ህያው ምስክሮችን [ቤተሰብ] እንመን ወይስ ሀብታሙ አያሌውን?

ሰባት ልጆች አባታቸውን ተነጥቀዋል። እናት ” ማጀቴ፣ ልጄ፣ ጓደኛዬ፣ አሽከሬ … ልጄን ተነጠኩ ፍረዱኝ፣ የኢትዮጵያ አምላክ ፍረደኝ…” እናት ሳግ እየያዛቸው የተናገሩት ነው። ጥይት የጎዳውን እጇን አቅፋ ባሏን እየዳኸች የተሰናበተችው ሚስት ስታገገም ምን እንደምትል ገና ይጠበቃል። ለምስክርነት የተረፉና እነሱን አግኝተው ስለመትረፋቸው የሰሙ ስለገዳዮቹ ማንነት መስክረዋል። ምንም ዓይነት ጥላቻና የግልም ይሁን የቡደን ፍላጎት ቢኖርም በዚህ መልኩ፣ ለታሪክ በሚቀር ማስረጃ ሃሰትን በድፍረት መናገር አሳፋሪ ነው።

ሃብታሙ አያሌውም የሚመራው 360 ከቅርብ ጊዜው ወዲህ በሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ መመራት ከጀመረ በሁዋላ፣ አብሮ ሊያኗኑር የማይችል ስብከት ላይ የማተኮሩ ውጤት የሆነው ይህ ግድያ ምስክር ነው። አቶ ግርማን ለጆሮ በሚቀፍና እጅግ ግምት ውስጥ በሚጥል መልኩ አጥንታቸው እየተቆጠረ የስብዕና ማጠልሸት ሲካሄድባቸው አንዱና ዋናው ተዋናይ ሃብታሙ አያሌው ነበር። ማናላቸው ስማቸውን እገዛ የሰጠበት ይህ አቶ ግርማን ለይቶ በማውጣት የባሩድ እራት እንዲሆኑ የተሰራው ስራ ታስቦበት ስለመሆኑ ጥርጥር የለኝም። ምክንያቱም ከግድያው በሁዋላ ይታይ የነበረው የእርካታ ስሜት፣ ግድያው ሲተነተንበት የነበረው ሁኔታና መረጃውን ከስፋራው እንደተገኘ ሲሰጥ የነበረው ምስክርነት ወዘተ ገላጮች ናቸው። ከዛም በላይ “ነብስ ይማር አንልም” በሚል በገሃድ ስምምነት ሲያደርጉ በዚያው በ360 መስኮታቸው ታይቷል። የማይካድ መረካም አለ።

ይህቺን አጭር አሳብ ለማካፈል ያነሳሳኝ ሸዋ ሮቢት ከባልደረቦቼ ጋር ሆኜ “አብይ አስገደለው” በሚል ሃብታሙ ለማስረዳት የሞከርበትን አግባብ ፊልሙን በስልኩ አውርዶ በያዘ ጓደናችን አማካይነት ከሰማን በሁዋላ ነው። እነሱ ቀደም ብለው አቶ ግርማ የሺጥላ እንዲወገድ፣ እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ መስል ባልደረቦቻቸውም ጭምር እንዲወገዱ ሲያስተባበሩና ሲያነቁ ስለነበር፣ አብይ አህመድ አስገደሉ የሚለው አግባብ

  • አብይ አሕመድ የእነ ሕብታሙ አያሌውን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ ሲሉ ነው ግድያ የሚፈጽሙት?
  • “አብይ አሕመድ በመደቡለት ጠባቂ ካልሆነ በሌሎች አይታጀብም” በሚልና በ360 በተደጋጋሚ “የአብይ ቀኝ እጅ” በማለት ውግዝ ከመአሪዮስ ሲቀርብባቸው በነበረው አቶ ግርማ ላይ መንግስት ስለምን እንደሚገድላቸው ለመረዳት የሃብታሙን ጭንቅላት መዋስ ካልተቻለ በስተቀር መረዳት አለመቻሉ
  • “በጥናትና በስልት የተፈጸመ” በሚል ሃብታሙም ሆነ ባልደረቦቹ በኩራት ስሜት ትንተና ሲያቀርቡበት የነበረው የግድያ ሂደት እንዴት አድናቆትንና በሌላ ማላከከን የሚያጣላ ድንቁርቁር ነገር መሆኑ
  • ከሁሉም በላይ በስም የተጠቀሱትና በድምጽ ይፋ በሆነው የስልክ ምልልሳቸው የቀረበውን ማስረጃ አምኖ የተቀበል፣ ( ማስተባበያ ቢኖረው ኖሮ ቀዳሚ ዜናቸው እሱ ይሆን ስለነበር ነው) በምን ስሌት ሃሜቱ ተቀባይነት ያገኛል?
See also  “ዳግም የሚዋረድ የወያኔ ቡድን እንጂ ሒሳብ የሚወራረድበት አንዳች የአማራ ህዝብ አይኖርም!”

