“ከአርበኝነት ውርስ ባሻገር”

የኢትዮጵያ አርበኞች 82ኛ የድል መታሠቢያ በዓል ሁሌም አዲስ ነው። የድሉ ጊዜ አንድ ዘመን ሊሞላ ቢቃረብም፣ ሁሌም አዲስ የሚሆነው በታሪኩ ግዝፈትና አሁን ድረስ አገር እያሰቃዩ ያሉ ባንዳዎች ህልማቸው እንደማይሳካ ማሳያ በመሆኑ ነው። አዲሱ ትውልድ ጀግነትን እሚማርበት፣ ኩራትን የሚቀበልበት፣ ባንዳነት ምን ያህል ነወር እንደሆነ የሚረዳበት ነው። የአርበኞች ቀን ሲከበር የዛ ዘመን ጀግኖች አጥንትና ስጋ እንደ ዜጋ በክብር ማማ ላይ ያቆመን እንደሆነ በመረዳት ነው። ከመረዳትም በላይ ከልብ የመነጨ ክብር በመስጠት ነው። ሲሻገርም ዓላማውን እንደ ዘመኑ በሟሟሸት የመረከብ ቃል በመግባትም ነው። ከአርበኛነት ውርስም ባሻገር ማየት ድግ ነው። ከስር ያለውን ያንብቡ

የኢትዮጵያ አርበኞች 82ኛ የድል መታሠቢያ በዓል ከመከላከያ ገጽ የተወሰደ

“አብሮነት ለፅናት እና ለድል” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው የድል በዓል ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አባትና እናት አርበኞች ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ፤ የሰራዊቱ ተወካዮች ፤የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ፤ ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሀገር በማያቋርጥ የትውልድ ቅብብሎሽ እየተገነባች በአዳዲስ ታሪክ ሁነት እየጎላች የምትቀጥል መሆኗ ይታወቃል። ትላንት ለኢትዮጵያችን ነጻነት በዱር በገደሉ በጀግንነት ተዋድቀው ያስከበሩንን አባቶቻችንን መዘከር የሀገራዊ ታሪክ ውርርስ አካል ነው።

ለሀገር ብሄራዊ ፍላጎትና ጥቅም ብሎም ለኢትዮጵያችን ሰላምና ክብር በተጠንቀቅ ዘብ ቆሞ የሚገኘው ጀግናው የኢትዮጵያ ወታደርም፤ከአያት አባቶቹ አርበኝነትን በክብር የወረሰ ነው። ትውልድ እንደየዘመኑ እውነታ የራሱ ቀለም አለው። ከ82 ዓመታት በፊት የነበረው ሀገራዊ እውነታችንና አሁናዊው የሀገራችን እውነታ ይለያያሉ።

ያኔ ጣሊያን በዳግም ወረራው ቂም ቋጥሮ በማንበርከክ ተስፋ የመጣ ጊዜ፤ወቅቱ ይጠይቅ የነበረውን ጽናትና ጀግንነት አንግበው የተዋደቁልን አባቶቻችን የዘመኑን ግዴታቸውን በአኩሪ መስዋዕትነት መወጣት ችለዋልና ታሪካቸው በህያውነት እየተከበረ ነው።ሲከበርም ይኖራል።

የጀግኖች አርበኞቹን ጽናት፣አይበገሬነትና ድል አድራጊነትን የወረሰው የአሁኑ መከላከያ ሠራዊታችንም በዘመኑ ቀለምና ነባራዊ እውነታ ላይ የተመሠረተ ታሪክ በመከወን ላይ ይገኛል።

ብርቱ ፈተናዎችንን እልህ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትንቅንቆችን በታላቅ ቆራጥነትና ተጋድሎ በድል የተወጣው መከላከያ ሰራዊታችን ስለ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ክብርና ሁለንተናዊ ዕድገት መቀጠል ሲል የከፈላቸውና እየከፈላቸው የሚገኙ መራር መስዋዕትነቶች በመጪው ትውልድ በኩራት ሲወሱ የሚኖሩ ናቸው።

See also  " በመንጋ የመጣው ሃይል እየተመከተ ነው፤ የተደራጀ ንቅናቄ"

ሀገርን በጫጫታ ለማፍረስ ያለ አንዳች ይሉኝታ አይናቸውን በጨው አጥበው የሚያደናቁሩ ኢትዮጵያ ጠል ሃይሎችን ህልም እያመከነ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር የምትሸጋገር ኢትዮጵያን ለማጽናት ያለ ዕረፍት ተልዕኮውን የሚወጣው ሠራዊታችን በሀገሩ መጻኢ-መልካም ተስፋ ላይ የጸና እምነት አለው።

