አተራምሱና ማማ ላይ … አይ አሜሪካ

አሁን አሁን ሊለይልን ወይም ቢለይልን ብሎ መመኘት የተሻለ ሆኗል። ገሽበናል። ወርደናል። አክለፍልፎናል። የማሰቢያ አንጎላችን ደርቋል። የማንም ደንቆሮ የሚነዳው፣ የሚጋልበው፣ የሚወቅረው፣ የሚጠልዘው፣ የሚያበራየው፣ የሚደፋበት፣ የ… ሆነናል። ቆርቆሮ እንደሚጮኸው ሁሉ ለጮሁ ሁሉ የጆሯችን በር ተበርግዷል… ያሳዝናል!! ዘጠና ሰባት በመቶዎች። እድሜ ለነጋ ልጅ በር ዘግቶ ፈትኖ የ27 ዓመት ምርት ምን እንደሚመስል አሳይቶናል። ከማፈር ይልቅ ወደ …

ምንድን ነው የሆነው? ምን ነክቶን ነው? ማጣራት፣ መጠየቅ፣ ማሰብ … አቆምን። ማንም ተነስቶ የሚሾፍረን … ቢያንስ “የዚህ ሁሉ ነውጥና አመጽ ባለቤት ማን ነው?” ብሎ መጠየቅ አይስፈልግም? ” ከነውጡ በሁዋላስ ማን እንዴት ያረጋጋናል” ተብሎ እንዴት አይታሰብም? ምን መሆን ነው ያማረን? ያበደው እንባውን አቀረረ። አንገቱን ሰብሮ ሽቅብ አየ? በልቡ ምስኪን ወገኖቹን ሰላም አላቸው። በቡድን ሙገሳ፣ በደቦ ጥላቻን የሚያከፋፍሉትን ” የራሳቸው ጉዳይ” አላቸው።

“ከመረጠን” ይላል ልክ ዘውደኞቹ ከሱ ሰፈረ የፈለቁ ይመስል፣ ከነ ጨጎጊቱ ወግ እየተጋተ!! ይህ የ ” ጭር ሲል አልወደም” ደራሲና አመጽ አምራች፣ ረብሻ፣ ሁካታ ስር የማይጠፋ፣ በፈላበት ሁሉ የሚገኝ የስምዖን ተረፈ ምርት… ይቅር … ቦሰና ሲብስባት ነው ይህን ያለችው። ቦሰና ሰው እንዴት ሁሉም ዓይነት ረብሻና ሁካታ ይመቸዋል? እንዴት ነውጥ በተባሉ የሴራ ቁማሮች ውስጥ “እቺም ቀይ፣ እቺም ጥቁር ይጫወታል?” የሚል ጥያቄ አላት። ” ይህ ሲሆን ጠርጥር፣ ከመጠርጠርም እለፍ” ትላለች። ወዲያው ደንግጣ “አንቱ” ስትል የተከበሩ የፓርላማ ተመራጭ …..

ፓርላማ መመረጥ ድሮ ክብር ነበር፤ እንደራሴነት ድሮ ወግና ማዕረግ ነበር፤ ከፊፉ ትህነግ የሚባል ተምች መጣና የመሸታ ቤት ወንበር አደረገው ” “ለዓላማችን ሟች ከሆነ ዘበኛም ቢሆን” ሲሉ ሊቀ ትጉሃን፣ ሊቀ ሊቃውንት ዘ ትህነግ ወልደ ዜናዊ መለስ ከነፍስ ይማር ማዕረጋቸው ጋር እንደተናገሩት። ቦሰና “ስምህን..” ብላ ተረቱን ትጨርሳለች ስሙ ሲነሳ። ያንገፈግፋታል።

“ምን አለሽ ተራ፣ ምን አለ ዛሬ” ነው የዘንድሮ ነገር። ድሮ የጣልከውን ጣሳ ድንገት ታገኘዋለህ። ምን አለሽ ተራ አዲስ ነገር የተወገዘበት፣ የነተበ፣ የተነደለ፣ የተቀደደ፣ የቀመለ፣ የተቦጫጨቀ… እቃና ጨርቅ የሚገበይበት.. “ምን አለ ዛሬ?” አሉት… በምን አለሽ ተራ ይቅርታ ምን አለ ዛሬ … ቦሰና ካስጀመረችው ያበደው ያጮሃል። ትንኮሳዋ የአናት እምብርትን ስለሚያጦዝ … ይፈላበታል።

