አብይ አህመድ “የኦሮሞ መንግስት” ለሚሉ “ሰብሰብ በሉና ሃሳብ ይዛችሁ ኑ” 1.7 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ተከፍለ

በዛሬው የፓርላማ ውሎ ላይ አብይ አሕመድ ከሁሉም አቅጣጫ የሚጮሁ ያሉዋቸውን በሙሉ ከአገርና ከውጭ ተሰባስበው አሳብ በመያዝ ለውድድር ቢያስቡበት እንደሚሻል አስታወቁ፤ በነውጥና በጩኸት የሚገኝ ነገር እንደሌለና በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የድህንነት ችግር ከውስጥም ከውጭም ስጋት እንደሌለ ተናገሩ።

በውጭ የተደራጁና አንዳንድ በውጭ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ሰሞኑንን በግልጽ በፓርላማ አብይ አህመድ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጥያቄ እንዲቀርብላቸው ሲጎተጉቱ ነበር። የ360 አባል ኤርሚያስ ለገሰ “ዛሬ አቶ ክርስቲያን በፓርላማ የስልጣን ልቀቁ ጥያቄ በማቅርባቸው አመሰግናቸዋለሁ ሲሉ” መደመጣቸው የመናበብ ስትራቴጂውን ያሳየ ሆኖ ተወስዷል።

የተረጂዎችን ገንዘብ ዘርፈው ከአገር እንደኮበለሉ ቢቢሲ በማስረጃ ያጋለጣቸው ሻለቃ ዳዊት የሚመሩት ሃይል የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ደጋግሞ ሲጠይቅ እንደነበር ይታወሳል። ሻለቃው “የጎጃም ድንበር ወለጋ ነው” በሚል በገሃድ መናገራቸውና ትግላቸውም ከዚያው አካባቢ ስሩን እንደተከለ ማስታውቃቸው አይዘነጋም። “አማራ የሰውነት ልክ” እንደሆነ በአደባባይ ሲናገሩ የነበሩት አቶ ክርስቲያን “ኦሮሞን አልተናገርኩም” በሚል ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠይቁ ራሳቸውን የሽግግር መንግስት ከሚጠይቁት አካል መድበው ይሁን በግል ተነሳስተው በውል የታወቀ ነገር የለም። አስተያየት የሰጡ እንዳሉት “ድርጅት ሳይኖር ይህ ጥያቄ አይቅርብም”

“በአስራ ስድሰተኛው ክፍለ ዘመን ጋላ ኢትዮጵያን ወሯል” ሲሉ በአደባባይ የኦርሞን ህዝብ የተሳደቡትና ራሳቸውን የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ አድረገው የሚወስዱት ድርጅቶች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በሃይል እንደሚጥሉ ሰሞኑንን አስታውቀው ነበር። መግለጫም አሰራጭተዋል። ለዚህ ምላሽ ይሁን ለሌላ አብይ አህመድ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሃይል የሚወድቅ መንግስት እንደሌለ። ከቻሉ ይሞክሩት በሚል መልኩ መልስ ሰጥተዋል። እንዲያውም ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ አንዳችም የደህንነት ችግር እንደሌለባት፣ ከውጭም ሆነ ከውስጥ ስጋት ሆኖ የሚታይ ጉዳይም እንደሌለ አስታውቀዋል።

ከየክልሉ ካሉ ነፍጥ ያነሱ ድርጅቶች ጋር ሁሉ በሰላም ለመወያየት በፓርቲ ደረጃ በተላለፈ ውሳኔ ንግግር እየተደረገ እንደሆነ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እህል ለከዘኑ “አውጥተው ቢሸጡ ይሻላል” ሲሉ መክረዋል። ከተለየዩ ሚዲያዎች ከስር ያሉት ተሰባስበዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት ዉስጥ አንድ ዶላር ኮሜርሻል ብድር አልወሰድንም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

  • ነገር ግን ከብድሩ ላይ 1.7 ቢሊየን ዶላር ከፍለናል ነዉ ያሉት፡፡

የአገራችንን ኢኮኖሚ የሚገዳደሩ ብዙ ጉዳዮች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከዉስጥ ያለዉ እና ከአለም ገበያ የምናስገባዉ እራሱን የቻለ የዋጋ ንረት፣ ምርትና ፍላጎት ለማገናኘት ከባድ የሆነዉ የመሰረተ ልማት ክፍተት እና በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለዉ ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ኢኮኖሚያችንን የሚገዳደር ነዉ ብለዋል፡፡

አገራችን ላይ ባለዉ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ዜጎች ተጎጂ መሆናቸዉ ግልጽ ነዉ ያሉ ሲሆን፣ ለዚህም እንደምክንያት ለ 20 ዓመታት በተከታታይ ያደገዉ የኑሮ ዉድነት እና አለመግታት መቻላችን ችግሩን አባብሶታል ብለዋል፡፡

See also  አቢይ አሕመድ ብራሰልስ ገቡ፤ ከአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ

ሌላኛዉ ደግሞ የአምራችና የሸማች ፍላጎት አለመጣጣም ሲሆን ከዚህ ዉጪ ደግሞ ጦርነት እና ድርቅ ምክንያቶች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

በጦርነት እና ድርቁ ምክንያት ደግሞ ለአገራችን የሚሰጠዉ የብድር እና የድጋፍ ስራዉ መቀዛቀዙን ነዉ ያነሱት፡፡

ለዚህም መፍትሄ የሚሆነዉ አቅርቦት በተለይም ምርት ላይ መስራት መሆኑን ገልጸዉ መንግስት ከሚበጅተዉ በጀት ዉስጥ 59 በመቶዉን ለድህነት ቅነሳ ስለሚያዉል ይህንን በመጠቀም ሁኔታዎችን ማሻሻል ያስፈልጋል ነዉ ያሉት፡፡

በዚህ በ 2 ወይም 3 ወራት ዉስጥ የተከሰተዉ የዋጋ ንረት እንደሚባለዉ የከፋ አይደለም፣ አቅርቦቱን በመጨመር እና ሁኔታዎችን በማሻሻል የሚረጋጋ እንደሚሆን ተስፋ አለን ብለዋል፡፡

ከሸኔ ጋር ለመደራደር ተደጋጋሚ ሙከራ መደረጉ

የፌደራሉ መንግስት ከአሸበሪዉ “ኦነግ ሸኔ” ጋር ለመደራደር 10 ጊዜ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታዉቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነዉ፡፡ ከሸኔ ጋር ለሚደረገዉ ድረድርም መንግስት ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ሥራ እንደገባ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተደረገዉ ድርድር ሙከራ ያልተሳካዉ የሸኔ ኃይል የተበታተነ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡ መንግስት ከሸኔ ጋር ያለዉን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ ፍላጎት እንዳለዉም ተነስቷል፡፡

በቅርቡ የኦሮሚያ ከልል ለሸኔ ያቀረበዉ የእንደራደር ጥያቄ የክልሉ ዉሳኔ ሳይሆን የፌደራሉ መንግስት ዉሳኔ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማብራሪያቸዉ አንስተዋል፡፡

……

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተወካዮች ምክር ቤት ከመለሱት

ሰላምን በተመለከተ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዛሬ ስደስት ወር በፊት ከነበረው ዛሬ የተሻለ ሰላም አለ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቆም አንድ እርምጀ ወደፊት የወሰደ ነው፤ ወደ ተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ስራ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ተኩስ ሲቆም ወዲያውኑ የሰላም ዓየር አይነፍስም፤ ድህረ ግጭት የሚያሳድረው ቁስል ቶሎ የሚሽር አይደለም፤ የጦርነት ነጋሪትን አብዝተው የሚጎስሙ ዜጎች በመኖራቸውም የሰላም ዓየር መኖሩን ለማስብ ያስቸግራል ብለዋል፡፤

