የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ ተገደሉ

የነቀምቴ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ። ዜናውን ” በምዕራብ ኦሮሚያ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የነቀምቴ ከተማ የገዢው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ” ሲል የአስተዳደሩን የፌስ ቡክ ገጽ ጠቅሶ ቢቢሲ ነው የዘገበው።

ግድያውን አስመልክቶ ቢቢሲ አማርኛ “ምንም እንኳን አማጺው ኃይል የእንቅስቃሴ አድማሱን ባለፉት በርካታ ወራት እየሰፋ መምጣቱ ቢነገርም እንዲህ ያለው ግድያ ስለመፈጸሙ በቅርቡ ተስምቶ አያውቅም ነበር” ሲል ታጣቂው ቡድን አጉልቶ አሳይቷል። ይሁን እንጂ መንግስት ከትህነግ ጋር ስምምነት ከተፈራረመ በሁዋላ የኦነግ ሰራዊት ምን ያህል ይዞታውን እንዳሰፋ አላብራራም። መንግስት ቀደም ባሉ መንግስታት ተነክቶ የማውቀውን የኦነግ ይዞታዎች ጨምሮ በርካታ ወረዳዎች ነጻ መውጣታቸውንና ይፈረሰ አስተዳደርን መልሶ እያቋቋመ መሆኑንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች መዘገባቸው የሚታወስ ነው።

የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ በታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት የተገደሉት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21/2015 ዓ.ም. ነው። “ለሥራ ከቤታቸው ሲወጡ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሉ” በማለት ስለ አሟሟታቸው አስተዳደሩ በፌስቡክ ገጹ ላይ የሐዘን መግለጫ ያስረዳል።

የ33 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ደሳለኝ ላይ ግድያው ከቤታቸው ደጃፍ መሆኑ መገደላቸውን ቢቢሲ ” ተነግሯል” ሲል አመልክቷል። ግድያው በታጣቂዎች ተፈጸመ ከመባሉ ውጭ በስም የተጠቀሰ ወገን የለም። መንግስት የሰላም ውይይት ጥሪ እንዳላቀረበት ኦነግ ባስታወቀ ማግስት ግድያው መፈጸሙ፣ ከዚህ በፊት አባቶርቤ የሚባለው የድርጅቱ የከተማ ክንፍ ከዚህ መሰል ተግባሩ ታቅቦ ከመቆየቱ ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ “ግድያውን ማን ፈጸመው” ለሚለው አመላካች ጉዳዮች መኖራቸው እየተገለጸ ነው። አጋጣሚዎችንና የውቅቱን ሁኔታ በማገናዘብ ከተሰጠው ውጪ ገሃድ ወጥቶ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

በኢትዮጵያ አመጽ ሲጠራ፣ ሰዎች ሲታፈኑ፣ ተመሳሳይ ግድያ በፖለቲካ አመራሮችና የአስተዳደር አካላት ላይ ሲፈጸም ሃላፊነት የሚወስድና ምክንያት የሚያቀርብ ድርጅት አለመኖሩ ህዝብን ግራ እያጋባ እንደሆነ አሁን አሁን በስፋት እየተገለጸ ነው።

“ህዝቡን ማህበራዊ እረፍት መንሳት” በሚል ሴራ ላለፉት አራት አመታት የሚፈጸሙ የደቦና የተናጠል ወንጀሎች እስከመቼ ብህቡዕ እንደሚቀጥል፣ ዓላማው ምን እንደሆነና ምን ሲሆን ሊቆም እንደሚችል ገሃድ የሚናገር አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን፣ “እነዚህ እነማን ናቸው” የሚለው ጥያቄ ከግድያውና ሁከቱ በላይ ገኖ እየወጣ ያለ ዜና ነው።

See also  የአለማችን ግዙፉ የሩሲያ ኒዩክለር ተሸካሚ ሚሳኤል ምን ተአምር የማሳየት አቅም ያለው ይመስላችኋል ?

በቅርቡ ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ በመላው አገሪቱ በተለይም አዲስ አበባን ለማተራመስ ሲሰራ የነበረው ፕሮፓጋንዳ ባለቤቱም ማን እንደሆነ፣ ረብሻው እንደታሰበው ተሳክቶ ህዝብ ቢያልቅ ማን ሃላፊነት እንደሚወስድ በማይታወቅበት፣ ይህንኑ ሁከትና ነውጥ የሚያራግቡትን አካላትና የዩቲዩብ አምደኞች ዝም ብሎ ከማዳመጥ በዘለለ “ማን ነው ከጀርባ ያለው? ለውጥ ቢመጣ ማን ነው ተረካቢው? ምንስ ነው በቀጣይ የሚፈጸመው? ህዝብ ምን ይጠቀማል? የተዘጋጁት መሪዎችስ እንደማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አለመቅረቡና ምላሽ እንዲሰጥ የሚደረግ ጥረት አለመኖሩ ህዝብን ስጋት ላይ እንደጣለው፣ ከዛም አልፎ መሰላቸቱን የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

መወለጋና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተመሳሳይ ግድያ መፈጸሙ ከመሰማቱ ውጪ በገሃድ ሃላፊነት የሚወስድ አካል እስካሁን አልቀረበም።

Leave a Reply