ኢዜማ ከዕብደት ለመውጣት ኢትዮጵያን ለሚያስቀድሙ ሁሉ የትግል ጥሪ አቀረበ፣ “መንግስት ውስጥህን አጥራ”

ሁላችንንም በስሜት ነድቶ የተዘጋጀልን ወጥመድ ውስጥ ገብተን አቅል የሳተ የእብደት መንገድ እንድንከተል ግፊት ለመፍጠር እየተሞከረ መሆኑንን የኢዜማ መግለጫ ያሰምረበታል። አክሎም “…ያለውን ጫና በአትኩሮት ልንመለከተው ይገባል፤ መንግሥትም በጉያው አቅፎ እዚህ ያደረሳቸው በሃሰት ትርክት የተሞሉ፣ በጥላቻ የሰከሩ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብ እንኳን ግልጽና የጠራ መዳረሻ ያላስቀመጡ አክራሪ ኃይሎችን በግልጽ ሊፋለማቸውና፣ ከመዋቅሩ ሊመነጥራቸው ይገባል ” ይላል።

ፓርቲው ያውጣው መግለጫ “ማን ነው የዚህ ሁሉ ትርምስና ሁከት ባለቤት” በሚል በርካቶች እየጠየቁ ባለበት ሰዓት መሆኑ መግለጫውንና ጥሪው ካልዘገየ በስተቀር አገራቸውን የሚወዱ ሁሉ ሊሳተፉበት የሚገባ፣ መንግስትም ቁርጥ አቋም እንዲይዝ የሚያደርግ እንደሆነ ከወዲሁ አስተያየት ተሰጥቷል።

  • ፓርቲዉ ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎቻችን ማስመር እንዲቻል ብሔራዊ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የጥናት ግብረ ኃይል እንዲቋቋም፣ ግኝቱንም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርብ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ሁላችንንም በስሜት ነድቶ የተዘጋጀልን ወጥመድ ውስጥ ገብተን አቅል የሳተ የእብደት መንገድ እንድንከተል ግፊት ለመፍጠር እየተሞከረ ያለውን ጫና በአትኩሮት ልንመለከተው ይገባል፤ መንግሥትም በጉያው አቅፎ እዚህ ያደረሳቸው በሃሰት ትርክት የተሞሉ፣ በጥላቻ የሰከሩ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብ እንኳን ግልጽና የጠራ መዳረሻ ያላስቀመጡ አክራሪ ኃይሎችን በግልጽ ሊፋለማቸውና፣ ከመዋቅሩ ሊመነጥራቸው ይገባል ሲል ኢዜማ አስገንዝቧል ፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል

የተደቀነውን የሀገር ህልውና አደጋ በቅጡ እንረዳለን፤ ጊዜውን የዋጀ አመራር ለመስጠትም ቁርጠኛ ነን! በሚል ርእስ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የለውጡ መንግሥት ከመጣ በኋላ ያለፉትን አምስት ዓመታት ያሳለፍነው አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ የሆነ ጉዞ በፅንፈኛ ብሔርተኝነት እየተገፋ ዛሬ ለደረስንበት ጠርዝ አብቅቶናል ብሏል።

በየቀኑ በሚፈጠሩ ውጥንቅጦች እና የሚፈለፈሉ አጀንዳዎች ማህበረሰባችንን የሥነልቦና ጫና ውስጥ ገብተናል ያለው ኢዜማ ፓርቲው የደረስንበት አሳፋሪ ሃገራዊ ዕውነታዎች ከሥር መሠረታቸው እንዲቀየሩ የመፍትሔ አካል መሆን እንዳለበትና ሀገራችን ወደ ቀና መንገድ እንድታመራ ከፊት ተሰልፎ አመራር መስጠት እንዳለበት እናምናለን ሲል ገልጿል።

ኢዜማ በመግለጫው በተለይ በሰሜኑ የተከሰተው ጦርነት እንዲቋጭ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ማግስት ጀምሮ ሀገሪቷን የሚንጡ አጀንዳዎችን በመፈልፈል ዜጎችን እረፍት የሚነሱ ተግባራት ላይ የተጠመዱ በመንግሥት ውስጥና ከመንግሥት ውጪ ያሉ ፅንፈኛ ብሄርተኞች ተናበው እየሰሩ መሆኑንና በዘር ፖለቲካ የሰከሩ ሰዎችን በመጋለብ መላው ህብረተሰብ በቁጣ እንዲወጣና አጠቃላይ ሃገራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ያለእረፍት እየሰሩ እንደሚገኙአስታውቋል።


ኢትዮጵያን እያመሳት ያለው የ”ገፊና ጎታች ሤራ” ሲገለጥ

ይህ ሁሉ የገፊና ጎታች ሤራ ዋና የትኩረት ማዕከል የሚያደርገው በሥልጣን ላይ ያለውን መሪ ነው፤ ለግቡ መዳረሻ ተጠንቅቆ ዝንፍ ሳይል የሚተገብረው መርህ ደግሞ እረኛውን ምታ መንጎቹ ይበተናሉ የሚለው። ይህ በመናበብ የሚከወን ድራማ


ሁላችንንም በስሜት ነድቶ የተዘጋጀልን ወጥመድ ውስጥ ገብተን አቅል የሳተ የእብደት መንገድ እንድንከተል ግፊት ለመፍጠር እየተሞከረ ያለውን ጫና በአትኩሮት ልንመለከተው ይገባል፤ መንግሥትም በጉያው አቅፎ እዚህ ያደረሳቸው በሃሰት ትርክት የተሞሉ፣ በጥላቻ የሰከሩ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብ እንኳን ግልጽና የጠራ መዳረሻ ያላስቀመጡ አክራሪ ኃይሎችን በግልጽ ሊፋለማቸውና፣ ከመዋቅሩ ሊመነጥራቸው ይገባል ሲል ኢዜማ አስገንዝቧል ፡፡

ከመንግሥት መዋቅር ውጪ፣ በተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ አክቲቪስቶችና ባለሃብቶች ጭምር እየተቀጣጠለ ያለው የአክራሪ ብሄርተኝነት ጦስ ካሁን በኋላ እያስነከሰን እንዲቀጥል ሊፈቀድ አይገባም ያለው ኢኤማ መንግስትም ጉዳዩን መስመር ለማስያዝ እያሳየ ያለውን እንዝህላልነት ለፅንፈኛ ብሔርተኞቹ የልብ ልብ እየሰጠ ድርጊታቸው ሁሉ መስመር እያለፈ ህዝቡ አድዋን የመሰሉ ብሔራዊ በዓላትን እንኳ በሚፈልገው መንገድ ማክበር እንዳይችል አድርጎታል፡፡ በዚህም መታለፍ የሌለበት ቀይ መስመር በመታለፉም በቃ ልንል ይገባል ሲል አስታውቋል።

ኢዜማ የሚይዛቸው የፖለቲካ አቋሞች እና ትንታኔዎች መሰረት የሚያደርጉት የሰከነ አስተሳሰብን እንጂ ጊዜያዊ ድጋፍን ለማግኘት በሚል የህዝብ ብሶትን እያቀጣጠለ፣ ወቅታዊ ጩኸትን እንዲሁም ወጀቡን ተከትሎ በመንጎድ ሲመሰረት ጀምሮ ካስቀመጠው የጠራ የትግል ሥልት እና ግብ ወደጎን የሚወጣ ድርጅት እናዳለሆነና
በፍጥነት ተለዋዋጭ የሆነው የሃገራችንንም ሆነ የቀጠናውን ጂኦ ፖለቲካ በሀገራችን ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ እየተነተነ፣ ሁኔታው የሚፈልገውን አቋምና ውሳኔ በመረጃ ላይ ተመስርቶ ውሳኔዎች እያስቀመጠ እና የትግል ስልቱንና የዓላማ መዳረሻውን እያጤነ የሚጓዝ ድርጅት መሆኑን በመጠቀስ
እንደሀገር የገባንበት ከፍተኛ አደጋ ከስሜታዊነት እና ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ፣ በወቅታዊ ክስተቶች ላይ ብቻ ተመስርተን ሳይሆን በዘላቂነት የሃገራችንን መፃዒ እድል እያሰቡ፣ ተከታታይነት ያላቸውን ማህበረሰቡን እረፍት የነሱ ክስተቶች በተናጠልና በድምርም በሃገራችን ላይ ጥለው የሚያልፉትን ጠባሳ እያሰቡ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