እነዚህና መስለ አመክንዮ የተመላባቸውን ጉዳዮች በማንሳት ምርመራ ሲካሄድ ነገሩ ሁሉ የሆነ ክበብ ውስጥ እንዳለ የሚመስከሩ ሆነው ይገኛል። ሁሉም በሚባል ደረጃ የመርዶ መርማሪ “ጋዜጠኛ” ለመሆን “በደረሰኝ፣ ከስፍራው ባገኘሁት” እያሉ ከሚያላዝኑት በቀር ግድያውን አፍርጠው በማሳየት በኩል እኩል በሚባል ደረጃ አሳፋሪዎች ናቸው። የ360ን ለየት የሚያደርገው ራሱን ቀድሞም በሁዋላም ወደፊትም የጉዳዩ ወኪልና ባለቤት ያደረግ በመሆኑ ነው። ይህም ብቻ አይደለም አቶ ግርማን ብቻ ሳይሆን የስራ ባልደረቦቹንም በአጥንት ቆጠራ ያቀፈና የገፋውን መልሶ የሳበ በመሆኑ ነው።

በተቃዋሚና ደጋፊ ጎራ ስላለው የአመለካከት ልዩነት “ተፈጥሯዊ ነው” ከማለት ውጭ ምንም ማብራሪያ ማቅርብ ስለማይጠበቅብኝ አልፈዋለሁ። ግን ልዩነትን ማናቸውም አካላት በዚህ መልኩ ማድረጋቸው ስጋቱ አደገኛ በመሆኑ እቃወማለሁ። ሸዋ ሮቢት እንዲህ ባለው ልክፍት እንዳትያዝ እኔም ሆን ሌሎች አብረን እንሰራለን።

360ም ሆነ ባለቤቶቹ ምን ፍላጎት ኖራቸው እንደመሰረቱት የማይታወቀው መረጃ ቲቪ ቢቻል ከአጥንት ቆጠራና ከዘር አጥራ የሚባል ፉከራ እንዲወጡ እማጸናለሁ። አቶ በቀለ ገርባና ካዋር መሐመድ በግልጽ ህዝብ እየሰማ አጥንት ቆጥረው ምን እንደሆኑ ማስታወስም ይበጃል። ከሁሉም በላይ የዘር ፍጅት ማቆሚያ የሌለው ክፉ መጋኛ ስለሆነ ሃላፊነት መውሰድ ግድ ነው።

አቶ ግርማ ሰባት ልጆቹንና ሚስቱን እንዲሁም ቤተሰቦቹን በትኖ አልፏል። ልጆቹና ቤሰቦቹን 360ም ሆነ መረጃ ቲቪ ምንም ቢሉና ቢያደረጉ ሊታረቋቸው አይችሉም። ሰሜን ሸዋ ውስጥ ይህ ስሜት በቅርቡ እንደሚቀጣጠል ጥርጥር የለውም።

የአቶ ግርማ ባለቤት ሲሻላት ሁሉንም ትተርከዋለችና በጥፋት ላይ ጥፋት አትደምሩ። በክፋት ላይ ሌላ ክፋት አታባዙ። እንደሰማሁት ከሆነ ብዙ መረጃ ተሰብስቧል። ሰሞኑንን ይፋ መሆኑ አይቀርም። የዛኔ ህዝብ ይፈርዳል። ውሎ አድሮ ሁሉም ጉዳይ ይጠራል። የኢትዮጵያ ጉዳይ በዚህ አይቀጥልም።

ሃብታሙ ሚስትህ እንዴት አትመክርህም? አንተ አስከሬን መስለህ ፎቶ ለጥፈህ እርዳታ ስትለምን ዘር ቆጥረው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ቁስልህን ጠግነው፣ ኪስህን ሞልተው ሰው ያደረጉህን በርካቶች በብዙ ምክንያት አሳዝነሃል። “ታሞ የተነሳ…” እንዲሉ፣ ሁሉን ዘንግተህ በደንደነ ልብ ህዝብን ሰላም የሚነሳ ጉዳይ ላይ ተነክረሃልና ይቅርብህ። ሻለቃ ዳዊት ከሁዋላ ሆኖ እንደሚነዳህ በሜሪ ላንድ የተካሄደውን ስብሰባ የተከታተሉ ገልጸዋል። መቀመጫውን ኤርትራ ያደረገው ዳዊት ስንቴ ያጫርሰናል? አስብ…

See also  ደብረጽዮን አመኑ!!

ጓንጉል ሽብሬ ከሸዋሮቢት

ዝግጅት ክፍሉ- አቶ ጓንጉል ይህን ጽሁፍ ያደረሱን አሜሪካ ባሉ ቤሰሰባቸው አማካይነት ነው። አሳቡ የሳቸውና የሳቸው ብቻ ነው። በተለየ አግባብም ሆነ በተመሳሳይ መሳፍ ለምትፈልጉ መድረኩ ክፍት ነው

Leave a Reply