Site icon ETHIOREVIEW

አውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋገጠ፤ ተመድም ተመሳሳይ ቃል ገባ

ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም 27 የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሕብረቱ ከፍተኛ ተወካይ (የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት) ሊቀ መንበርነት ባደረጉት ስብሰባ÷ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ደረጃ ለማድረስ አዲስ እና መሰረታዊ መደምደሚያዎችን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

ውሳኔው በሕብረቱ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው አጋርነት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባሕር ለአውሮፓ ሕብረት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኗም ተጠቅሷል፡፡

በመሆኑም የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ሰላም በሚወስደው መንገድ ላይ የምታደርገውን ተጨማሪ መሻሻል ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ስለሆነም በእነዚህ አዲስ የፖሊሲ መደምደሚያዎች ሕብረቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ለተፈረመው ዘላቂ የጦርነት ማስቆም የሰላም ስምምነት ሙሉ ድጋፉን ገልጿል።

የስምምነቱን ትግበራ ቀጣይነት መሰረት በማድረግም÷ የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጠንካራ የፖለቲካ እና የፖሊሲ ውይይት ጋር መደበኛ በማድረግ ወደ ሙሉ እና የተጠናከረ ስትራቴጂያዊ ግንኙነት እንዲመለስ እንደሚያደርግ አመላክቷል፡፡

በዚህ አውድ ውስጥ በተለይ ተጠያቂነት እና የሽግግር ፍትህ አስፈላጊ መሆናቸውንም ነው ሕብረቱ የገለጸው፡፡

የአውሮፓ ሕብረት የሽግግር ፍትሕን በተመለከተ የወጣውን ግሪን ፔፐር (Green Paper) በመቀበል የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መመዘኛዎች እና ደንቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ በውስጡ የተካተቱትን አማራጮች በማሻሻል ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድ ያበረታታል።

በምክር ቤቱ መደምደሚያ ላይ የአውሮፓ ሕብረት በአብዛኛዎቹ ግጭት በተከሰተባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በቅርቡ የተሻሻለውን ሰብዓዊ አገልግሎት አቅርቦት በደስታ እንደሚቀበለውም ነው የተመለከተው፡፡

በከባድ ድርቅ እና ሌሎች ቀውሶች የተጎዱትን ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ጨምሮ የተስፋፋው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎቶች በቂ እና የተቀናጀ ምላሽ የሚሹ መሆናቸውንም እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የኦሮሚያና የአማራ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች የአውሮፓ ሕብረትን በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ግልፅ፣ ሁሉን አቀፍ፣ አካታች እና ሕዝብን ያማከለ ብሄራዊ የውይይት ሂደት እንዲቀጥል የአውሮፓ ሕብረት ጠይቋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ የግጭት አፈታት፣ ዕርቅ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በማጠናከር ላይ ተጨማሪ መሻሻል እንዲኖር የአውሮፓ ሕብረት መደበኛ የባለ ብዙ-ዓመት የልማት አመላካች መርሐ ግብሩን (EU MIP) እንደገና ለመጀመር ዝግጁ መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ትግበራን በሁሉም መስክ እንደሚደግፍ አስታወቀ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስት ደመቀ መኮንን ከተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ መኮንን የሰላም ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የሰላም አጀንዳውን በሌሎች አካባቢዎች ለመፈፀም መንግስት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን ጥረት የሚመጥን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ መፍታቷን አድንቀው፥ ፈታኝ የሆነውን የሰላም ሂደት ትግበራ በሁሉም መስክ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ዳግም ግንባታ እቅዱን ማገዝ እንደሚገባ በመጥቀስም፥ ሰላሙ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ዋቤዎቹን አመሳክሮ የዘገበው ፋና ነው።

በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉ
በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አንድ ኮሎኔል መገደላቸውም ተሰምቷል። የጊዚያዊ …
የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
በተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአባይ ድልድይን ለመመረቅ ወደ ባህር ዳር እንዳይመጡ ለ"ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ" በሚል በተለያዩ ቦታዎች ቦንብ ማፈንዳቱን ሃላፊነት ወስዶ ባስታወቀበት ወቅት ነው። ድልድዩ ሲመረቅ አብይ …
ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
አሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ "ተፈላጊዎች" ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች፤ ኤምባሲው ንግግር መደረጉን አስታውቋል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ …
“ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
በሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን …
Exit mobile version