ETHIOREVIEW

አብን በአማራ ክልል የተፈጠሩት ችግሮችን መንግስት በጥንቃቄና በውይይት ሊፈታቸው እንደሚችል መከረ

.….የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸውን በሸፍጥ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተገባ መልኩ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው እንደሚቀርቡ ሊታወቅ ይገባል። ትላንት የአማራ ሕዝብ መጠነሰፊ የወረራ ጦርነት ሲከፈትበት ዳር ላይ ቆመው የነበሩ እና ከጠላት ጋር አብረው የከረሙ አካላት የአማራ ሕዝብ ድንገተኛ ወዳጅ እና ወኪል በመሆን ግጭት ለማስነሳት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እናሳስባለን። የአማራ ሕዝብ እነዚህ አካላት የሚያደርጓቸውን አደንቋሪ የጥፋት ጥሪዎች ፈፅሞ እንዳይሰማ ለማስገንዘብ እንወዳለን

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ህዝብ በተደጋጋሚ ከተከፈተበት የወረራ ጦርነት ወጥቶ አንጻራዊ መረጋጋት ካሳዬ ገና ጥቂት ወራቶች ብቻ ተቆጥረዋል። በተከፈተበት ተደጋጋሚ ወረራ ለከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት መዳረጉ ይታወቃል። የአማራ ህዝብ ግጭትና ጦርነትን በተግባር የተመለከተ እንጅ በሩቅ የሚያውቀው ጉዳይ አይደለም።

የአማራ ህዝብ ያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ከፍትህ እና እኩልነት ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ከጥላቻና ፅንፈኛ ሃይሎች በስተቀር ሌሎች ወገኖች በተለይም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚያደምጧቸውና የሚደግፏቸው ናቸው።

በተለይ በጦርነቱ ወቅት የተከፈለውን ዋጋ በማይመጥን ደረጃና አግባብ የተመራው የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሁም ድኅረ-ጦርነት በመንግስት በኩል እየተካሄደ ያለው ግልፅነት የሌለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እና ስጋት መፍጠሩን መተማመን ያስፈልጋል።

በዚህ ረገድ የአማራ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ቀናኢነት እና ሀገሩን ለመታደግ የከፈለውን ዋጋ የሚያራክሱ ተግባራት መደበኛ ሆነው አደባባይ ላይ መዋላቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።

Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces (RSF), the paramilitary group is claiming. The RSF which has been battling soldiers of the Sudanese armed forces for control of the country since …
Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
Sudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of the Sudanese Armed Forces (SAF). Civil war broke out in Sudan in April last year involving Rapid Support Forces (RSF) led by …
Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
The Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the country’s diplomatic activities over the week, Spokesperson of the Ministry Nebiyu Tedla, indicated that Ethiopian delegation led by State …

ከዚህ በተጨማሪ በድኅረ-ጦርነት ወቅት ከሕዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሰረታዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ግልፅ ውይይት ባለመደረጉ ምክንያት የተፈጠሩ ችግሮች መሆናቸውን እንገነዘባለን።

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ምክንያቶቹ ለረዥም ጊዜ የቆየው የፖለቲካ ችግር እና ወቅታዊው የመንግስት ፍላጎትና አቅም ማጣት ናቸው።
በአንድ በኩል የአማራ ሕዝብ በተደጋጋሚ ሀገሩንና የማዕከላዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በመንግስት የተደረገለትን ጥሪዎችን በክብር ተቀብሎ መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል። ሆኖም መንግስት ለአማራ ሕዝብ ፍትኅዊ ጥያቄዎች፣ ፍላጎቶች እና ስጋቶች በቂ ትኩረት አለመስጠቱ ችግሩን አባብሶታል ብለን እናምናለን።

በአማራ ሕዝብ በኩል መንግስት ፍፁም መወያየትና ማድመጥ የማይፈልግ አካል መሆኑን አንድምታ ከተወሰደ ቆይቷል። አጠቃላይ ፖለቲካው ግልፅነት የጎደለው በመሆኑ እና ማሕበረሰቡን የሚያስተዳድርበትን ፍኖት ስለማያሳይ ዘወትር ጥርጣሬና የሴራ ትንተና የበላይነት እንዲኖረው በር ከፍቷል። ይሄም በሂደት እየጎለበተ ሄዶ አሁን ለተፈጠው የፀጥታ ችግር አስተዋፅኦ አድርጓል።

ስለሆነም በመንግስት በኩል በቀጠናው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጥታ በመወያየት ለተፈጠሩት ችግሮች እልባት የመስጠት ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አናሳስባለን። በተለይ ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና አንድነት በጋራ ተሰልፈው መስዋዕትነት የከፈሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቅራኔ ውስጥ እንዳይገቡና ለግጭት እንዳይዳረጉ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል።

