ገበታ ለሃገር ወሎ ሎጎ ሀይቅ

ሎጎ ሐይቅ ከደሴ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዛችሁ ሐይቅ ስላለባት ሐይቅ በሚለው ስም የምትጠራውን ከተማ ታገኛላችሁ፡፡ ሎጎ ሐይቅ- የተፈጥሮ በረከት ያደላት ባለ 3 አሳ ዝርያዎች ሀይቅ ነች። ቀረሶ፣ ዱቤና አምባዛ አሳዎች አሉ፡፡

ሎጎ ሀይቅ ከባህር ወለል በላይ 1950 ሜትር ከፍታ ላይ ያረፈ 35 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡ አማካይ ጥልቀቱ 23 ሜትር ይደርሳል፡፡ ሎጎ ሐይቅ በስሜናዊ ምዕራብ ክፍሉ ሙሉ ለሙሉ ከየብስ ጋር የተገናኘ ባህረ ገብ ምድር አለው፡፡ ይህ ምድር ቀደም ሲል ሙሉ በሙሉ ደሴት ነበር ይላሉ የተሁለደሬ አባቶቻችን፤ የሚያምረውን ተፈጥሮ ያክል የገዳሙም ታሪክ ገናና ነው፡፡ ሐይቅ እስጢፋኖስ በአጼ ድልናኦድ ዘመነ መንግስት የተመሰረተ እንደሆነ ይነገራል።

ይበልጥ የገነነው በ13ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት አባ ኢየሱስ ሞአ ወደ ገዳምነት ከቀየሩት በኋላ ነው፡፡ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም በመንፈሳዊ የትምህርትና ምርምር ማእከልነቱ ይታወቃል፡፡ ያሳለፈውን ገናና ዘመን በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ጊቢ የሚገኘው ሙዚየም ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ የሐይቅ ሙዚየም በርካታ የብራና መጻህፍት፣ ገድሎች፣ ከእንጨትና ከድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ልዩ ልዩ ቅርሶች ይገኙበታል፡፡ ይሄ ሀይቅ በመንግስ የገበታ ለሀገር ሊለማ መሆኑን ሰምተናል።ደስ ይላል። አርዲቦ ሀይቅም እንዳይዘነጋ እናሳስባለን። ከቴሌግራም የተገኘ

See also  በአማራ ሕዝብ ዝክረ ታሪክ ማዕከል ውስጥ ቅሬታ ይነሳበት የነበረው ኃውልት በአዲስ ተሰርቶ ተመረቀ

Leave a Reply