ኢዜማ መንግስት ከኦነግ ጋር በሚያደርገው ድርድር ግልጽነትን ጠየቀ

መንግስት ባለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በሚንቀሳቀሰውና የተለያዩ ሽብር ተግባራትን በማከናወኑ በኢፌዴሪ ሕ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚለው እራሱን የኦሮም ነፃነት ሰራዊት ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር ችግሮችን በውይይት ለመፍታት በታንዛኒያ መቀመጡን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጥቅምት 24 /2015 ዓ.ም. የፕሪቶሪያው ስምምነት ሊደረግ መሆኑን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ‹‹በሌሎች የሀገሪቷ ክፍሎች ያሉ የታጠቁ ኃይሎችም ጋር በሰላማዊ ንግግር መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ ላይ በአፅንኦት መስራት ያስፈልጋል›› ሲል ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

አሁንም ሰላም የሰፈነባት እና ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለማየት ከፈለግን የትኛውም ዓይነት የሃሳብ ልዩነቶች ከአፈሙዝ ተላቀው ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ መቅረብ እንዳለባቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እናምናለን፡፡

በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ክቡር የሆነው ሕይወታቸውን ሲያጡ ንብረታቸውም ሲወድምና ከቀያቸው ሲፈናቀሉ በገሀድ ተመልክተናል፤ መንግስትም በተደጋጋሚ የተፈፀሙትን በደሎች ይህ ታጣቂ ቡድን ሲፈፅማቸው እንደነበር ከማሳወቁ አንፃር ይህን መሰል የዜጎች ሰቆቃ የሚያስቆም ድርድር ውስጥ መግባቱን የምናበረታታው ነው።

ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ሀገራችንን መምራት የጀመረበትን ጊዜ ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያየ ጊዜ የሚፈጸሙ እንዲህ አይነት ድርድሮች ግልጽነት ሲጎድላቸው እና አፈፃፀማቸው በተገቢ ሁኔታ ሳይከናወን ቀርቶ ብዥታዎችን ሲፈጥር ተመልክተናል፡፡

በቅርብ ጊዜ እንኳ መንግስት ከሕወሓት ጋር ድርድር አድርጌ ሰላም አውርጃለሁ ባለበት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደ ስምምነቱ ያልተፈጸሙ ጉዳዮችን አስተውለናል፡፡ ሂደቱም ምን ላይ እንደሆነ አሁንም ድረስ በግልፅ አይታወቅም፡፡ በዚህ ምክንያትም ኢዜማን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ላይ አሁንም ድረስ ከፍተኛ ቅሬታን እያስነሳ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡


ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል
   Facebook   Twitter   Messenger   Linkedin   Pinterest "ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም …
የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር
"ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል" ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ …
“የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”
የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ) የሚለው የቆየ …
በአማራ ክልል የተነሳው ጦርነት በሰላም ሊቆጭ እንደሚችል ተሰማ
በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የሚቋጭበት አግባብ ተስፋ ሰጪ ደረጃ …

ስለሆነም መንግስት ከዚህ ቀደም በለውጡ ሰሞን ኦነግ ከኤርትራ ወደ ሀገር ቤት ከገባ በኋላ በስምምነቱ መሠረት አልተፈጸመልኝም ሲል አንደነበረው ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር በተለይም ከሕወሓት ጋር ከተደረገው ስምምነት ልምዶች መነሻ በማድረግ፣ የድርድሩን ሂደትና ስምምነቱን በተመለከተ ህዝቡ ሊኖረው የሚገባውን ግልፅ መረጃ ፤ እነማን እየተሳተፉ እንደሆነ፣ የስምምነቱን ይዘት፣ እንዴት እንደሚፈጸም እና በአፈፃፀሙም ጊዜ ተግባራዊነቱን ለዜጎች ተገቢና በቂ መረጃን በማስተላለፍ ከተጨማሪ ውዥንብርና ትርምስ ማኅበረሰቡን እንዲጠበቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

See also  "ትህነግ ሰብዓዊ የእርዳታ ማጓጓዙን እያስተጓጎለ ነው" ዲና ሙፍቲ፤ "በቀን 300 ተሽከርካሪ እርዳታ ያስፈልጋል"ትህነግ

የዜግነት_ፓለቲካ ማኅበራዊ_ፍትህ ኢዜማ

Leave a Reply