የምዕራቡ ክንድ … አስተማማኝ ሃይል

በህግ ማስከበር ዘመቻው ግንባር ቀደም ነው ፤ በህብረ ብሔራዊ እና የህልውና ዘመቻው ስኬታማ ነው፤ በላቀ የሜካናይዝድ እውቀቱ በጠንካራ ስነ አዕምሯዊ እና ወታደራዊ ዝግጁነቱ ከሌሎች አሀዱዎች ጋር በመናበብ አገርን ከብተና ህዝብን ደግሞ ከእልቂት የታደገ አስተማማኝ ሃይል ሜካናይዝድ ክፍለጦሩ።

የምዕራቡ ክንድ ሶሜክ ከዘመኑ ጋር የዘመነ የካበተ የሜካናይዝድ ልምድ ባለቤት ነው ፤ መደበኛ የሜካናይዝድ ተልዕኮውን በጀግንነት እየተወጣም ይገኛል። የተሟላ ወትሮ ዝግጁነቱን በማረጋገጥ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ የአገራችን ዳር ድንበር እና ሉዓላዊነት በጀግንነት እያስከበረ የሚገኝ ነው፤ በበሳል አመራር ሰጭነት በተሟላ የዕዝ ቁጥጥር እና ስርዓት ተልዕኮውን ይከውናል ።

መደበኛ የሜካናይዝድ ተልዕኮውን በድል ይፈፅማል ፤ በወታደራዊ አካል ብቃቱና በስነ አእምሮው እራሱን ያዘጋጃል ፣በሜካናይዝድ እውቀቱ የበቃ የላቀ እና የዳበረ ምድብተኛ ያረጋግጣል ፣ በግዳጅ የተፈተነ በድል የተረጋገጠ አስተማማኝ የሆነ ሃይል ገንብቷል ፤ በአላማው የፀና በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ነው ፤የምዕራቡ ክንድ ሶሜክ በአደረጃጀቱ ልክ ብቃቱን እውቀቱን እና የማድረግ አቅሙን በማሳደግ የነገን ፈተና በስኬት መሻገር የሚችል ነው።

ወታደራዊ ዝግጁነቱን ከሳይንሳዊ እውቀቱ ጋር በማዋሃድ ከዘመኑ ጋር የዘመነ የሜካናይዝድ ግንዛቤውን ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ከፍ እያደረገ የሚገኝ የምዕራቡ ክንድ አስተማማኝ መቺ ሃይል ነው፤ ካለው የሜካናይዝድ እውቀት ላይ እየደመረ በየጊዜው ይሰለጥናል፣ እራሱን ያበቃል ፣ያዘጋጃል ፣የተሟላ የሜካናይዝድ እውቀቱን በማበልፀግ በወታደራዊ ዓላማው የፀና በሙያው ብቁ የሆነ ሃይል አዘጋጅቷል።

የምዕራቡ ክንድ ሶሜክ ረዥም ርቀት የሚመታ ነው ፤የጦር ሜዳው አውደ ንጉስ የእግረኛው ሃይላችን የጀርባ አጥንት ነው፤ ከፍተኛ ዕርቀት ያለው ኪሎ ሜትር በመወርወር ድንበር ወሰን ይጠብቃል ፤ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ መሰናክል አያቆመውም ፣ጋራ ሸንተረር ሸጥ ተራራም አያግደው ፣በጠላት አናት ላይ ሳይታሰብ ደንገት በመድረስ እንደምታት በማስጨነቅ ስነ ልቦናዊ ጫና ይፈጥራል።

አገር ወገን ይኮራበታል፤ ይተማመንበታል ፤በሰራው ታምር ስራ የሶስተኛ ደረጃ የአውደ ውጊያ ሜደይ በመከላከያ ሚኔስቴር ተሸላሚ ሁኗል። የአባቶቹን የጀግንነት ታሪክ በተግባር ድግሟል፤ ሙሉ የሜካናይዝድ አቅሙን በመጠቀም ስምሪት ባደረገባቸው ኦፕሬሽኖች ሁሉ በጠላት ላይ የበላይነትን ማረጋገጥ የቻለ የምዕራቡ ክንድ መቺ ሃይል ነው ።

See also  ጌራሲሞቭ የፑቲን ቀኝ እጅና የጦርነት ዶክትሪን ባለቤት

በስነ ልቦናው እና በስነ አዕምሮው የላቀ ነው ፤ከግዳጅ በተጓዳኝ የጋራ አንድነቱን ና ህብረብሔራዊነቱን የሚያጎለብቱ ውጤታማ የግንባታ ስራዎችን ያከናውናል፤ የአገሩን ሉዓላዊነት እንደብረት በጠነከረ የዓላማ ፅናቱ ይጠብቃል፤ የዜጎችን ሰላምና ልማት በማይሸረሸር ወታደራዊ አቋሙ በዘላቂነት እያረጋገጠ ይገኛል።

ዜጎች በአገራቸው ኮርተው በማንነታቸው ተክብረው በአንድነታቸው ፀንተው በሰላማቸው ተማምነው የሚኖሩባት አገር በማድረግ የምዕራቡ ክንድ ሶሜክ ሀገራዊ ተልዕኮውን አፅንቶ ግዳጁን በጀግንነት እየፈፀመ ይገኛል።

በላይነህ ፈንቴ
ፎቶግራፍ በላይነህ ፈንቴ የኢፌዴሪ መከላከያ

Leave a Reply