አየር መንገድ በቱርክና ሶሪያ የሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ የሚደረገው ጥረት ተቀላቀለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ የሚደረገው ጥረት ተቀላቀለ፡፡

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውፕላኖች ከሜክሲኮ በአደጋው ተጎጂ ለሆኑ ቱርካውያን የተደረገውን 100 ቶን የሰብዓዊ እርዳታ እያጓጓዙ መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን ከ41 ሺህ በላይ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ በርካቶች ደግም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)

See also  ኬላዎች አካባቢ የሚታዩ ሕገ ወጥ ተግባራት ለእህል ዋጋ ጭማሪ ምክንያት ሆነዋል -ነጋዴዎች

Leave a Reply