ሙሽራው ሙሽሪትን ትቶ ከሰርጉ ቤት ፈርጥቶ ወጣ

በናዝሬት ከተማ ሐምሌ 6 ቀን 67 ዓ.ም በርከት ያሉ ወጣቶች ጋብቻቸውን ባከበሩበት ዕለት በዚሁ ቀን የጋብቻውን በዓል የሚያከብረው ሌላው ሙሽራ ሙሽራይቱን ትቶ ከሰርጉ ቤት ፈርጥቶ የወጣ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በዚሁ ዕለት በናዝሬት ከተማ ውስጥ ጋብቻቻውን ከፈፀሙ ወጣቶች መካከል አቶ በቀለ ይልማና ወይዘሪት ደመቁ አሚኖ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኘው ህዝብ አዲስ ታሪክ ወይም ሆኖ ያልታወቀ ታአምር በማየቱ ታሪኩ በእነሱ ብቻ ሳይወሰን ለናዝሬት ከተማ ህዝብም ሳምንቱ ዜና ሆኖ መሰንበቱን አቶ ያለው በላቸው ለኢዜአ ወኪል ባስተላላፉት ዜና አስታውቀዋል፡፡

በዜናው ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በቀለ ይልማና ወይዘሪት ደመቁ አሚኖ የትዳር ጓደኞች ለመሆን ከተጫጩና ቀለበት ካደረጉ ጊዜው መሰንበቱ ታውቋል፡፡ይሁን እንጂ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት የተፈፀመው ከላይ በተጠቀሰው ዕለት ሲሆን በዚህ ቀን የወ/ሪት ደመቁ አሚኖ ቤተሰቦች የጠሯቸው ዕንግዶች በሰባት ሰዓት በሙሽራይቱ ቤት በተተከለው ድንኳን ውስጥ ተገኝተው የሙሽራውን መምጣት ሲጠባበቁና የሙሽራዋ ጓደኞችም አታሞ ድልቅ ድልቅ እያደረጉ የሰርግ ቤት ለማስመሰል ጥረት በማድረግ ላይ እንደነበሩ በዜናው ተገልጧል፡፡

ሙሽራው በተወሰነው ሰዓት ባለመምጣቱ የተጠራው ዕድምተኛ ምሳውን በልቶ የቀረበለትን ጠላ ጎንጨት እያለ መጠባበቁን ያላቋረጠ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

በዚሁ ወቅት ለዘጠኝ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ሲሆን ይጠበቅ የነበረው ሙሽራ የውል አባቱን ሚዜዎቹንና አጃቢዎቹን አስከትሎ እንደመጣ ‹‹ አናስገባም ሰርገኛውን ›› የሚሉ የሴት ወገኖች ሙሽራውን ለመቀበል ከበሩ ላይ እንዳሰፈሰፉ ሙሽራው ካራባት ባለማሰሩ መግባት የለለበትም የሚል ተቃውሞና ክተርክር መደረጉ ታውቋል፡፡

በዚሁ ጊዜ “ሙሽራው ክረባት ማሰር ሲገባው እንዴት እንዲሁ ይመጣል” በማለት ከአጃቢዎቹ መካከል አንዱ ለሙሽራው ክራባት አምጥቶ ሰጠው ሙሽራው ከራባቱን ሸብ አድርጎ ወደ ድንኳን መግባቱ ታውቋል፡፡

ህዝቡ ‹‹ሙሽራይቱን ማን ሊያመጣለት ነው›› እያለ የሹክሹክታ ወሬውን እንደቀጠለ የሴት ወገኖች አሁንም ሌላ ቅሬታ ስለነበራቸው ሚዜዎቹንና የውል አባቱን ወደ ውጭ አስጠርተው ማናጋገር እንደጀመሩ ሙሽራው ከጥቂት አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ በድንኳንኑ ውስጥ ቁጭ ብሎ መቅረቱን ይህው ዜና ያስረዳል፡፡

See also  ለ185 ቀናት በጠፈር ላይ የቆየዉ ሩሲያዊው በኢትዮጵያ ልምዱን እያካፈለ ይገኛል

በዚሁ አንፃር ከሙሽራይቱ ቤተሰቦች ጋር በውጭ ይነጋጋሩ የነበሩ ሰዎች ሙሽራው ለሙሽሪት ልብስ ሳይዝ መምጣቱ ነገር አስገርሟቸው ወደ ድንኳን ከተመለሱ ብኋላ ገንዘብ ያስይዝ ወይም ዋስ ይጥራና ይውሰድ የሚለውን ድምፅ ስላመዘነና ሚዜዎች ሁኔታውን ወደ ሙሽራው ጠጋ ብለው ቢያማክሩት ሙሽራው ከተቀመጠበት ፎቴ ብድግ ብሎ ‹‹አላደርገውም ምንም የማደርገው ነገር የለም›› በማላት ያሰረውን ከራባት ከአንገቱ ውልቅ አድርጎ በመወርወር ከድንኳኑ ውስጥ በሩጫ መውጣቱ ታውቋል፡፡

በዚሁ ወቅት ህዝቡ በመገረም ሙሽራውን ለመያዝ ቢከታተሉም አንድም ሰው ሊደርስበት ባለመቻሉ የተከታተሉት ሚዜዎች ወደ ሙሽራይቱ ቤት ተመልሰው ምክር ጀመሩ፡፡

ከዚያም የሙሽራው የውል አባት በመኪና የሙሽራው ቤት ቢሔዱ ሙሽራው ተቀምጦ ሙዚቃ በማዳመጥ ላይ እንዳለ አባብለው ወደ ሙሽሪት ካማጡት ብኋላ ለሙሽሪት ልብስ ማሟያ ገንዘብ እንዲከፍል ዋስ ጠርቶ ሙሽሪትን ይዞ እንዲሄድ መደረጉን ከተላላፈው ዜና ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጨረሻም አቶ በቀለ ይልማ አጃቢዎችና ሚዜዎች በቀኛ/እውነቱ ሀይሉ ሆቴል እራት ጋብዞ ሁለቱም የጋብቻ ስነ ስርአት በዚሁ አይነት ሁኔታ መፈፀሙን ይህው ዜና ጨምሮ ገልጧል፡፡

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ሐምሌ 07 1967 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ ከኢፕድ_ማህደር

(በሀይማኖት ከበደ)

Leave a Reply