ሀገር ፈተና ውስጥ ሳለች ብርቱ ክንዶቻቸውን ጋሻ አድርገው ሀገር እና ሕዝብን ከውርደት ታድገዋል፡፡ እንደ አባቶቻቸው ክተት ሲባሉ ከትተው ግንባራቸውን ለአሩር፣ ደረታቸውን ለጦር እግሮቻቸውን ለጠጠር ሰጥተው ታሪክ እና ሀገርን አስጠብቀው አቆይተዋል፡፡ ታሪክ የማይረሳ እና ትውልድ በየዘመኑ የሚያስታውሰው ጀብዱ የሰሩት የዘመኑ አናብስት የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት፡፡
የክልል ልዩ ኃይል አባላትን በላቀ ደረጃ መልሶ ማደራጅት እንደሚያስፈልግ ታምኖበት ወደ ሥራ ከተገባ ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡ ምንም እንኳን ይላሉ የልዩ ኃይል አባላቱ “ጦሩን በላቀ ደረጃ መልሶ ለማደራጀት የተሰጠው ጊዜ አጭር በመኾኑ በቂ ውይይት አለመደረጉ ተፈጥሮ ለነበረው አለመግባባት ምክንያት ቢኾንም፤ በቀጣይ የክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ በላቀ ብቃት ለመፈጸም የሚያስችል ዝግጅት እያደረግን ነው” ብለዋል፡፡
የልዩ ኃይል አባላቱ በፌዴራል እና በክልል የጸጥታ ተቋማት ውስጥ እንደየፍላጎታቸው እና ምርጫቸው እንዲሰማሩ አሠራር ተዘርግቶ እየተተገበረ ነው፡፡ ከቀረበላቸው ምርጫዎች መካከል የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽንን ከመረጡት ኮሚሽኑ የሚሰጠውን የተሃድሶ ሥልጠና ከሚወስዱ አባላት መካከል ረዳት ኢንስቴክተር ከፍያለው ደጀንን እና ሃና ደገፉን አሚኮ አነጋግሯቸዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት ክልሉ እና ሀገሪቱ ከነበሩበት የህልውና ሥጋት አንጻር በተለያዩ ግንባሮች የአማራ ሕዝብ እና መንግሥት የሰጡንን አደራ በብቃት ለመወጣት ሞክረናል ያለን የነብሮ ክፍለ ጦር የሕግ ክፍል ኃላፊ የነበረው ረዳት ኢንስፔክተር ከፍያለው ደጀን በቀጣይም የክልሉ ሕዝብ እና መንግሥት የሰጡኝን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ጥረት አደርጋለሁ ብሏል፡፡ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከሌሎች የጸጥታ ተቋማት የተለየ የራሱ ተግባር እና ኃላፊነት አለው ያለን ረዳት ኢንስፔክተር ከፍያለው የኮሚሽኑን አሠራር ለመገንዘብ የሚያስችል የተሃድሶ ስልጠና መውሰዳችን ተገቢ ነው ብሏል፡፡
በአማራ ልዩ ኃይል የነበልባል ክፍለ ጦር አባል የነበረችው ሃና ደገፉ ከቀረቡላቸው አማራጮች መካከል የማረሚያ ቤት ኮሚሽንን መምረጧን ገልጻ በቀጣይም የተሰጣትን ተግባር እና ኅላፊነት በብቃት ለመወጣት መዘጋጀቷን ገልጻለች፡፡
የአማራ ልዩ ኃይል በቆይታው የክልሉን ሕዝብ በላቀ ብቃት አገልግሏል ያሉት አባላቱ የተሰው እና ጉዳት የደረሰባቸውን የሠራዊቱን አባላት እና ቤተሰቦች በዘላቂነት ማቋቋም የክልሉ መንግሥት ኃላፊነት ሊኾን ይገባል ብለዋል፡፡ ሀገር እና ሕዝብ በፈለገቻቸው ጊዜ በየትኛውም ግዳጅ ለመሳተፍ ዝግጁ እንደኾኑም ተናግረዋል፡፡
የክልሉን ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምርጫቸው ያደረጉ የልዩ ኃይል አባላት ኮሚሽኑ የነበሩበትን ክፍተት ለመሙላት ጉልበት ይኾናሉ ያሉን ደግሞ የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴ ናቸው፡፡ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ከሌሎች የጸጥታ ተቋማት በተለየ የሕግ ታራሚዎችን የማረም፣ የማነጽ፣ የማጀብ እና የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያሉት ረዳት ኮሚሽነር ውቤ ለዚህ ተልእኮ ብቁ የሚያደርግ ተጨማሪ የተሃድሶ ሥልጠና መሥጠት አስፈላጊ ነበር ብለዋል፡፡
በአዲስ ኮሚሽኑን የተቀላቀሉ የልዩ ኃይል አባላት ክብራቸውን፣ ጥቅማቸውን እና ደረጃቸውን የሚመጥን ስምሪት ይሰጣቸዋል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ የነበራቸውን ወታደራዊ ልምድ፣ እውቀት፣ ሥነ-ምግባር እና ክህሎት በመጠቀም የኮሚሽኑን አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሳሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው አሚኮ
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report
- ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችምዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የጠቀችውን ብድር ለመፍቀድ ያቀረቡት ዋና ቅድመ ሁኔታ የብርን የመግዛት አቅም ዝቅ ማድረግ ወይም በነጮቹ አፍ… Read more: ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችም
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories ረሃብና ስንዴ – ኢትዮጵያን የመክሰስ አባዜ-ከጥንት እስከ ዛሬJune 17, 2023 ትህነግ በውጊያ በቆሰሉና በሞቱ ታጣቂዎቹ “የጅምላ ጭፍጨፋ ተደረገ የሚል” የሴራ… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