የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በቅርብ ጊዜ የወረራት ፣ የተጣባት ቫይረስ ዘመድኩናዊነት ይባላል። ዘመድኩናዊነት እንደ ቀደመው ዘመን ፈሪሳዊነት 99.9% ጊዜውን የሚያጠፋው የእግዜሩን ቃል በማካፈል ፣ ቀን የጎደለባቸውን ደገፍ ማድረግ ላይ አይደለም። ዘመድኩናዊነት አሳዳጅነት ፣ ስድነት ፣ ተሳዳቢነት ነውርን ክብር አድርጎ አደባባይ የመውጣት ህመም ነው።
ዘመድኩናዊነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ እነ መምህር በጋሻው አጠፉ ለሚባሉት ይቅርታ ጠይቀው ቤተክርስትያኒቱን አማኙን ባገለገሉ ነበር። ዘመድኩናዊነት ባይገን ኑሮ ዛሬ መነኩሴው ፣ ዘማሪው ፣ ሰባኪው ውሎውን ቲክቶክ ፣ ፌስቡክና ዩቱይብ ላይ ባላደረገ ነበር። ዘመድኩናዊነት በጓዳ የሰማኸውን የጓደኛህን ህጸጽ በአደባባይ በሞንታርቦ ለህዝብ የማወጅ ነውረኝነት ነው።
አቡነ ጴጥሮስ ክርስትናን ሊኖሩት የሚሞክሩ ፣ የሚታትሩ ክህን ናቸው ስል አስባለሁ ። አቡነ ጴጥሮስ እና ካህናት ወዳጆቻቸው እነ አቡነ ሳዊሮስን ረግሞና አዋርዶ ከቤተስኪያን ከማራቅ ይልቅ ይቅርታን ፣ ክርስትያናዊ ወንድማማችነትን ለምዕመኑ ያስተማሩ ይመስለኛል። አቡነ ጴጥሮስ በትናንትናው ንግግራቸው የማህበራዊ ሚዲያን አጥፊነትን በገደምዳሜም ጠቆም አድርገዋል ። የዚህ ዘመን ምዕመን መንፈሱ ለዘመድኩናዊነት ቅርብ ነው ፣ ትናንት አባ ያላቸውን ካህናት ዛሬ በመንደር ቃል ለመዘርጠጥ ሰከንዶች አያመነታም። ብዙው አማኝ የእግዜሩን ቃል ከማዳመጥ ፣ በየሰፈሩ ቀን ለጎደለባቸው የሚላስ የሚቀመስ ከማካፈል የቤተስኪያን ጠላቶች የሚላቸውን ቢያሳድድ ለአምላኩ ትልቅ ውለታ የሚውል የሚመስለው ነው።
ክርስትና ሌሎችን መውደድ ፣ ደከም ያሉትን ( በመንፈስም በስጋም ) ማገዝ ነው። ክርስትና ውስጡ የአሳዳጅነትና ከሳሽነት መንፈስ ፍጹም የለበትም። አቡነ ጴጥሮስ ውስጥ ፍቅርና ትህትና የሞላበት ክርስትናን አያለሁ ።
መምሬ Samson Michailovich እንደጻፉት !
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው። በተጀመረው የአብይ ጾም ማቅ ለብሰውና አመድ ነስንሰው ችግራቸውን ሊፈቱ እንደሚገባ ምክር እየተሰጠ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories ኢትዮጵያዊው ድሮን ሰርቶ የተሳካ ሙከራ አደረገFebruary 18, 2022 ትንሽ ብቻ ጠብቅ‼February 20, 2022 “ህወሃት በሚያኮርፍባቸው… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም ሲቲ” (Neom City) በሳውዲው ልዑል መሀመድ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the Horn of Africa and resulted in a similar deal struck between Somalia and… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ህገመንግስቱ በሚያዘው መሰረት በህዝበ ውሳኔ እንዲቋጭ በይፋ ስምምነት ላይ መደረሱ ተረጋገጠ።… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