ግብርና ሚኒስቴር 480 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታወቀ

በዘንድሮው 2014/15 የምርት ዘመን ከሰብል ልማት ከ 480 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለኢፕድ በላከው ሪፖርት እንዳስታወቀው፤ የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው። በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በዘር ከተሸፈነው 14 ነጥብ 43 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 480 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቷል።

እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጻ፤ በአነስተኛ አርሶ አደሮች በአዝርዕት ሰብል 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ 14 ሚሊዮን ሄክታር መሬት
በዘር የተሸፈነ ሲሆን፣ ከዚህም 393 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት እንደተቻለ ሪፖርቱ አመላክቷል።

በአነስተኛ አርሶ አደሮች የዋና ዋና ሰብሎች ምርታማነት 31 ኩንታል በሄክታር ለማድረስ ታቅዶ 30 ኩንታል በሄክታር ማድረስ እንደተቻለም ታውቋል።
በኩታ ገጠም እርሻ 6 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እቅዱን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት የተቻለ ሲሆን በዚህም 9 ነጥብ አንድ ሚሊዮን አርሶ አደሮች ተሳታፊ መሆናቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በ2014/15 ምርት ዘመን በሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት ከለማ ሰብልም በጥቅሉ 30 ነጥብ 34 ሚሊዮን ኩንታል የአዝርዕት ምርት ተገኝቷል ሲል አስረድቷል።
ከውጭ የሚገባ የስንዴ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተቀመጠውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት የመስኖ ስንዴ ልማት በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ ሲዳማ፤ ሶማሌ፤ ጋምቤላ፤ቤኒሻንጉልና አፋር ክልሎች አንድ ነጥብ 32 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመሸፈን 52 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ አንድ ነጥብ 36 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑንም ሪፖርቱ ጠቁሟል።

በባህላዊ 274 ሺህ 853 ሄክታር መሬት እና በዘመናዊ ዘዴ 62 ሺህ 852 ሄክታር መሬት በድምሩ 337 ሺህ 705 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ከለማ የስንዴ ሰብል ሰባት ሚሊዮን 849 ሺህ 441 ኩንታል ምርት መገኘቱም ታውቋል።
በተጨማሪም በባህላዊ ዘዴ ከተሰበሰበው 274 ሺህ 853 ሄክታር መሬት ላይ 71 ሺህ 240 ሄክታር ላይ ስንዴ እየለማ መሆኑንም ሪፖርቱ አመላክቷል።

See also  የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በሳይንሳዊ መንገድ ያዘጋጃቸውን የባህል መድኃኒቶች፤ ሰው ላይ ሊሞክር ነው

Leave a Reply