“አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት!” ብልጽግና እስከመቼ ይሸከማል?


ወያኔ”ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፣ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እወርዳለሁ”ብሎ ጦርነት ሲያውጅ ጦርነቱ እኛን አይመከትም ያሉ የግብፅ፣ የአሜሪካ መሩ የምዕራባውያን፣ የወያኔ ቅጥረኞች አሁን ላይ ደግሞ በመንጋው ዘንድ የአማራ ዋና እና ትክክለኛ ጠበቃዎች ተደርገው ተቆጥረዋል(አንዳች ለውጥ ሳያሳዩ)

ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ነፍጥ በማንሳት ጦርነት ገጥመው ልካቸውን ማወቅ የሚገባቸው “አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት!” አቀንቃኞች ሳይደመሩ በብልፅግና ውስጥ ሆነው የመቀጠል ብቻ ሳይሆን እንደፈለጉ የመሆን ዕድል በማግኘታቸው፣ከውስጥ ሆነው ከወያኔ ያልተናነሰ ግጭት እየጠመቁ የአማራን የኦሮሞን የሌላውንም ሕዝብ ማህበራዊ እረፍት በመንሳት ኢትዮጵያን እያደሙ በተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ደግሞ እነሱ እንደጀግና የተደመሩት ሐገሬን ያሉት ደግሞ እንደባንዳ እንደከሃዲ እንደሆዳም እንዲቆጠሩ አድርጓል።

እነዚህ አካላት የአማራ ብልፅግናን ብአዴን አስመስለው በመሳደብ እንደአማራ ተቆርቋሪ ራሳቸውን ከመቁጠር ባሻገር የዋህ አማራዎችንም እንደዛው ጥሩን ብለው ይጠራሉ።

የአማራ ብልፅግናን ብአዴን እያሉ ሲሳደቡ ለብዙ የዋህ አማራዎች የሚመስላቸው ብአዴንን እንደሚጠሉ ከብአዴን የተሻለ ለአማራ ሕዝብ የሚያስቡና የሚታገሉ አድርገው ነው። እውነታው ግን በተቃራኒው ብአዴንን ለመሆንና ራሱን ብአዴንን ዳግም ለመመለስ ነው።

ብልፅግና ሲፈጠር ብአዴንን እንደሕወሓት ወደብልፅግና እንዳይዋሃድ ሞክረው ነገር ግን ከፍ ያለ የተፅዕኖ ድምፅ ስላልነበራቸው በመደመር የተሸነፉ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት ላይ ቆመው የቀሩ አፍቃሬ ወያኔዎችና የእነሱ ቅጥረኛ አክቲቪስቶች ናቸው አሁን ላይ የአማራ ብልፅግናን(በተለመደው በመንጋው ቋንቋ ለማውራት ነው እንጅ የአማራ የሚባል ቅርንጫፍ ካልሆነ ፓርቲ የለም) በከፍተኛ ዘመቻ እንዳንሰድብህ እንዳናጣጥልህ ከፈለክ በብልፅግና ላይ ተነስ አመፅ ምራ የሚሉት።

እስኪ እንግዲህ በብልፅግና ውስጥ ሆነው “አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት!”እያሉ ሳይደመሩ ግጭት እየጠመቁ የተደመሩ ብልፅግናዎችን ደግሞ ስም እያጠፉ እስከመቼ ዕድል ተሰጥቷቸው አብረው እንደሚቀጥሉ እኛም አብረን የምናየው ይሆናል።

በነገራችን ላይ ከለውጡ በፊት ለአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅምና መብት መከበር ለኢትዮጵያ ሐገረ መንግስት መፅናት እታገላለሁ ብሎ የጠራ አላማ የነበረው እውነተኛ የኢህአዴግ ተቃዋሚ(ኢህአዴግ ተቃዋሚ ያስመሰላቸው ተቃዋሚዎችም ስላሉ ነው)የሆነ አንድ አማራ የኢህአዴግ ግንባር ፈርሶ ብልፅግና ሲፈጠር ተቃውሞ የማሰማት ዕድሉ ጠባብ ነው። ብልፅግና የእሱ የትግሉ የጥረቱ ውጤት ነውና እንደ ድል የሚቆጥሩት እንጅ በማይረባ ጉዳይ ሁሉ እንደኢህአዴግ የሚቆጥሩትና አምርረው የሚቃወሙትና የሚታገሉት አይደለም። ይህንማ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይሞ ሞት ያሉት ወያኔና የግብር ልጆቹ የትግል መስመር ነው!!

See also  "በአራት አቅጣጫ የገባው የጠላት ሀይል መክኗል"


ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ነፍጥ በማንሳት ጦርነት ገጥመው ልካቸውን ማወቅ የሚገባቸው “አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት!” አቀንቃኞች ሳይደመሩ በብልፅግና ውስጥ ሆነው የመቀጠል ብቻ ሳይሆን እንደፈለጉ የመሆን ዕድል በማግኘታቸው፣ከውስጥ ሆነው ከወያኔ ያልተናነሰ ግጭት እየጠመቁ የአማራን የኦሮሞን የሌላውንም ሕዝብ ማህበራዊ እረፍት በመንሳት ኢትዮጵያን እያደሙ በተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ደግሞ እነሱ እንደጀግና የተደመሩት ሐገሬን ያሉት ደግሞ እንደባንዳ እንደከሃዲ እንደሆዳም እንዲቆጠሩ አድርጓል።

አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት ላይ ተቸንክረው የቆሙ በብልፅግና ውስጥ ሳይደመሩ ከቀጠሉ ሰዎች በላይ ለአማራም ሆነ ለኦሮሞ በጥቅሉ ለኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነት ስጋት የሚሆኑ የጥፋት መልዕክተኞች የለም!

Thomas Jejaw Molla – ቶማስ ጀጃው ሞላ

Leave a Reply