ከትላንት አባቶች ከወረሰው አርበኝነት ባሻገር፤ ከሀገር በዘለለ ቀጠናዊ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የውትድርና ጥበብና ሳይንስን በተላበሰ ዘመናዊነት በእውቀትና ክህሎት አይደፈሬ ሀገርን እውን የማድረግ ፈጣን ጉዞው ቀጥሏል።

እናም በራሱ የዘመን ቀለም የራሱን ታሪክ በአንጸባራቂ ድሎች ታጅቦ እያነበረ የሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፤ ሀገር የማጽናት ተግባሩን ትላንት ለሀገራቸው ቀናኢ ሆነው በዱር በገደሉ ተዋድቀው ነጻነታችንን እንዳላስደፈሩት አርበኞቻችን ሁሉ በጥልቅ የሀገር ፍቅር የተሞላ ነው።

አስቻለው ሌንጫ ከአገር መከላከያ ገጽ የተወሰደ

……………………………………………………………

“አርበኝነት ሀገርን በፍቅር መውደድና ያንንም በተግባር ማሳየት ነው” ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ አበበ

ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ አበበ ትውልድና ዕድገታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ላይ እንዳሉ የሶማሊያ ጦር ሀገርን ሲወር 1969 ዓ.ም ወደ ካራማራ ማቅናታቸውን ይናገራሉ፡፡ ከዚያ በኋላም ለ14 ዓመታት በውትድርና ሙያ ሀገሬን በፍቅር አገልግያለሁ ሲሉ ነግረውናል፡፡

በዓድዋ ፣ በካራማራና በሌሎች ሀገር ላይ በተቃጡ ወረራዎች ሀገራችን ድል ያደረገችው አባቶቻችን በፍጹም የሀገር ፍቅርና አንድነት ስሜት በመዝመታቸው ነው የሚሉት ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ ይህም ከጦር መሣሪያ በላይ ዋጋው ትልቅ እንደኾነ ያነሳሉ፡፡

ቀደምት አባቶቻችን ቤትና ቤተሰብ ሳይሉ ሀገራቸውን በፍቅር ይወዱ ስለነበር ያንንም በተግባር ማሳየታቸውን ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ አስታውሰዋል። እኛም በነበርንበት ዘመን ያንን አድረገናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የአርበኞች ድል መታሰቢያንም ኾነ ሌሎች በዓላትን ከማክበር በዘለለ ያንን ታሪክ ማስረዳትና በወቅቱ የነበረውን ኢትየጵያዊ አንድነት የተረዳ ማኅበረሰብ መፍጠር ይገባል ነው ያሉት፡፡

እኛ ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር የከፈልነው መስዋዕትነት ከቀደሙት አባቶች የተማርነው በመኾኑ የአሁኑ ትውልድም ከእኛ ሊማርና የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቆ የማወቅ ኀላፊነት አለበት ሲሉ ይናገራሉ፡፡

ለኢትዮጵያ ነጻነትና ሉዓላዊነት መከበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገር ፍቅር ስሜት ያስገኘውን ድል ሌሎች ሀገራትም ምስክርነታቸውን የሰጡት የአንድነታችን ውጤት መኾኑን ልናውቅ ይገባል ነው ያሉት፡፡

See also  የሰላማዊ ሰልፉ ተራዘመ፤ የስምምነት ፍንጭ እየተሰማ ነው

አሁን ለውስጣዊ አንድነታችን መጠናከር ከቀደሙ ታሪኮችና አባቶች ልምድ መውሰድ የሚገባን ጊዜ ላይ በመኾናችን ሀገርን ማዕከል ያደረገ ተግባቦት ሊኖረን ይገባል ሲሉ ሻለቃ ባሻ ስንታሁ አበበ አመላክተዋል፡፡

ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ / አሚኮ

ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?
አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! …
ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው
– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ …
መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉ
የታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን …
በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነው
በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት …
አዲስ አበባ – ሙስና በገሃድ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ … አገልግሎቶች ምሬት
" የጸረ ሙስና ኮሚሽን ራሱ ሌላ መረማሪ ተቋም ሊበጅለት ይገባል" እስኪባል ድረስ ተቋሙ የነተበ ስለመሆኑ ያቋቋሙት አቶ መለስ በህይወት እያሉ የተሰጠ አስተያየት ነበር። ዛሬም ድረስ …

Leave a Reply