“360 የሚያዘጋጃቸው ዜናዎች ሰባ አምስት ከመቶ ሃሰትና ፈጠራ ናቸው”

360 የሚል ስያሜ ያለው የዩቲዩብ ልሳንና የመረጃ ቴሌቪዥን ተመጋጋቢ የተቃዋሚ ሚዲያ በየዕለቱ ከሚያቀርባቸው ዜናዎች ውስጥ ከሰባ አምስት በመቶ በላይ የሃሰትና የፈጠራ ውጤት መሆናቸው ተገለጸ። ሆን ተብለው የሚፈጠሩ ዜናዎች በ”ምን አለ ዛሬ” ከሚቀርበው በተለየ የዜና መልክ በማስያዝ የሚቀርቡት ዜናዎች ፍጹም እውሸት መሆናቸውን የገለጹት በጉዳዩ ዙሪያ ቅርብ እውቅና ያላቸው ናቸው።

“በቅርቡ በምሳሌና በማስረጃ ሰፊ ተከታታይ መረጃ አቀርባለሁ” ያሉት የመረጃው ባለቤት ከአምስት ዜናዎች ሶስቱ ሙሉ በሙሉ እውሸት እንደሆኑ ገልጸዋል። ይህ ተደጋጋሚ አሰራር እንዲታረም ሃሳብ ቢቀርብም ተሰሚነት ሊኖረው እንዳልቻለና ” ትግል ነው” የሚል ምላሽ እንደሚሰጥበትም አመልክተዋል።

“እዚህ ግባ የሚባል የዜና ክህሎትም በሌላቸው የሚሰራው የቅጥፈት ዜና እንዴት እንደሚሰራ በቅርብ ለሚያውቅ ያስደነግጣል” ሲሉ ያስታወቁት እኚሁ ሰው፣ 360 በዚህ ደረጃ ሆን ብሎ የሃሰት ዜና የሚያሰራጭበትን ምክንያትና ልዩ ፍላጎት፣ እንዲሁም ከጀርባ ያሉ ሃይሎች ዝርዝርም ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ሙሉ በሙሉ ሃሰት ከሆኑት ውጪ ቀሪዎቹ ደግሞ የተጋነኑ፣ ትንሽ እውነት ይዘው በሃስት የሚዋቡ፣ በሚፈለገው አውድ የሚቀኙና የሚሰሩ እንደሆነ አክለው የገለጹት እኚሁ የቅርብ ሰው፣ አሰረራሩ እንዲታረም በሚያውቋቸው በኩል ለመምከርና ሙያዊ ስነልቦና ያለው ሚዲያ እንዲሆን አሳብ መስተታቸውን አመልክተዋል።

See also  ኔቶ ከሩስያ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ እንደማይገባ ዐስታወቀ

Leave a Reply