Warning: array_column() expects parameter 1 to be array, string given in /home/ethio12/www/www/wp-content/plugins/coblocks/src/blocks/posts/index.php on line 32
በአመራሮች ላይ ጥቃት ለመፈፀም እና ግድያን ለማስቀጠል ፣ ሕገ መንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በማሰብ በኢ – መደበኛ አደረጃጀት በመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት የቀረቡት።
ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎችም መንበረ አለሙ ተከታይ፣ ሲሳይ መልካሙ አበበ፣ ገብርዓብ አለሙ ዘሪሁን (ዶ/ር)፣ ተስፋዬ መኩሪያው አበባው እና ወንደሰን ተገኝ ተስፋዬ ይባላሉ።
ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር ተግባር ሲንቀሳቀሱ መንግስት ባደረገው የሕግ ማስከበር ስራ አራቱ በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር ሲውሉ÷ 5ኛ ተጠርጣሪ ወንደሰን ተገኝ ተስፋዬ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎት አስረድቷል።
ተጠርጣሪዎቹ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በአመራሮች ላይ የሚያደርጉትን ግድያ ለማስቀጠል በማሰብ ፣አመፅና ብጥብጥ እንዲነሳ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ለወንጀል ተግባር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ሲያደራጁ ነበር ሲል ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አብራርቷል።
በተጨማሪም አንደኛና ሁለተኛ ተጠርጣሪዎች በአማራ ክልል ሕገመንግስቱን እና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በኢ-መደበኛ አደረጃጀት ለተደራጁ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ አስረድቷል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ በዚህ መልኩ በተጀመረባቸው የመነሻ የምርመራ ስራን አጠናክሮ ተጨማሪ ማስረጃ አካቶ ለመቅረብ በወ/መ/ስ/ህግ ቁጥር 59/1 መሰረት የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል ።
ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው÷ በፖሊስ የተገለፀው የሽብር ተግባር ተሳትፎ እንደሌላቸው በመከራከር የዋስ መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የተጠርጣሪዎችን የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ካለው የስራ ሰዓት አኳያ ተወያይቶ ለመወሰን በሚል በይደር ቀጠሮ ሰጥቷል።
fana