አጋቹ ተያዘ

አጋች ሁኔ ደጀን በማዕከላዊ ጎንደር የታች አርማጭሆ ወረዳ ያይራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን አቶ ፈጠነ ሸቴን አግቶ 100 ሽህ ብር ተቀብሎ ሊሰወር ሲል የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል ።

የሆነው እንዲህ ነው አጋች ሁኔ ደጀን ነዋሪነቱ ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ደንብ ከተማ ሲሆን ታጋች ፈጠነ ደጀንን በታች አርማጭሆ ወረዳ ያይራ ቀበሌ ድረስ በመጓዝ ልጁን አግቶ ወደ ጫካ ገብቶ በድርድር ላይ ሳለ የታጋች ቤተሰቦች የአጋች መኖርያ ወደሆነው ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት በማመልከታቸው የወረዳው የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ከታጋች ቤተሰብ የተቀበለውን ብር በሻንጣ እንደቋጠረ ወደ መኖርያ ቀበሌው ተመልሶ በተደበቀበት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ወረዳው ይህን ብሏል በርካታ አጋች ግለሰቦችን በመከታተል ለህግ አቅርበን አስቀጥተናል ለወደፊትም አንድም ግለሰብ በእገታ ወንጀል ተደራድሮ ብር እንዲከፍል ፍቃደኛ አይደለንም ለዚህ ትግላችን ማህበረሰቡ ከጎናችን በመቆም መረጃ በመስጠት ሊተባበረን ይገባል።

አርማጭሆ ወረዳ

See also  ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን ቤላሩስ ውስጥ ልታጠምድ ነው

Leave a Reply