ቦሰና “ሽልማቱን ሰማህ” ብላ የሽሙጧን ስታስነካው ደጎል ው ው ው ው ብሎ ዘሎ ወጣ። ደጎል “ውሻ ይሉሃል” ትላለች ስታቆላምጠው። ያበደው የደጎልና የቦሰና መናበበ ገብቶታል። “ጀግና ሴት” ተብላ የመሸለም ሚስጢሩ ዛሬ ተገልጦላታል። ያብደው ሲያብድ ሁለቱ መላ ነድፈዋል። ደጎል ቦሰናን ዋይት ሃውስ ውስጥ ጀግና ድርጎ ለማሾም ቆርጧል። ለውሾች ቃል ኪዳን ታላቅ ነው።

See also  ሱዳን - በጫጉላ ሰረገላ - "ሳምሪዬ ሳምሩ" አዲሱ ዘፈን ለትህነግ

ደጎል ቦሰናን መጀመሪያ ” የአንድነት ሃይል አድርገሽ ራስሽን ሰይሚ” ሲል ይጀምራል። ቀጥሎ “ከርሳም ሁኚ” ያላታል። ምክሩ ለውጭ አካላት አሳብና ዓላማ በሚጠቅም መልኩ የተሰላ ስለሆነ ” ኢትዮጵያ የሚል ቅባት ተቅቢና ብሄርተኛነት ተጫሚ” ብሎ የሆነ ነገር ትዝ አለውና በውሽኛ አሽካካ። ከዛ በሁዋላ ” ጦርነቱ የኢትዮጵያ ህዝብን … የኛን ብሄር አይመለከትም” ብላ ዕለት ዕለት እንድትጮህ አሳሰበ። ” በድንብ መራገምን አትርሺ” ሲል አሳሰበ። ይህ ካልሆነ ተከታይ አይኖርም። ሼርና ላይክ አይገኝም። …… ብዙ መክሮ ዘለለና

“ባስቸኳይ ዩቲዩብ ለቦሰና” መፈክሩን ይዞ ወጣ። “ትርምስ ለኢትዮጵያ የቻናሉ ስም ነው። ለማተራመስ የቆረጡ ስፖንሰር አይቸገሩም”። ደጎል ድምጹን እያሰማ ከተማውን ዞረ። ያበደው መፈክሩን ቀየረ ” ሁለት ኪሎ ጥሬ ስጋ ለቦሰና” የሚል መፈክር ይዞ ወጣ … ያበደው ረጋ ሲል ተገለጠለት። “ጥሬ ስጋ ቁረጡ፣ አገር የሚያተራምስ ዘር ተኮር ቻናል ላይ ቀስቅሱ። የወቅቱ ኪሎ መስፈርት ስላልሆነ በድፍረት ጩሁ” ሲል የደጎልን ጩከት ጮክ ብሎ አሰማ ። ሰዶማዊያንና አተራማሾችን አሜሪካ ታነግሳቸዋለ። ቦሰና አሜሪካን አሜሪካ አትላትም ” ወራዶች” እንጂ!!

የመጀመሪያው ቀን ፕሮግራም ተለቀቀ። “ትርምስ ለኢትዮጵያ” ቻናል በደቂቃዎች ውስጥ እንደ ነፋስ ሁሉ ሰው ደጅ ደረሰ። “ታላቅ የአመጽ ጥሪ” የሚል ርዕስ ነበረበት ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይኮበልሉ ህዝብ ቤተመንግስቱን ይክበብ” የሚል ተከታይ ርዕስ አለው። ስዕሉ አብይ አህመድ አብርሆትን ነቅለው ይዘው ሊኮበልሉ ሲሟሟቱ፣ ሚሽታቸው ጎንደር ዳቦ ቤት ስታስመርቅ ያስያል። ዳቦ ቤት ማስገንባት ሃጢያት በሆነባት ኢትዮጵያ ዝናሽን ቦሰና እንደ ደብተራ ወረደችባቸው፤ አድማቂው “ማን ናት ይህቺ ጀግና” አለ። ላይኩና ሼሩ እንደ ጉድ ተዥጎደጎደ። ቦሰና ፕሮግራሙን ጨርሳ እንደ ብልጣ ብልጦቹ ” ላይክና ሼር ማድረግ አትርሱ፤ የዕለቱን መዋጮም …” ሳትል በሱፐር ቻት አሞቁላት። ተደራራቢ ቪዲዮ ለቀቀች። ገነነች። አሁን ደጎል አንድ ጉዳይ ታወሰው ” መታሰር አለብሽ” አለ። ድሮ ኢሃዴግ እያሰረ ያጀግን ነበር። አሁን ብዙም አይደለም። ቢሆንም ደጎል ተሳክቶለት ቦሰና ታሰረች። ደጋፊዎቿ ” የኢትዮጵያ ቀንዲል፣ የኢትዮጵያ ዓይን፣ የጀግና ማማ፣ የጋዜጠኞች ጥግ፣ የዘመኑ ጣይቱ፣ የድፍረት ተምሳሌት … ” እያሉ መንግስትን ሰደቡላት። ያበደው ይህ ሁሉ ሲሆን ይስቃል። በሚስቱ ጀግንነት ይላጣል። ጀግና ሴቶች!! ለዚያውም የዓለም!!

