መስከረም አበራ ለምን ታሰረች? በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቅ የስልክ ምልልስ ይፋ ሆነባት፤

  • ነገሮች ባስቸኳይ መልካቸውን እይቀያየሩ ነው። ምናባታቸው እንደሆኑ አይታወቅም ትጥቅ ፈቱ፤ ባስቸኳይ ገንዘብ ያስፈልጋል

ራሱን አፈትላኪ leaked ብሎ የሚጠራ የማህበራዊ ሚዲያ በእስር ላይ ያለችውን መስከረም አበራ በይፋ በተቃውሞው ጎራ የፋኖ አሰባሳቢ ኮሚቴ ናቸው ከተባሉ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ጋር በስልክ ያደረጉትን ንግግር ይፋ ሆነባት።

መስከረም በስልክ ከተጠቀሱት ግለሰብ ጋር ያደረገችው ምልልስ የአማራ ልዩ ሃይል ውስጥ ስላላቸው አደረጃጀትና በቀጣይ ስላሰቡት ታላቅ አመጽ ነው። የገንዘብን አስፈላጊነት በማንሳት ባስቸኳስይ በስም ካልተጠቀሱ በውጭ ያሉ አካላት ብር እንዲልኩ ከነ አስፈላጊነቱ ሲነጋገሩ ነው የወጣው አፈትላኪ መረጃ የሚጠቁመው።

“እንዴት አባታቸው ዝም ብለው መሳሪያ ያወርዳሉ” በሚል በውልቃይት አካባቢ ሙሉ በሙሉ የመንግስት ሃይል ሁሉንም በሚፈልገው መልኩ ማከናወኑን በቅሬታ ሲገልጹላት መስከረም በመገረም ስትጠይቀና ስለቀጣዩ ስራ እቅድ ሲቀያየሩ የተለቀቀው ድምጽ ያስረዳል።

ድምጹ እንዴትና በማንኛው አካል ሊወጣ እንደቻለ ይፋ ባይሆንም ይህ እስከተጻፈ ድረስ ለማስተባበል የሞከረ ሃይል የለም። በአምራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ለታሰበው አድማ “We need money፣ ባለፈው ከሰጣችሁን ገንዘብ አሁን በላይ በጣም ያስፈልገናል” በማለት ዶ/ር ወንድወሰን ስማቸውን ላልጠቀሷቸው አካልት መስከረም ሃላፊነቱን ወስዳ እንድታስፈጽም ሲነገራትና እሷም ስትስማማ ተሰምቷል።

” በስልጣን ንገሪያቸው” በሚል ዶክተሩ ለመስከረም አበራ መመሪያ ሲሰጧትና “ጌታቸው” የሚል ስም በመጥራት እንድትደውልለት ሲነገራት፣ እንዳገኘችው ገልጻለች። ምልልሱን የሰሙ “ጌታቸው ማን ነው” በሚል ጥያቄ እያነሱ ነው።

የስልክ ነገገሩን መረጃውን ካሰራጨው አፈትላኪ ላይ በመውሰድ እንዳለ አትመነዋል። ያድምጡት።

በሌላ ዜና በአማራ ክልል የተከሰተውን ቀውስ በግንባር ቀደምትነት መርቷል የሚባለው የሰሜን ወሎ ፋኖ መሪ ምሬ ወዳጆ የባለወልድ አባቶችን ሽምግልና መላኩ ተሰምቷል። ምሬ ወዳጆ ከልዩ ኃይሉ እና ከህዝቡ ድጋፍ አገኛለው በሚል ወደ ግጭት ቢገባም ባሰበው ልክ ድጋፍ ማግኘት ባለመቻሉ ለመከላከያ ሰራዊት ሽምግልና መላኩን ከስፍራው መረጃ ያላቸው አመልክተዋል። በዚህ ሽምግልና የተሳትፉ የባለወልድ አባቶችም “ጦርነት በቃን፣ ከዚህ በላይ ጦርነት ውስጥ መቆየት አንፈልግም” ብለው ምሬን የገሰፁ መሆኑን እና መከላከያ ሰራዊትም ኢመደበኛ አደረጄጀቱ ትጥቁን ለመከላከያ ሰራዊት በማስረክብ በሰላም ወደየ ቤቱ እንዲገባ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ኢመደበኛ አደረጃጀቱ እንደተቀበለው ታውቋል። በዚህ መሰረት መከላከያ ሰራዊት ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታዎች፤

  1. ከዚህ በኋላ ምንም አይነት መንገድ እንዳይዘጋ፣
  2. ምንም አይነት የታጠቀ አካል ከተማ ውስጥ እንዳናገኝ እርቅም ይሁን ግጭት ከከተማ ውጭ ጫካ ላይ ይሁን፣
  3. አፈሙዝ ወደ መከላከያ ሰራዊት እንዳያዞሩ ሠራዊቱ የሚላቸውን ትዕዛዝ አክብረው ይቀመጡ፣
  4. የመከላከያን ጥቁር ክላሽ ሰብስበው ያስረክቡን በሚል ቅድመ ሁኔታ ካስቀመጠ በኋላ የሽምግልና ሂደቱን እንዲያስቀጥሉ ተስማምተው ከሽማግሌዎቹ ጋር ተለያይተዋል።
See also  አክሱም ነጻ ወጣች - ንግግሩ ሳይጀመር ነገሮች ወደ ድምዳሜ፤ አሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ መፍቀዷ አነጋጋሪ ሆኗል

ይህን ተከትሎ ምሬ ወዳጆ በሰጠው ምላሽ “ግጭቱ ሲፈጠር እኔ ምንም አላውቅም እንደ ቡድንም አልተወያየንበትም አልወሰንም ሁሉም የሆነው በዳንኤል አለሙ ትዕዛዝና ፍላጎት ነው” ሲል መናገሩና በተጨማሪም “ጫካ የገባነው ራሳችንን ለማዳንና መከላከያ እንደሚመታን ስናውቅ ነው የምንተኩሰው ጥይትም ሰው ላይ እንዲያርፍ አይደለም ለመከላከል ያክል ነው” ማለቱን ዜናውን የለጠፈው ገጽ አስታውቋል።

በመሆኑም የነ ምሬ ወዳጆ ቡድን በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቶ በሰላም ሊገባ እንደሚችል ተገልጿል። በተባለው መሰረት ግን እስካሁን ተፈጻሚ ስለመሆኑ አልተሰማም።

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ስለፎችና መንገድ የመዝጋትና አገልግሎት የማስተጓጎል አድማ ከጸጥታ ሃይል ጋር በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በተመሳሳይ የተዘጋ መንገድ ለማስከፈት ድንጋይ ሲያነሱ የነበሩ የመከላከያ አባላት መገደላቸው ይታወሳል።

Leave a Reply