Site icon ETHIOREVIEW

“ልዩ ኃይሎችን መልሶ ማደራጀት ትጥቅን ከማስፈታት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም”

ሚኒስትር ዳኤታ

የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ የማደራጀት ስራ በሁሉም ክልሎች መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት በመግለጫ እንዳስታወቁት ልዩ ኃይሎችን መልሶ የማደራጀት ስራ በሁሉም ክልሎች ተጀምሯል። ልዩ ኃይሎችን መልሶ ማደራጀት ትጥቅን ከማስፈታት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ብለዋል።

መንግስት ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ባለፉት አመታት በጥናት ላይ ተመርኩዞ ሲሰራ ቆይቷል። አንዱ ጥናትም የክልል ልዩ ሃይሎችን መልሶ በማደራጀት የመከላከያ ሰራዊትን እንዲያጠናክሩ ማድረግ ነው። የክልል ልዩ ሃይሎች አገር ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት መስዋእትነት ከፍለዋል፣ መንግስት ለዚህ እውቅና ይሰጣል ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት መቀላቀል፣ የክልሎችን ፖሊስ መቀላቀልና ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ምርጫ አላቸው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ የልዩ ሃይል አባላት በምጫቸው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።

የልዩ ሃይሎችን የማደራጀት ስራ መንግስት በከፍተኛ ጥንቃቄ እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ የማደራጀት ስራው ከትጥቅ ማስፈታት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ስለዚህ ህዝቡ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን መጠበቅ አለበት። መከላከያ ሰራዊት በጥንቃቄ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከህወሓት ጋር በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው ስምምነትም አሰራሩን በመከተል እየተሰራ ነው። የኦነግን ሸኔ አባላት በተመልከተም የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉት ወደማከላት እየገቡ ነው። የሰላም አማራጮች ሙሉ ለሙሉ ክፍት አድርጐ እየሰራ ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታዋ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ለማንኛውም ታጥቆ ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች የመንግስት የሰላም ጥሪ በሩ ክፍት መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ብለዋል።

በሸኔ ጉዳይ በርካታ በሽብር ቡድኑ ስር የነበሩ ቦታዎች ነፃ ወጥተው መደበኛ እንቅስቃዎችን ለማስጀመር ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በተዘረጋው የሰላም ጥሪም በርካታ የቡድኑ አባላት ወደ ሰላሙ እየመጡ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ መንግሥት በዚህ ዙሪያ ለሚሠሩ ምስጋና እያቀረበ አሁንም ለሸኔ እና በሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙ ኀይሎች ሁሉ ለሰላም በሩ ክፍት ነው ብለዋል ።

ሰላም እና ደኅንነትን ለማረጋገጥ መንግሥት የቀበሌ መዋቅሮችን በማጠናከር ያምናል እናም አቅማቸውን የመገንባት ሥራ እየተተገበረ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡ ለምሳሌ 635 ሺህ በላይ የሚሆኑ በኦሮሚያ አካባቢ በቀበሌ ለሚገኙ የፀጥታ እና የልማት መዋቅሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው ይሄ በሌሎች አካባቢዎችም እየተሠራበት መሆኑንን አመልክተዋል።

የህገወጥ ንግድ እና የንግድ አሻጥሮች ከሀገር የተሻገረ ዓለም አቀፍ ትስስር ያለው ነው እናም ይህን ለመከላከል ሥራዎች ሲሠሩ ነበር በዚህም በሕገወጥ መንገድ የማእድን ማውጣት እና ማምረት ሥራ ላይ የነበሩ በሁለት ክልሎች በቤንሻጉል ጉምዝ እና በጋንቤላ ክልል 92 የውጭ ሀገር ዜጎች እና 12 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል።

ይህ የሆነው ሰላም በመሆኑ እና መንግሥት ትኩረቱን ወደ ልማት ያዞረ በመሆኑ እንደኾነም ገልጸዋል፡፡ ግለሰቦቹንም በክትትል ከነኤግዚቢታቸው መያዝ ስለመቻሉም አስረድተዋል። በሥራው ላይ የሕዝቡ ርብርብ እና ተሳትፎ ሰፊ ነበር ያሉት ሚንስትር ዴኤታዋ አሁንም መንግሥት የሚሠራው ሥራ በሁሉም ክልል ያለ ተግባር በመሆኑ ኅብረተሰቡ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ በበልግ እርሻ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር የእርሻ መሬት በማረስ 24 ሚሊዬን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታሰቡን አስረድተዋል። ሌላው 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞ ከከረመው 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ጋር ለማስራጨት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል እስካሁን መሰራጨቱንም አስረድተዋል።

የበልግ ዝናቡን በአግባቡ ለመጠቀም ዝግጅት ማድረግ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የደረሱ ሰብሎች በዝናብ እንዳይበላሹ ርብርብ በማድረግ መሰብሰብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ዜናው ከአማራና ሚዲያና ኢፕድ የተወሰደ ነው

Exit mobile version