See also  [አብይና ትግሬ ታረቁ - አብረው አማራን ሊያጠቁ] የአንገት በላይ ቁምጥና

ከዓመት በሁዋላ ቦሰና ” ጀግና ሴት” ተብላ ነጩ ቤት ገባች። ማህበራዊ ሚዲያው አበባ ተራጨ። የምስጋናና የማጀገኛ ቃል ጠፋ። የበረከት ልጅም ፓርላማ ሆነው “እሰይ እህቴ” አሉዋት። ነጩ ቤት ከጎኗ እንደተለመደው ሰዶማዊያን ” ጀግና ሴት” ተብለው ከጎኗ ተኮልኩለው ቆሙ። ደጎል ቀስ ብሎ ጎተታት። “እነዚህ ሴቶች ናቸው እንዴ” አለ። ሰውነታቸው፣ ደረታቸው፣ አፍንጫቸው፣ መዳፋቸው … ሁሉም ሰፋፊ ነው። ” ይቅርብሽ” ሲል ደጎል በጆሮዋ አንዳች ሹክ አላት … ቦሰና እንደመብረቅ ሳቀች። አድናቂዎቿን አስባ ተንተከተከች። ከዛም “ወራዶች ….” ብላ ጮኸች። “ገዲቲ” ብላ ገሬርሳዋን አቀለጠችው። ስትነቃ … !!

ጎበዝ ከሽልማቶች ጀርባ ብቃት፣ ጥራት፣ እውቀት፣ …. ምን ይሸታል? ወደሁዋላ መለስ ብሎ ተሸላሚዎችን መመርመር የሽታውን ጥራት፣ የዋጋውን ብዛት ለማስላት ይበጃል። ዓለም የማትሸልማቸውን ደግሞ ብልጽግና ይሸልማል። ብልጽግና መረጃ በወጉ ያሰራጩልኛል ብሎ የሰንበት ልጆችና የማይፋፋ ድርጅት ይቀልባል። ያብደው ያየውን ተነተነ። በብልጽግና ውስጥ ብልግና ገንግኖ አይቶታል። “ለካ ይህን መናገር ዋጋ ያስከፍላል” ብሎ ተወው። ግን የህዝብ ገንዘብ እንደ አሸን በብጫቂ ወረቀት ይፈሳል። መረጃ ቢስ ዝርፊያ፣ ያብደው ዕድሜ ተመኘ ፤ ከውጭ በሚፈስላቸውና የአገር ውስጥ ሌቦች በሚበጅቱት ሌሎቹ ከዛም ከዚህም አገሪቱን ያልሟታ። ይህ ነው ተያያዞ መውደቅ … ወይ ከብልጽግና ወይ ከነ እንቶኔ ሳንሆን … አናሳዝንም ወይ? ” የማያስተውሉ ይገለበጣሉ!!

ጎሃጺዮን ላይ ጎጃሜ መታወቂያ ስለተጠየቀ ጎጃም ጤፍ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ አደመ አሉ። “የተከበሩ” የሚባሉት ሰውዬ ይህንኑ አመጽ እንደ ታላቅ ድል አስተጋቡት። እኚህ በረከት ወልውሎ የሰራቸው የእጁ ውጤት ምነው ግን ረብሻ ባለበት ሁሉ ዘው ይላሉ? ጥያቄ ነው። ያበደው “አዲስ አበባ አንዴ ይቆለፍብሻል። አንዴ ጤፍ ትከለከያለሽ። ነገ ደግሞ ምን ይገጥምሽ ይሆን?” ሲል አሰበ። የኦሮሞ ብሄርተኞች አዲስ አበባን አሳሯን አብልተዋት ነበር። አሁንም ጠፉ ማለት አይቻልም። እዚህ ላይ ግን ያበደው ያሳስባል። መንግስትና ህዝብ ተለይቶ የማይታይበት ብሽቅ ፖለቲካ!! ይቁም!! ለነገሩ 97 ከመቶዎች ሲበዙ ምን ይጠበቃል? ለመሆኑ አዲስ አበባ ዙሪያን በባጃጅ ያንበሸበሸው ማን ይሆን? ስራ ፈጥራ ወይስ … የሸማኔ ዘፈን …

የልዩነት ዘር ሴራ፣ የዕግት ሴራ፣ የማፈናቀልና አፈናቃዮችን የማስታጠቅ ሴራ … የቤተክርስቲያን ሴራ …. አሁን ደግሞ የጤፍ ፖለቲካ፤ ያበደው ዛሬ ለሰላምታ ጊዜ የለውም። ጎጃሜ ጤፉን በባንክ ብድር በሰበሰበው ገንዘብ የሚገዛው ካገኘ እዛው በዶላርም ይሽጠው። ይህን አመጽ ሰምቶ ጤፍ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ያደመው ነገ ሌሎች ለሚያድሙበት አድማ ከወዲሁ ይዘጋጅ። ለሁሉም አስንድ እውነት አለ። ህዝብና ብልጽግና ይለያያሉ !! በስልጣን ወላፈንና በሳይበር ንግድ የናወዛችሁ ጥገቡ!!