መንግስት የክፉ ቀን አጋሩ ከነበሩትና በእውነትም ከሕዝብና ከሃገር ፍላጎትና ጥቅም በተፃራሪ የመቆም ተሞክሮ፣ ዝንባሌና ታሪክ ከሌላቸው የአማራ ገበሬዎች፣ ወጣቶችና ፋኖዎች ጋር ያልተገባ ግብግብ ውስጥ መግባት የለበትም። ይህ ጉዳይ በውይይት እና ምክክር ሊፈታ የሚችል መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

በሌላ በኩል ግን የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸውን በሸፍጥ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተገባ መልኩ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው እንደሚቀርቡ ሊታወቅ ይገባል። ትላንት የአማራ ሕዝብ መጠነሰፊ የወረራ ጦርነት ሲከፈትበት ዳር ላይ ቆመው የነበሩ እና ከጠላት ጋር አብረው የከረሙ አካላት የአማራ ሕዝብ ድንገተኛ ወዳጅ እና ወኪል በመሆን ግጭት ለማስነሳት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እናሳስባለን።
የአማራ ሕዝብ እነዚህ አካላት የሚያደርጓቸውን አደንቋሪ የጥፋት ጥሪዎች ፈፅሞ እንዳይሰማ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በተለይ የአማራ ወጣቶች፣ ፋኖዎች እና የልዩ ሃይል አባላት የሕዝባችን ሰላም እና ደህንነት እንዳይናጋ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዳይሰተጓጎሉ፣ የልማት ስራዎች እንዳይኮላሹ፣ በዋናነት ደግሞ ወገኖቻችን ላይ ምንም አይነት አካላዊ እና የህይወት ጉዳት እንዳይደርስ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ጥሪ አናቀርባለን። የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ምናልባት በጊዜያዊ ስሜት ሳይገፉ በሆደ ሰፊነት ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ተመሳሳይ ትጋት እንዲያሳዩ ጥሪ ለማቅረብ እንወዳለን።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአማራ ሕዝብ ያሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲዘነጋና በምትኩ በደራሽና ስሜታዊነት በተጫናቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩር የሚገፋፉ እንቅስቃሴዎች፣ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ የአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳዎች ሰለባ እንዳይሆን ህዝባችንና የህዝባችን ወዳጆች ሁሉ አዎንታዊ እገዛ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ህዝባችን ግራ ቀኙን በአግባቡ መዝኖ በስሙ የሚነግዱ ኃይሎችን ይሁንታ ሊነሳቸው ይገባል።

አብን አጠቃላይ የህዝባችን ትግል በሂደትና በየደረጃው ሰላምና መረጋጋት እንዲጎለብት፣ ጦርነትና ደም መፋሰስ እንዲቆም፣ የንግግርና የምክክር ምዕራፍ እንዲከፈት የሚያደርግ መሆን አለበት ብለን እናምናለን። ለአማራ ህዝብ እንታገላለን የሚሉ ኃይሎች ለህዝቡ ሰላም እና መረጋጋት ቅድሚያ መስጠት እና ሕዝባችን ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር ያለው ወዳጅነት እየተጠናከረ የሚሄድበትን መንገድ መቀየስ አለባቸው። በዚሁ አጋጣሚ የሌሎች ወንድም ሕዝቦችን ማንነት ማንቋሸሽ እና መዝለፍ የአማራ ሕዝብ ፍላጎት እንዳልሆነና መቼም ሆኖም እንደማያውቅ፣ ወደፊትም ጭምር እንደማይሆን በጥብቅ ማሳወቅ እንሻለን። ይህ የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የሚያዛምቱትን የሀሳት ትርክት በተዘዋዋሪ መንገድ ለማረጋገጥ የሚደረግ ከንቱ ጥረት እንደሆነ ማስገንዘብ እንፈልጋለን።
በአማራ ሕዝብ ላይ ነውረኛ የሆኑ ፅንፈኛ ኃይሎች የሚያሰሙትን ፀያፍ ንግግርና የሚፈፅሙትን ጥቃት በአማራ ሕዝብ ስም በሌሎች ወገኖች ላይ መፈፀም ለአማራ ሕዝብም ይሁን ለኢትዮጵያ ተጨማሪና ተደራራቢ ችግር ከመፍጠር ባለፈ የሚያጣፋው ወይም የሚፈታው ችግር አይኖርም። የአማራ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ያደሩና የሚታወቁ የፍትኅ፣ የእኩልነት እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በመሆናቸው በጊዜ ሂደት፣ በሰላማዊ መንገድ፣ በውይይትና በሰለጠነ ድርድር እንዲሁም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወንድምና እህቶቻችን ድጋፍና ትብብር የሚሳኩ ናቸው።

ሌላው ከህዝባችን የመከራና የሰቆቃ አድማስ የራቁና የማይታወቁ እንዲሁም በመንግስት መዋቅሮች እና በተለያዩ የፖለቲካ አሰላለፎች ውስጥ ሆነው በአማራ ሕዝብ ላይ ዘወትር ግጭት የሚጠምቁ፣ የአማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና ማድረግ የሚፈልጉ አካላት በአስቸኳይ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጥሪ እናስተላልፋለን።

