ከ125 ኮሌጆች የስኮላርሽፕ ጥያቄ የቀረበለት ተማሪ

በአሜሪካ የኒው ኦርሊያንስ ኢንተርናሽናል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ዴኒስ ባርነስ ከ125 ኮሌጆች በድምሩ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የስኮላርሽፕ ጥያቄ ቀርቦለታል።

ተማሪ ዴኒስ ባርነስ በበርካታ ኮሌጆች በመፈለግ ግንባር ቀደም የሆነ ሲሆን ፣ ከኮሌጆቹ የቀረበለት የ9 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ በጊነስ ቡክ እንዲመዘገብ አድርጎታል።

ትምህርት ቤቱ እንዳሳወቀው፣ የኒው ኦርሊያንስ ተወላጅ ተማሪው ለ200 ኮሌጆች የስኮላርሽፕ ጥያቄ ማቅረቡን እና በፈረንጆቹ ግንቦት 2 ምርጫውን እንደሚያሳውቅ ጠቁሟል።

ተማሪ ባርነስ ከዚህ ቀደም ለፋየት የተባለች የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ በ8.7 ሚሊየን ዶላር በጊነስ ቡክ ይዛ የነበረችውን ክብረወሰን አሻሽሏል።

ዴኒስ ባርነስ ያመጣው ውጤት 4.98 ሲሆን በአሜሪካ የክብር መዝገብ ውስጥ የመሪነት ቦታ ይዟል።

ተማሪው ስፓንሽ ቋንቋን አቀላጥፎ በመናገር እና የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ከስፔን ትምህርት ሚኒስቴር የላቀ ውጤት የክብር ሰርተፍኬት ማግኘት ችሏል።

በቀጣይ በአንዴ ሁለት የድግሪ ትምህርቶችን በኮምፒውተር ሳይንስ እና በወንጀል ፍትህ ለመማር ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።

ተማሪዎች ንቁ መሆን አለባቸው የሚለው ተማሪ ባርነስ፣ የስኬት መንገዶች ቀድሞ ማቀድ ፣ ከጓደኞች ጋር ትስስር መፍጠር እና ራዕይን ቀድሞ ማየት መሆናቸውን ገልጿል።

EBC

See also  በመንግስት የሚሰጡ መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የትግራይን ህዝብ ሳይሆን ወንጀለኛውን ህወሓት ብቻ ነው-- ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

Leave a Reply