ለአባላት ለደጋፊዎች እና ለመላው ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት ፓርቲው ዋነኛው ቁም ነገር ሀገራችንን እየተፈታተኑ ያሉ ነባር ውስብስብ ችግሮችንም ሆነ አንገብጋቢ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ እያየን እንጂ በዝምታ እና በቸልታ ኃላፊነት እንደሌለበት ፓርቲ ሁኔታዎቹን ዳር ላይ ቆመን እየተመለከትን አደለም ሁኔታውን ተረድተን፣ ችግሩ እንዲቀረፍ የመሪነት ድርሻና ኃላፊነታችን መወጣት ታሪካዊ ግዴታና አደራ እንዳለብን ምንም አይነት ብዥታ የለንም ብሏል፡፡

ኢዜም “ኢትዮጵያዊነትን አስቀድመው ሰለ ሀገር አንድነት በፅኑ የምትታገሉ የብሔር ፖለቲካ ምን ውስጥ አንደከተተን ተገንዝባችሁ ከምንጊዜውም በላይ የሚከፋፍሉ አጀንዳዎችን እና ጥቃቅን ልዩነቶችን ከማጉላት በመቆጠብ አንድነትና ህብረት ላይ በማተኮር ከገባንበት አዘቅት ውስጥ መውጣት የሚያስችሉ የትብብር ስራዎች ላይ ማተኮር፤ ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታውን ልብ ብሎ በማስተዋል በአንድነት ስም የተሰባሰበው ሀይል ቆም ብሎ ቀድሞ ሲጓዝበት ከነበረው አፍራሽ መንገድ በመውጣት እርስ በእርስ ከመጓተትና ከመጠላለፍ በመራቅ ፅንፈኛ ብሔርተኝነትን በጋራ መታገል እንደሚያስፈለግ አምኖ በሰከነ መንገድ ለመተባበር ካሁን በኋላ የምናባክነው ተጨማሪ ጊዜ መኖር እንደሌለበት በዜግነት ፖለቲካ ለሚያምኑ ሁሉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን”፡፡ ብሏል።

ኢዜማ ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ መፍትሄው እኩልነት ላይ የቆመ የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት መሆኑን በጽኑ እንደማመኑ፣ ይህን የሚጋሩ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ እንደዚሁም ይህንን የምትጋሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጎናችን እንድትሰለፉ አደራ እንላለን፡፡ብሏል በመልእክቱ።

ከዚህ በፊት እንደሆነው በጎንዬሽ መጓተት ጊዜ የምናጠፋ ከሆነ አያት ቅድም-አያቶቻችን ዋጋ ከፍለው ያቆዩዋትን ሀገር ዓይናችን እያየ ብሄርተኞች ያፈርሷታል፡፡ እኛም ይህ እንዳይሆን ቢያንስ በሚያግባቡን መሰረታዊ የሀገር ህልውና ጉዳዬች ላይ አብሮ ለመስራት እና ኢትዮጵያችንን ለማዳን በጋራ በመቆም ህዝባችንን ለመምራት ባለመተባበር ከሃገር አፍራሽ ብሄርተኞች እኩል በታሪክ የምንጠየቅ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

ኢዜማ ሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ በሥፋት ለማጥናት፣ በተጨማሪም እንደሀገር እየሄድንበት ያለውን የፖለቲካ አካሄድ እና በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ያሉ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታን ቆም ብሎ በመገምገም ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎቻችንን ማስመር እንዲቻል ብሔራዊ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የጥናት ግብረ ኃይል እንዲቋቋም፣ ግኝቱንም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርብ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
ብሔራዊ የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ

Leave a Reply