ኢትዮጵያ በሕንድ የከባድ መሳሪያ አውደ ረዕይ ላይ ተሳተፈች

ኢትዮጵያ ዛሬ ምዕራባዊ ሕንድ ፑኔ ውስጥ በተከፈተው የከባድ ጦር መሣሪያ አውደ ርእይ ላይ ከተሳተፉ 31 የአፍሪቃ አገሮች መካከል አንዷ መሆኗን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP)ዘገበ።

የተለያዩ ሃገራት ጦር ሠራዊት አዛዦች እና መኮንኖች በተገኙበት የከባድ ጦር መሣሪያ አውደ ርእይ ላይ ሕንድ በሀገሯ ያመረተቻቸውን ሔሊኮፕተሮች፤ ሰው አልባ ጢያራዎች (ድሮኖች) እንዲሁም መድፎችን ለዕይታ አቅርባለች።የዛሬው የከባድ ጦር መሣሪያ አውደ ርእይ በሕንድ የተከናወነው ከ23 የአፍሪቃ ሃገራት የተውጣጡ 124 ወታደሮች የዘጠኝ ቀናት «የአፍሪቃ-ሕንድ የመስክ ሥልጠና ልምምድ» (AFINDEX -2023) በሚል የጦር ልምምድ ካደረጉ በኋላ ነው።

ስብስቡ የኢትዮጵያ፤ ግብጽ፤ ኬንያ፤ ሞሮኮ፤ ናይጄሪያ፤ ርዋንዳ እና ደቡብ አፍሪቃ ልዑካናትንም ያካተተ ነበር ሲል የዜና ምንጩ ዘግቧል።20 የአፍሪቃ ሃገራት የተሳተፉበት መሰል ልምምድ ከአራት ዓመት በፊትም ሕንድ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካሂዶ እንደነበረም ተዘግቧል።ጦር መሣሪያዎችን አምርታ ዋነኛ ሻጭ ወደ መሆን የተሻገረችው ሕንድ ከአፍሪቃ ደምበኞቿ ግብጽ፤ ኢትዮጵያ፤ ኬንያ፤ ሞሮኮ፤ ናይጄሪያ፤ ርዋንዳ እና ደቡብ አፍሪቃ መሆናቸውን የዜና ምንጩ አክሎ ዘግቧል።

የሕንድ መከላከያ አምራች ማኅበር ኃላፊ ኤስ ፒ ሹክላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፦ የአፍሪቃ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ማግባቢያ ርእይ ብረት ለበስ ከባድ ተሽከርካሪዎች፤ ራዳሮች፤ የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁሶችንም ያካተተ እንደነበር ተናግረዋል።ሕንድ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን በመሸጥ የምታገኘውን ገቢ አሁን ካለው የ1,7 ቢሊዮን ዶላር ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ማቀዷም ተገልጧል።

ጀርመን ድምጽ

See also  "ወያኔ አማራ በመኾናችን ከ40 በላይ ሰዎችን በድብደባና በእስራት አካላችንን አጉድሏል" የጠለምት ነዋሪዎች

Leave a Reply