ኢትዮጵያ አሜሪካ ችግር ሲያጋጥማት በተደጋጋሚ ድጋፍ ያደረገች እውነተኛ ወዳጅ ሀገር ናት ሲሉ “በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዥ ገለጹ፡፡
የአሜሪካ መንግስት በሱዳን የሚገኙ ዲፕሎማቶችን በማስወጣት ሒደት የኢትዮጵያን መንግስት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የአሜሪካ ጦር በሱዳን የሚገኙ የዋሽንግተን ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸውን ለማስወጣት ባካሄደው ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ቲቦር ናዥ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በሱዳን የሚገኙ ድፕሎማቶችን በማስወጣት ሒደት ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ኢትዮጵያ፥ አሜሪካ ችግር ሲያጋጥማት በተደጋጋሚ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ የምትታወቅ እውነተኛ ወዳጅ ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
በአሜሪካ ውስጥ በተፈፀመው የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ወቅት ኢትዮጵያ ለዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን እና አጋርነቷን አሳይታ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
- የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበር
- ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል