ኔይማር ወደ ቼልሲ? ዩናይትድ ወይስ ኒውካስትል?

ያሆን ስፖርት ኔይማርና ማንችስተር ዩናይትድ ቀለበት ለማሰር ርቀው መጓዛቸውን እትቷል። ከፈርንሳይ የሚወጡ መረጃዎችን ዋቤ ያደረገው ያሆን ኔይማ በ2017 በዓለማችን ውድ ዋጋ ወደ ማሪስ ሴንትዠርመን መግባቱ አስታውሷል። ላለፉት ስድስት ዓመታት የሻምፒዮንስ ሊግ ውጤት አልባ መሆን ያማረራቸው መቶ የሚዘልቁ ደጋፊዎች ቤት ድረስ ሄደው “Neymar, get out” ወይም በአገራችን አባባል ” ሂድ ጥፋልን” ብለውታል።

በዘገባው የአገሩ ልጆች እንደሚወሰውሱት የተመለከተ ሲሆን ማንችስተር ሁለት ቀሪ ጨዋታዎቹን በማሸነፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ማረጋገጥ እንዳለበትና ይህም የኔይማር ቅድመ ሁኔታ እንሆነ ተመልክቷል።

ኳስን ጠንቅቆ የሚያውቃት ኔይማር በጎልበት ቀዶ ጥገና ከፊብሩዋሪ ጀምሮ ከሜዳ የራቀው ኔይማር ቼልሲን እንደሚቀላቀል እየተወራ ነው። ኒውካስትልም ከኔይማር ጋር ስሙ ተነስቷል። ሁሉም የዝውውር ዜናዎች ከጀርባቸው የሚያነሱት ግን ኔይማር ከጉልበት ቀዶ ጥገናው በሁዋላ ውድ ገንዘብ የሚፈስበት ተጫዋች የመሆኑ ጉዳይ ነው።

ማንችስተር ዩናይትድ አሳቡን ይቀይር አይቀይር በውል ባይገልጽም ከኔይማር ፈላጊዎች መካከል አንዱ እንደሆነ እንደሚሳካለት ቢገለጽም ንግግሩ ከፍ ባለ ደረጃ ማደጉን እንጂ በውል ስለተደረሰ ስምምነት የተባለ ነገር የለም። ከሁሉም ወገን የሚወጡ መረጃዎች እርግጠኛ የሆኑት ሴንት ዠርመን ኔይማርን ሊለቀው ፈቃደኛ የመሆኑ ጉዳይ ብቻ ነው።

ኔይማር ሜሲ በሌለበት ቡድን ውስጥ ኮከብ የመሆን ህልም ቢኖረምው፣ ይህን ህልሙን ማሳካት ይቻለው ዘንድ እንግሊዝ መምጣቱ ይበጃል ወይም አይበጅም በሚለው ጉዳይ ሰፊ ዝገባ ባይወጣም፣ ከጉዳት አገግሞ አቅሙና ወቅታዊ ሁኔታው ሳይታወቅ ማን በሚሊዮን ደፍሮ ያፈሳል? የሚለውን ስጋት ግን የሚያነሱ ብዙ ናቸው።

የዓለም ምርጡ ተጨዋች መሆኑን ዳታ ጠቅሰው የምመሰክሩ ደግሞ በጭብጥ መረጃዎች መመዘኛ ቼልሲ ኔይማርን ቢያገኘው እንደሚያተርፍ ይገልጻሉ።

“አርቲስት” በሚል ስም የሚወደሰው ኔይማር ቼልሲ ቢገባ ውበት፣ መነቃቃትና የተበተነውን የቼልሲን ምርጭ ስኳድ አንድ ላይ የማሰባሰብ አቅም እንደሚፈጥር አግንነው ያሳዩ እንደሚሉት ቼልሲ ኔይማርን ጨክኖ እጁ ካስገባ ይነዳል።

በአመቱ 35 ጎል ብቻ ያገባው የቼልሲ የፊት መስመር፣ ኔይማርን ቢያገኝ የጎሉን በር የመመልከቻ አጋጣሚዎችን እንደሚፈጥር በርግጠኛነት የሚናገሩ ጸሃፊዎች አሁንም ቼልሲ ተጣቃሚ እንደሚሆን ያብራራሉ። ማስረጃም ያቀርባሉ።

See also  ሴት አትሌቶች በሞሮኮ በተደረገ የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል

Leave a Reply