የትህነግ ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ክስ ተቋረጠ

በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሃት ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጡ ተሰማ። መደበኛ ክሱ ቢቋረጥም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በተቋቋመው የሽግግር ፍትህ ማእቀፍ እንዲታይ ስምምነት ላይ በመደረሱ ነው። ይህ ዜና ይፋ ከመሆኑ በፊት አቶ ጌታቸው ይህ እንዲፈጸም ንግግር እየተደረገ መሆኑንን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጡን ያስታወቀው የፍትህ ሚኒስቴር እንደሆነ የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች በማህበራዊ ገጾቻቸው አመልክተዋል።

በፌዴራል መንግስትና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሓት/ መካከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነትን በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱን ፍትህ ሚኒስቴር ጨምሮ ገልጿል።

በዚህ መሰረትም በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሃት ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ በማቋረጥ ጉዳያቸው በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንዲታይ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ስለዚህም በተገለፀው አግባብ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት ክሳቸው ተነስቷል።

See also  ማንነት ሲማሰል - " ... መስማማት ውዴታ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው"

Leave a Reply