See also  የጠፈር ሽርሽር በረራ ሊጀመር ነው

ውድ ኢትዮጵያዊያን ልብ በሉ፣ አዲስ አበባ ጤፍ እንዳይገባላት ማሳደም ማንን ለይቶ ለመጉዳት ነው? ያበደው ጠየቀ፣ መልሶ ሳቀ፣ አብይ አህመድን መጥላትና መታገል ሰላማዊ ሰዎችን ከማስራብ ጋር ምን ያገናኘዋል? ጣና እየተጠመቀ ያለው ፖለቲካ ግራ ነው። ሻለቃ ዳዊት የሚባለው የሲአይኤ ሽንት ያስበላቸው ምርጥ የኢትዮጵያ ጀነራሎች ደም፣ ከረሃብተኞች ዘርፎ የኮበለለው ሳያንሰው “የጎጃም ድንበር ወለጋ ነው” ብሎ ያሳለፈውን ጥሪ ሰምቶ ጨርቁን የጣለ ብዙ ነው። እዛ ሰፈር የሚሆነው ሁሉ … ቡሬ፣ አንገር፣ … ቤት ይቁጠረው …

የስርዓትም የአመራርም ለውጥ መፈለግ፣ መሪ ለመሆን መመኘት አያጣላም። ግን ለምን በትርምስ? አራት ዓመት ህዝብ አለቀ፣ ተፈናቀለ፣ ተዘርፈ፣ ታፈነ፣ ምን ያልሆነው ነገር አለ? አራት ዓመት ለመደራጀት ብዙ ነው። የሚወጣውን ወይም እንዲወጣ የሚፈለገውን ህዝብ ያውቃል። የሚገባው ማን ነው? አገር በጨረባና በጨበጣ ማንነቱ በማይታወቅ አተራማሽ እንድትመራ መፍቀድ እንዴት ይሆናል? ያበደው ተቆጣ። ቦሰናም ” እነማን ናቸው? መሪያቸውስ ማን ነው?” ትላለች። እውነት ነው አሮጌውን ለመጣል አዲሱ ቀድሞ መገዛት አለበት። አሳብ ሽጡልን። ዕቅድ አምጡ። ስትራቴጂ አቅርቡ። መሪዎቻእሁን ከጠራ መርሃ ግብር ጋር አሳዩን። የሚዲያ ችግር የለባችሁምና ስድቡን፣ እንካ ሰላንቲያውን አቁሙና የራሳችሁን አውሩን…

መልካም ሴቶች አሉ። የሴት ጉልላቶች አሉ። ጀዝመኛ ሴቶች ብዙ ናቸው። የነብር አራስ የሆኑ ምርጥ እናቶች ነበሩ ዛሬም አሉ። ያበደው ዘለለ። የቦሰና ትክክለኛ ጀግንነት ታወሰው። አሁን ወደቤቱ መሮጥ አለበት። መንገዱ ሁሉ ያዳልጣል። ካልተጠነቀቁ መቀጨት አለ። ሶስት በመቶዎቹ ወደ አመራር እስኪመጡ በ97 ከመቶዎቹ የመለስ ጫጩቶች መነዳት ግድ ነው። ያበደው ግን ይህ አይመለከተውም አሁን ቦሰና ጋር ደርሷል። ገባ። አቴቴ እንዳለባት ባልቴት ጅርግግ ያለ ፈትል ለብሳለች። ምልክቱ ቀላል ነው። ንቢቱም ነበረች። አብረን አዋህድነው። ገና ሳይመሽ ሞቀን። ደጎል ተሽክርምሞ እየተንጎራደደ ላሽ አለ። እኛም ላሽ አልን። ሞተር አስነሳን … ባቡሩ ባቡሩ ባቡሩ … ሸከተፍ ሸከተፍ ሸከተፍ … ፌርማታውን … ሰላም ሁኑ። ኢዜማ የጎታችና ገፊ” የመናበብ ፖለቲካ አልጋ ላይ እንጂ አገር ላይ መጫወት አደጋው የከፋ እንደሆነ ገብቶታል። ሳይውል ሳያድር .. ተግባብተናል። ወራጅ አለ!!

Leave a Reply