲያከናውኑ የተነጋገሩት ተሰምቶ ሳያልቅ፣ ዳግም ወደ ቀውስ መሄድ ራሳቸውን ከሚጎዳው በቀር ሌላ ውጤት እንደማያመጣ የሚገልጹ፣ ምዕመኑ ምን እንደሚያጣላቸውና ለምን መግባባት እንዳልቻሉ ከራሳቸው አንደበት ስለሰማ ” በተራ የሰማእትነት መፈክር” ዳግም እንደማይጃጃል፣ ሳይውል ሳያድርም መፍትሄ እንደሚሰጥ፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲያልቅ መግለቻውም እንደሚያበቃ ጠቁመዋል።

Leave a Reply