ኢትዮጵያ ውስጥ የመጠላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ ሲንጸባረቅ ቆይቷል ያሉጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የሚያስፈልገን ግን የሚያስፈልገን የሰላም፣ የይቅርታ መንገድ ነው ሲሉ መልሰዋል።

ሰላምን ማምጣት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን ያሉት ተቅላይ ሚንስትሩ፣ይሁን እንጂ ሰላምን ለማምጣት እንደ ጦርነት ጀግንነት ይፈልጋል፤ ሰላም ከጦርነት ባልተናነሰ ከፍተኛ ጥረት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ሰላም ከጦርነት ያልተናነሰ ትጋት እና ስራን ይፈልጋል፤በተለይም አወንታዊ ሰላም ብዙ ከእኛ ይቅር ከሰላም የምናተርፈው ይበልጣል ብሎ ማመንን ይጠይቃል ብለዋል በምላሻቸው።

ሚዲያን በተመለከተ

ሚዲያን ሰው መርጦ መስማት አለበት፤ ይህ ካልሆነ አላስፈላጊ ነገሮች ይተላለፋሉ፤ አድማጭ ሃላፊነት አለበት፤ ሚዲያ ስለሆነ ብቻ ማዳመጥ አስፈላጊ አይደለም።

See also  የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የዜጎችን ደኅንነት የማስከበር ተቀዳሚ ኀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪ አቀረበ፡፡

የሚዲያ ነጻነት እስከምን ድረስ ነው? የሚዲያ ነጻነት ዜጎችን እስከ ማጫረስ መድረስ የለበትም፤ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን በሚያስራጩበት ጊዜ ሃላፊነት ሊወስዱ እና ሊሰማቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ

“ሰላምን በተመለከተ ከዛሬ ስድስት ወር የተሻለ ሁኔታ አለ።

ወደተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል።

ነገር ግን አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደ ሥራ ተሠርቷል። ጦርነት እንደቆመ ወዲያውኑ ሰላም አይሰፍንም ድኅረ ጦርነት አውድ ጫና አለ።

ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ፖለቲካ የመተላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ ነበር።

ሰላም አስፈላጊ ነው ብለን በጽኑ እናምናለን። ሰላም እንደጦርነት ጀግንነት ይፈልጋል።

ከጦርነት ያልተናነሰ ሥራ ድካም ይጠይቃል። የረጋ ሰለማዊ ነገር እንዲሁ አይመጣም አዎንታዊ ሰላም በሀይል አይመጣም። ምንግዜም ሰላም ሲባል የአንድ ሰው ህይወት ማትረፍም ስለሆነ በዚህ ላይ መሥራት ይገባናል። ” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትሩ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

  • ከድህረ ጦርነቱ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ሰላምን ለማስፈን ጊዜ ይፈልጋል
  • የተሟላ ሰላም ለማምጣት በትብብር መስራት ያስፈልጋል
  • የሰላም አየር በተሟላ መልኩ ለማስፈን ጦርነት ጎሳሚዎች የሚፈጥሩት ችግር እንቅፋት ሆኗል
  • በአሁኑ ጊዜ ገዳዩ ሰይፍ ሳይሆን የሰላም፣ የፍቅርና የይቅርታ ሰይፍ ነው የሚያስፈልገን
  • ሰላምን ለማስፈን በይቅርባይነት እና በአዎንታዊነት ደግፈነው በጋራ እውን ለማድረግ በትብብር ልንሰራ ይገባል
  • አዎንታዊ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የምክክር፣ የትብብር ተቀራርቦ የመስራት ጅምሮች አሉ፣ ተጠናክሮ ይቀጥላል
  • የሰሜኑ ጦርነት በሠላማዊ መንገድ የተደረሰው ስምምነት ወጤታማ ነው
  • የሰራ ፖለቲከኞች ሰላም እንዳይፈጠር ይሰራሉ፤ በጉልበት ፖለቲካ የሚያምኑ ሰላም እንዳይፈጠር ይሠራሉ
  • ለሠለም ምክክረ ውይይት ለመግባባት ብዙ መድረኮች ተፈጥረዋል የሚሉ ነጥቦችን አነስተዋል፡፡

ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ መንገደኞች

የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ወደ ከተማዋ በሚገቡ ዜጎች ላይ ፍተሻዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነዉ፡፡ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ይህም በተደራጀ መልኩ ጭምር የሚደረግ ነዉ ብለዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች ከየትኛዉ አካባቢ በስፋት ወደ ከተመዋ እንደሚገቡ ያልገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤አበል እየተከፈላቸዉ ጭምር ከተመዋን ለመበጥበት የሚሰሩ አካላት መኖራቸዉን አንስተዋል፡፡

በተለይም የአደባባይ በዓላት ሲኖሩ ከፍተኛ የሰዉ ቁጥር ወደ ከተመዋ እንደሚገባ መንግስት መረጃ አለዉ ነዉ ያሉት፡፡ በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማን ሠላም ለማስጠበቅ ሲባል አጥፊዎችንና ሰላማዊ ዜጎችን ለመለየት ፍተሻዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የከተመዋ ነዋሪዎችም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር የአዲስ አበባን ሰላም እንዲያስጠብቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

See also  አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅጥፈት መግለጫ አወጣ፤ ቡድኑንን እየበጠበጠ ነው

የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ

 የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የተጀመሩና እየተተገበሩ የሚገኙ መፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ማተኮርና የምርት አቅርቦት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያጋጠመው ንረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እየጎዳ መሆኑን በጽኑ እንገነዘባለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩ ላለፉት 20 ዓመታት የማያቋርጥ የዋጋ ንረት በመፈጠሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ሸማች እና አምራች መካከል ያለውን ክፍተት ማስተካከል አልተቻለም፤ ጦርነት፣ ድርቅ፣ የአጋር አካላት እርዳታ መቀነስ እና ወደ ከተማ ፍልሰት መጨመር ዋና ዋና የዋጋ ንረት ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡

ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ማጋጠሙን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን ለመፍታት በርካታ የግብርና ምርቶች እንዲገቡ እየተደረገ እንደሆነና የዋጋ ንረት የተፈጠረውም የምርት እጥረት ኖሮ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

በዘህም በምርት ዙሪያ ባስጠናነው ጥናት ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት እስከ 1 ሺሕ ኩንታል ምርት ቤታቸው ያስቀመጡ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

ስንዴ ከታሰበው በላይ መመረቱንና በቂ ምርት መኖሩን ገልጸው የኢትዮጵያ አርሶ አደር ሚዛናዊ የግብይት ስርዓት መከተል ይገባል፤ ምርት በማከማቸት የከተማው ነዋሪ እንዲቸገር ማድረግ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

ድንበርን አስመልክቶ

 በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ግጭት በዘላቂነት ሊፈታ የሚችለው የሁለቱ አገራትን ድንበር መሬት ላይ የማካለል ስራ ሲሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር በሰላማዊ መንገድ ጉዳዩን ለመፍታት የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ተቋቁሞ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱም አገራት በኩል ግለሰቦች እና አርሶ አደሮች መጉላላት እንዳይገጥማቸው በሚል በጋራ ስምምነት ያለ ቢሆንም በአፈጻጸም ደረጃ የታዩ ስህተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ በዘላቂነት ሊፈታ የሚችለው ግን በንግግር እና በውይይት ብቻ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ከምክር ቤቱ አባላት ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ስለመፈፀሟ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ ”ደቡብ ሱዳን የሰው አገር ለመውረር የሚያስችል ፍላጎት የላትም፤ በወረራ መንገድ ባይቆጠር ጥሩ ነው” ብለዋል፡፡

ነገር ግን በደቡብ ሱዳን ድርቅ በመከሰቱ ምክንያት አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸውን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን እና መንግስትም ጉዳዩን እንደሚያውቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8፣ ከዋልታና ከግል የተውጣጣ ዘገባ ነው።

Leave a Reply