የህልውና ዘመቻው አይነተኛ ሚና የነበራቸውን የአማራ ፋኖዎች በውትወታ ከመስመር ማስወጣት እና ግጭት ውስጥ ማስገባት፣ በቅጡ ባልተሰላ ፖለቲካ ሕዝባችንን ማጎሳቆል የሚፈልጉ ኃይሎች ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

ስለሆነም:-

  1. የባለድርሻ አካላት ውይይት ማለትም የክልል እና የፌድራል መንግስት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ የምሁራን መማክርት፣
    ታዋቂ እና ተደማጭ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ካውንስልን ያካተተ ቡድን በተመረጡ ከተማዎች አንገብጋቢ አጀንዳዎችን ለይቶ ከህዝባችን ጋር ውይይት በማድረግ፣ ውዥንብርን በማጥራት የጋራ መረዳት እንዲፈጠር ማድረግ ይገባል ለዚህም ጥሪ እናደርጋለን።
  2. ሐገራችንም ሆነ የአማራ ህዝብ የተቃጣባቸውን ወረራ በመመከት ሂደት ላይ ለመከላከያ ሰራዊት ባደረገው የደጀንነት ሚና ከፍተኛ ምስጋና የተቸረው መሆኑ የትናንት ትዝታ ነው። በዚህም የአማራ ህዝብ ሐገር ችግር ላይ በወደቀች ጊዜ ከሐገሩ ጎን የመሰለፍ የቆዬ ታሪኩን ያስመሰከረ ሐቅ ሆኖ አልፏል። ስለሆነም ከዚህ የወገን ኃይል ጋር ፈፅሞ መቃቃር አስፈላጊ ነው የሚል እምነት የለንም።
  3. ፋኖን ጨምሮ ለሁሉም ታጣቂ ወንድሞቻችን ህዝባችን ላይ የተቃጣውን ወረራ በመመከት ሂደት ላይ ያሳያችሁት ቆራጥነት በታሪክ የተመዘገበ የጀግንነት ፍኖት ሆኖ አልፏል። ለዚህ ውለታችሁም የአማራ ህዝብ የተሟላ ሰላም ውስጥ በሚገባበት ወቅት አስፈላጊውን ሽልማት እና እውቅና የሚቸራችሁ እንደሚሆን እናምናለን። ሆኖም ትናንት በአንድ ምሽግ አድራችሁ፣ በአንድ ኮዳ ጠጥታችሁ፣ በአንድ ሳህን ቆርሳችሁ፣ በአንድ ጉድጓድ ከተቀበረው ወንድማችሁ ከሆነው የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል የፀጥታ ኃይል ጋር በፍፁም ግጭት ውስጥ መግባት እንደሌለባችሁ አበክረን እንረዳለን። ስለሆነም አሁን ያለውን መካረር በማርገብ በተወካዮቻችሁ ዘንድ ከፀጥታ አካላት አመራሮች ጋር ንግግር ትጀምሩ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
  4. የአማራ ክልል መንግስትን ጨምሮ የፌደራል መንግስት ከግጭት ተጨማሪ ሀገራዊ ጉስቁልና ከመጋበዝ ውጭ ምንም አይነት ዘላቂ ፖለቲካዊ ትርፍ ማግኘት እንደማይቻል ያሳለፍነው የጦርነት መንገድ በቂ ትምህርት ሰጥቷል የሚል ፅኑ እምነት አለን። ስለሆነም መንግስት ከግጭት ምንም ፋይዳ እንደማይገኝ ተረድቶ አሁን ላይ እየታዬ የመጣውን መካረር በሰላም ማዕቀፍ የሚፈታበትን እድል እንዲተገብር በጥብቅ እናሳስባለን። ስለሆነም መንግስት ደም አፋሳሽ ሊሆን የሚችልን እቅድ ሁሉ ከወዲሁ ተረድቶ ለሰላም እና ውይይት በር እንዲከፍት እና በአስቸኳይ እንዲተገብር እንጠይቃለን።

በተያያዘ መልኩ የመንግስት የፀጥታ አስከባሪ አካላት ንፁኃን እንዳይጠቁ እና ያላግባብ እንዳይታሰሩ ማድረግ እንዳለባቸው እንዲሁም ያላግባብ የታሰሩትን ባስቸኳይ እንዲፈቱ እናሳስባለን።

በመጨረሻም የጋራ የውይይት መድረኩ በአስቸኳይ እውን ይሆን ዘንድ አብን የማስተባበር ድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ እየጠቆመ ባለ ድርሻ አካላት ዕቅዱ በአፋጣኝ ይተገበር ዘንድ የዘወትር ትብብራችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች

አሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች፤ ኤምባሲው ንግግር መደረጉን አስታውቋል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ጥያቄውን ያቀረቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር…

ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል

ፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በህዝብ ጥቆማ እንደሆነ ተመልክቷል። ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ…

“ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ

በሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን ከፍፍሏል። ትህነግ በድርጅት ደረጃ በውስጡ አለመጋባባት…

Exit mobile version