የአማራ ክልል መዋቅር ውስጥ በጽንፍኞች የተጠለፉ ያዘጋጁት ዕቅድ ፈረሰ

ጽንፈኞች፣ በፋኖ ስም የተደራጁ፣ የተጠለፉ የአማራ ክልል የመዋቅር ሰዎች አንድ ላይ ሆነው ያቀዱት ክልሉን የማፍረስና የመቆጣጣር የመፈንቀለ መንግስት ይዘት ያለው እቅድ መምከኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ። የተጠቀሱት ሃይሎች የክልሉን መዋቅር ሽባ አድርገውት እንደነበርም አመለከቱ። “ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ሕዝብ ማንቃቱ አብቅቷል። አሁን ጊዜው የተገባር ነው” ሲሉ በቅርቡ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

የክልል ልዩ ሃይል መዋቅር ሙሉ በሙሉ መምከኑን ባስታወቁበት ንግግራቸው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እንዳስታወቁት ከሆነ ቃል በቃል ባይገልጹትም አማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ተወጥኖ እንደነበር የሚያመላክት መረጃ በግልጽ ሰጥተዋል

ኤታማዦር ሹሙ ህዝብን በማስቀየም፣ በአደባባይ በማዋረድና በመስደብ ድጋፍ ማግኘት እንደማይቻል ገልጸው ” እየሆነ ያለው ሁሉ እንዴት እስካሁን አብሮ ተኖረ” የሚል ግርምት እንደፈጠራባቸው አውስተዋል። በርካቶች ዙሪያውን ሲዞሩበት የነበረውን ጉዳይ በማፍረጥ በገሃድ ” የአገሪቱን የመሸረሽ ምሽግ መከላከያን በማዋረደ፣ ብሄር ብሄረሰቦችን በመስደብ፣ በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ሃይል በማደራጀት ስልጣን አይያዝም። ይህን እያየ አብሮ የሚሆንም አካል የሚገኝ አይመስለኝም” ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ዓይነቱ የትርምስ አካሄድ መንግስት መሆን እንደማይቻል ያስረዱት አዛዡ፣ አደዋን፣ የኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ተነስቶ የነበረውን አለመግባባና አሁን የልዩ ሃሎችን የማክሰሙና መልሶ የማደራጀት አጀንዳን በምሳሌ በማንሳት ሁሉም ውስጥ ጥልቅ እያሉ በመቀባበል ትርምስ የሚፈጥሩ ወገኖች እንደለመዱት የተሳሳተውን መረጃ በማሰራጨት ጉዳት ማድረሳቸውን አስታውቀዋል።

“ጉዳት ደርሷል። የተጠልፈው የክልሉ መዋቅር ለልዩ ሃይሉ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት እንዲበተን አደረጉት” ካሉ በሁዋላ ” የተበተነውን ሃይል ለጠብመንጃው ሲል በፋኖ ስም ራሱን የሚጠራ ሽፍታ ጨፈጨፋቸው” በማለት የጉዳቱን አስነዋሪነት አመልክተዋል።

ፋኖ በፋሽስት ወረራ ወቅት የተመሰረተ አገርን ከወረራ የታደገ ክብር ስም እንደሆነ አመልክተው፣ ይህን ክቡር ስም ተገን አድርገው ዛሬ ክልሉን እያተራመሱ ያሉ ሃይሎች መከላከያ ላይ እየተኮሱ እንደሆነ ገልጸዋል። ” አምኖ ያስጠጋን፣ የስታጠቀንና ወገን ያለ ሰራዊት ላይ የሚተኩስ የፋኖ ሃይል በምንም መስፈርት ህዝብ ሊደግፈው አይችልም” በማለት ምንም ይሁን ምን የታሰበው ከሽፎ የቃርሚያ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ገልጸዋል።

See also  “ አሸባሪው የህውሃት ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው -“

በጽንፈኞች ያልተጠለፉ አመራሮች በተሰማሩባቸው አካባቢዎች ሁሉ ልክ እንደ ሌሎች ክልሎች ስራው በሰላም መከናወኑን ገልጸዋል። የተበተነው የልዩ ሃይል አንድም ጥይት መከላከያ አለመተኮሱን በመግለጽ ሃይሉን ስርዓት ያለው እንደሆነ አመልክተዋል።

ሙሉውን ከዚዲዮው ያድምጡ

Leave a Reply