የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ ሊሰጥ ነው

በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ – አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።

በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።

ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።

ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡

ሩሲያ የአፍሪካ ልሂቃን ዲግሪ ለማግኘት ከሚሄዱባቸው አገሮች አንዷ እንደነበረች ያነሱት በውይይቱ የተሳተፉት ምሁር ቱንዴ አጂሌዬ÷አሁን ላይ ሩሲያ እና አፍሪካ የትምህርት ልውውጡን መቀጠል አለባቸው ሲሉ አክለዋል።

እንደ ምሁሩ ገለጻ በግብርና፣ በኃይል እና ኢንቨስትመንት ላይ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

 • “ደብረ ኤሊያስ ገዳም የደረሰበት ጉዳት የለም” ወረዳው፤ መከላከያ ስራውን መጨረሱ ተሰማ
  አካባባዊ በተለይም ገዳሙ ወታደራዊ ማስለጠኛ፣ የሚፈለጉ ሰዎች መመሸጊያ፣ ሃይማኖታዊ ዓላማውን የሳተ በመሆኑ በአባቶች፣ በሃይማኖት መሪዎች፣ በመንግስት ሃላፊዎችና ታውቃ ሰዎች ቢለመኑም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ፣ በስተመጨረሻም ደብሩም ሆነ መኖኮሳቶች ምንም ሳይሆኑ መከላከያ ገብቶ ስራውን አከናውኖ መጨረሱ ተሰማ። በርካታ ታጣቂዎች ለመከላከያ እጃቸውን መስጠታቸውም ተገልጿል። ወረዳው መከላከያ ስራውን ጉዳት ሳያደርስ ማከናወኑን ይፋ ሲያደርግ እጅቻውን ስለሰጡናContinue Reading
 • አሮጌውን ወይን በአዲስ አቁማዳ ! የኖርንበት ፣ የቸከ የሰለቸ የፖለቲካ …
  የኢትዮጵያ ታሪክ የእርስ በእርስ ጦርነት civil war & strife ነው። ይሄንን ያደፈ ጉድለታችንን ማስተካከል የምንችለው መሀከለኛውን መንገድ የያዙ ስብስቦችን በማብዛት ነው። ችግሩ በእኛ ሀገር ፖለቲካ መሀከሉን መንገድ ልትይዝ ስትሞክር የሚወረወርብህ ፍላጻ መብዛቱ ነው። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ኢዜማ ነው። ህወሃትም ፣ የኦሮሞ ብሄረተኜችም ፣ በቅርብ የተፈለፈሉት የአማራ ብሄረተኞችም ለፓርቲው ያላቸውን ጥላቻContinue Reading
 • US Special Envoy for HoA Amb Mike Hammer to Visit Ethiopia
   US Special Envoy for the Horn of Africa Ambassador Mike Hammer will visit Ethiopia on May 31 – June 6. In Ethiopia, Ambassador Hammer will meet African Union officials on implementation of the November 2, 2022 Cessation of Hostilities Agreement (COHA). He will discuss progress and priorities including transitional justiceContinue Reading
 • በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ በ38 ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ተፈቀደ
  የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በ3 መዝገብ የቀረቡ የ38 ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ተመልክቷል። ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ያቀረበው የፌደራል ፖሊስ መርማሪ በቀዳሚነት በነመላክ ምሳሌ መንግስቱ መዝገብ የተካተቱ 16 ግለሰቦችን እና በነደበበ በሻህ ውረድ መዝገብ የተካተቱ በ12 ተጠርጣሪዎች አጠቃላይ 26 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል የጥርጣሬ መነሻውን በፅሁፍም በቃልምContinue Reading
 • ሟችን በጭፈራ የሚሸኘው ማህበረሰን
  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን ውስጥ ተወልደው ያደጉት ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳታ በቅርቡ ነው አያታቸውን በሞት ያጡት። የሚወዷቸው አያታቸው ቀብር የተፈፀመው ግን ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ ዘፍኖ እና ጨፍሮ በተከናወነ ሥነ ሥርዓነት መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። ሞት በሁሉም ዘንድ ሁሌም አዲስ ነው። በመጣ ቁጥር የሚያስደነግጥ በብዙ ማኅበረሰቦች ዘንድም ማቅ የሚያስለብስContinue Reading
See also  ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር አባይ እና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ማረሚያቤት እንዲወርዱ ታዘዘ

Leave a Reply