ብሊንከን “በግጭቱ የተሳተፈ” ያሉት የኤርትራ ጦር መውጣቱን አረጋገጡ፤ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ተፈቀደ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ.ብሊንከንን አዲስ አበባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተገኝተው ከኢትዮጵያ መሪ አብይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ከተነጋገሩ በሁዋላ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ስምምነት መደረሱ ተመለክተ። አሜሪካ የ331 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓንና ታግዶ የነበረውም የአጎዋ በር እንደሚከፈት ተመለከተ። ለሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ ስኬት አሜሪካ አስፈላጊውን ትብብር እንደምታደርግ በይፋ አመልክተዋ። የኤርትራ ሰራዊት ለቆ መውጣቱን እንዳረጋገጡ ተናገሩ

በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉን በርካታ የዓለም መገናኛዎች ዘገቡ። በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ራሳቸውን የዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን መሪ ያደረጉና በዚሁ ስም ድርጅት የመሰረቱ ባስፈራሩ በቀናት ዕድሜ ውስጥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ማደሷን በፊትለፊት ማስታወቋ ዜናውን ትልቅ አድርጎታል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ራሳቸው አንቶኒ ብሊንከን ጨምሮ በመንግሥትና ሕወሓት መካከል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በየግላቸው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን ጠቅሶ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው አሜሪካ ከረጀም ዓመታት በፊት የነበረው የሁለቱ አገራት ወዳጅነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱን የተከታተሉት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፤ በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ፍሬያማ ምክክር ማደረጉን ነው ያስታወቁ። በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካካል በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የረዥም ዓመታት አጋርነት ለማጠናከር የሚሰሩ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ በኢትዮጵያ አዲስ የመረጋጋትና የሰላም ምዕራፍ መከፈቱን ለአንቶኒ ብሊንከን ማብራራታቸውን አምባሳደር መለስ ገልጸዋል። ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት በማከናወን ሂደት መንግሥት በቁርጠኝነት በመሥራት ላይ መሆኑንም ዋቢ መረጃ በማስቀመጥ አስረድተዋል።

የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን ለማሳለጥ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት የአሜሪካ መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መጠየቃቸውን ቃል-አቀባዩ አልሸሸጉም። የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው የሰላም ትግበራ ሂደቱ በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ የበለጠ እንዲጠናከር የአሜሪካ መንግሥት ሁለገብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ለአንቶኒ ብሊንከን ማብራሪያ መስጠታቸውን አምባሳደር መለስ አለም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት ጋር በመተባበር በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን፣ የሶማሌላንድ ችግር እንዲፈታ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ተመሳሳይ ጥረቶችን እያደረገች መሆኗን ተናግረዋል። በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ለአብነት አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተም ሁሉንም አካላት አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ የሚደረገውን ጥረትን አብራርተውላቸዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እያደረገች ያለውን ጥረት አሜሪካ በአድናቆት እንደምትመለከተውና የሚበረታታ መሆኑን መግለጻቸውንም አምባሳደር መለስ አክለዋል። ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የሚመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኗ የሚያስመሰግናት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ሰክሬታሪ) አንቶኒ ብሊንከን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውሽጥ በሰጡት መግለጫ ከህወሓት አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተው መምከራቸውን ገለጹ። አንቶኒ ብሊንከን የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለመፍታት የሠላም ስምምነት ለፈረሙት ሁለቱም ወገኖች እውቅና ሰጥተዋል። በግጭቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እየወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሰላም ስምምነቱ ተጠናክሮ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ የገበያ እድል ዳግም መመለስ የምትችልበት እድል እንደሚኖርም ገልጸዋል። በተጨማሪም በሂደት ላይ ላለው የሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ አሜሪካ አስፈላጊውን እርዳታ እንደምታደርግም ተናግረዋል።

አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውል የ331 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስታውቀዋል።ድጋፉ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በኩል እንደሚደረግ መግለጻቸውን ጎልጉል አመልክቷ።

በግጭቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እየወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

ብሊንከን በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ የገበያ እድል ዳግም እንደምትመለስ ቀን ባይቆርጡም በይፋ አመልክተዋል። መንግስት እያዘጋጀና እያሰራበት ላለው የሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍና እርዳታ እንደምታደርግ በይፋ አስታውቀዋል። በግጭቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ለቆ መውጣቱን አመልክተዋሎኦ

መንግስት ሲወቀሰና ማዕቀብ ሲጎርፍበት የነበረው ከኤርትራ ጦር ጋር በተያያዘ በመሆኑ ብሊንከን የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንደወጣ ማስታወቃቸው ኢትዮጵያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የአገዋን ነጻ የገበያ እድልና የተባበሩት መንግስታት የሰባዊ መብት ኮሚሽን ጣልቃ ገብነትን እንደሚያስወግድ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ገልጸዋል። ዜናው ፕሬዚዳን ኢሳያስን እንደማያሰደስትና አመልክተዋል።

Leave a Reply