ከሳምንት በፊት “ኢትዮጵያ አራተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት በቅርቡ ትጀምራለች፤ አሁንም አቤቱታችሁን ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ልትወስዱት ትችላላችሁ?” የሚል ጥያቄ በጋዜጠኞች የቀረበላቸው የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ የሰጡት ምላሽ የአረብ ሊግ የአቋም መግለጫን ቀድሞ ያመላከተ ነበር፡፡ “ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ” እንደሚባለው ከስብሰባው በፊት የአቋም መግለጫውን የስብሰባው ዘዋሪዎች ለዓለም ሕዝብ ጆሮ አደረሱት፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሚ ሽኩሪ በምላሻቸው “እስከአሁን አቤቱታችንን ከጸጥታው ምክር ቤት እስከ አፍሪካ ኅብረት አቅርበን የተለየ ነገር አልመጣም፡፡ በተደጋጋሚ መንገድ መሄድ ሳይኾን ጉዳዩን አቅጣጫ ቀይሮ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ የግድቡን የውኃ ሙሌት በተመለከተ ግብጽ ጉዳዩን ወደ አረብ ሊግ ትወስደዋለች” ሲሉ ተደመጡ፡፡ እንደ እውነቱ ከኾነ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ የተካሄደው 32ኛው የአረብ ሊግ ስብሰባ ከወትሮው የተለየ እና ትኩረት የሚሹ የመወያያ አንገብጋቢ ነጥቦች ነበሩት፡፡
የአረብ ሊግ እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር መጋቢት 22/1945 ሲመሰረት ከመሥራቾቹ ሰባት ሀገራት መካከል አንዷ የኾነችው የበሽር አላሳዷ ሀገር ሶሪያ ከ12 ዓመታት በኋላ በተመለሰችበት ስብሰባ ከኢትዮጵያ የተሻገረ የአባል ሀገራቱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ነበሩባቸው፡፡ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት እና በጦርነት የተጎዳችውን ሶሪያን ከማቋቋም በላይ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ አቋም መያዝ ከሊጉ ጀርባ የስብሰባው ዘዋሪዎች እነማን እንደነበሩ በግልጽ አመላካች ኾኖ ታይቷል፡፡
ላለፉት ሦስት ዓመታት በሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ዙሪያ ከካይሮ ጋር የወገነችው ካርቱም በሁለቱ ጀኔራሎቿ እልኽ አስጨራሽ ጦርነት ድምጿ ጠፍቷል፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ እንዴት እና ለምን ሱዳን ውስጥ እንደተገኙ እስካሁንም ድረስ ምክንያቱ ግልጽ ያልኾነው የግብጽ ወታደሮች ጉዳይ ለሱዳን ሕዝብ የእግር እሳት በኾነበት በዚህ ወቅት ግብጽ በውኃ ሙሌቱ ዙሪያ ሱዳንም ተመሳሳይ አቤቱታ እንዳላት ሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ተገኝታ ጉዳይ ፈጻሚ መኾኗን አረጋገጠች፡፡ ይህ ሁሉ ተሰባስቦ የዓባይ ጉዳይ ከግብጽ እስከ አረብ ሊግ ውስብስብ እጆች እንዳረፉበት አመላካች ነው ይላሉ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አደም ካሚል፡፡
ግንባር ቀደም ጉዳይ አስፈጻሚዎቹ እና ዋና ጽሕፈት ቤቱ ካይሮ ላይ ከተቀመጠ ሊግ ከዚህ የተለየ አቋም መጠበቅ “በተኩላ ዘመን በግ መኾን” ነው ያሉት ፕሮፌሰር አደም ሳዑዲ አረቢያም የዓባይን ጉዳይ የአረቡ ዓለም ጉዳይ ለማድረግ በቅርቡ የምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የሊጉ አቋም ቅድመ ምልክቶች ነበሩ ይላሉ፡፡ በሳዑዲ አረቢያው የሊጉ ስብሰባ የሕዳሴ ግድቡን በሚመለከት የታየው አቋም ከወትሮው ያልተለየ እና መሻሻል ያልታየበት ነውም ብለዋል፡፡
“የግብጽ የውኃ አቅርቦት ጉዳይ የአረብ ሊግ ሀገራት የፀጥታ ስጋት ጉዳይ ነው” የሚለው የሊጉ ወቅታዊ አቋም የሳዑዲ አረቢያን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ነው የሚሉት ፕሮፌሰር አደም ምክንያቱን ሲያነሱም ሳዑዲ አረቢያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በግብጽ እና ሱዳን ከፍተኛ የእርሻ ኢንቨስትመንት ማስፋፋቷን ተከትሎ የቀረበ ስጋት ነው ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ በየጊዜው “አልቀበለውም” ከሚል ምላሽ ወጥታ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን በጥናት እና በውጤት ተመስርታ መሥራት እንደሚኖርባትም አስገንዝበዋል፡፡ በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጎላ የመጣው የፐብሊክ እና ዲጂታል ዲፕሎማሲ ለግብጽ ሴራ ፍቱን መድኃኒት እንደኾነም አንስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው ባሕር ዳር ፡ (አሚኮ)
- ሸኔ መከፈሉ ተሰማ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቹ እጅ እየሰጡ ነው፤ ተማራኪዎቹ ድርጅቱ መፈረካከሱን አስታወቀ“የህግ የበላይነት ለማስከበር እየተወሰደ ያለዉን እርምጃ መቋቋም የተሳናቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪዉ ሸኔ አባላት ለመንግስት እጅ ሰጡ” ሲል የዘገቡት መገናኛዎች እንዳሉት ድርጅቱ ቁመናው ፈርሷል። በቅርቡ በታንዛንያ ለስምምነት ብዙ ርቀት ከተኬደና ከንግገሩ መልካም ዜና የተጠበቀ ባለበት ወቅት ስምምነት ላይ እንዳልተደረሰ መንግስት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በሰላም ንግግሩ የተኩስ ማቆም ስምምነት ተደርሶ እንደነበር፣ አነጋጋሪ … Read moreContinue Reading
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading