የአማራ ክልል የቴዎድሮስ ክፍል ጦር ልዩ ሃይል የሰላም ጥሪ ተቀበሎ ካምፕ ገባ

በሕግ ወጥ መልኩ በዘመን ትህነግ በየክልሉ ተቋቁመው የነበሩና ልዩ ኃይሎች ፈርሰው ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ እንዲገቡ በተወሰነው መሠረት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር ጥሪውን ተቀበሎ ወደ ካምፕ ገብቷል።

መንግሥት ያቀረበውን የልዩ ኃይል ሪፎርም ተቀብለው ሰላምን መርጠው ወደ ሕጋዊ መንገድ የመጡ የቴዎድሮስ ክፍለ-ጦር የልዩ ኃይል አባላትን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ደማቅ አቀባበል አደርጎላቸዋል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተንጠባጥበው ለተበተኑ የልዩ ኃይል አባላትም በፈለጉት ማለትም የክልል ወይም የፌደራል ፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ዶ/ር ወንደሰን የተባለ ግለሰብ ከመስከረም አበራ ጋር ሲያወራ የተቀዳ ተብሎ በተሰራጨው የድምጽ ቅጂ ላይ እንደሚሰማው በጎንደር ያለውን ልዩ ኃይል ለማስካድ የተሠራው ሥራ መክሸፉን የሚገልጽ ነበር። ሤራውን እምቢ ብለው ወደ ካምፕ የገቡትን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን በተመለከተ ለምን እንደገቡ መስከረም ለጠየቀችው ወንደሰን ሲናገር “እንጃባታቸው” በማለት ነበር የመለሰው።

ጎንደር የቅርቡን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማርሽ በመቀየር በተደጋጋሚ ወሳኝ ሚና ስትጫወት ቆይታለች፤ ይህ ሦስተኛዋ ነው።

ከለውጡ በፊት የነበረውን ኦሮሙማ እንቅስቃሴ “የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” በሚል ገልብጦ ለውጡን አገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ማርሻ የቀየረው ጎንደር፣ የፖለቲካውን ትግል እንዲነድና የትህነግ/ህወሃት መጥፊያ እንዲቃረብ በማድረጉ ሲጠቀስ እንደሚኖር ያወሱ ወገኖች፣ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በምላሹ “የአማራ ደም የኔም ደም ነው” ሲሉ የትግሉን አቅጣጫ በመቀበልና በማስተጋባት፣ በትህነግ የተፈራውን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ የትግል አንድነትን በማግነን ታሪክ መሠራቱን ገልጸዋል።

ሁለተኛው የዛሬ ሁለት ዓመት በወለጋ እና በሌሎች አካባቢዎች ማንነትን መሠረት ያደረገ የጅምላ ጭፈጨፋ ሲካሄድ የአማራ ክልል በሰላማዊ ሰልፍ መናወጥ ጀመረ። የዚህ ነውጥ ፊት አውራሪ ግን ከጀርባ ሆኖ ይዘውረው የነበረው በደርግ ጊዜ በተከሰተው ድርቅ የረሃብተኛውን ብር ሰርቆ ከአገር በኮበለለው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ነበር

በሁሉም የአማራ ክልል ቦታዎች እየተቀጣጠለ ይሄዳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት እንቅስቃሴ ጎንደር ሲደርስ ተነፈሰ። ኦሮሞን ወንጅሎና በኦሮሞ ላይ ጽንፈኛ አቋም ይዞ ይወጣል የተባለው ጎንደር የችግሩን ምንጭ ነቅሶ አወጣው፤ እንቅስቃሴውም በረደ። 

See also  የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ

በሰሜን ሸዋ በተለይ አጣዬ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘር የለየ ጭፍጨፋ በመቃወም አደባባይ የወጡት የጎንደር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች “የከዳን ኦህዴድ እንጂ ወንድም የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም” የሚል መፈክር አጉልተው በማሳየት ያሳዩት ተቃውሞ በወቅቱ “ሥልጡን” ተብሏል። ጽንፈኛ አመለካከት ላላቸው ደግሞ ታላቅ መልዕክት እንደሆነ ነው የተጠቆመው።

አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ልዩ ኃይሉን መከታ በማድረግ፣ በወልቃይት በማስፈራራት ወደ አመጽ እንዲገባ ሲዋከብ የነበረው በተለይ የጎንደር ልዩ ኃይል ሁኔታዎችን አመዛዝኖ በውስጥና በውጪ ኃይሎች የተደገሰውን ሤራ አክሽፏል። ከልዩ ኃይል ውስጥ በስመጥር እንደሆን የሚነገርለት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ካምፕ ገብቷል። ጎንደርም ታሪክ በመሥራት ኢትዮጵያን እየታደገች ትቀጥላለች።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

Leave a Reply