በሩዋንዳ ንጹሃን ጭፍጨፋ የሚፈለገው ወንጀለኛ ተያዘ

በሩዋንዳው የዘር ግጭት ከ2 ሺህ በላይ ግጭቱ ሸሽተው በቤተክርስቲያን የተጠለሉ ሰዎችን ቤተክርስቲያኑ ውስጥ በገፍ አቃጥሎ ሲያበቃ በኋላ በዶዘር ቆፍሮ የቀበራቸው ወንጀለኛ Fulgence Kayishema ከዓመታት ክትትል በኋላ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ስር ውሎ ተይዞ ፍርድቤት ቀርቧል።

ይህ ነብሰ ገዳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስደተኛ ሆኖ ስሙ ቀይሮ ነበር የገባው። የአንድ እርሻ ዘበኛ ሆኖ ነበር ሲሰራ የነበረው። የሩዋንዳና የደቡብ አፍሪካ የጽታና ድህንነት ሰራተኞች ባደረጉት ክትትል በ2018 እሱ መሆኑ ካወቁ በኋላ ለተባበሩት መንግሥታት በማሳወቅ የስደተኝነት ማንነቱ ተፍቆ ዛሬ ፍርድቤት ቀርቧል።

PS: ትላንት በአማራ ህዝብ ላይ በኦሮሞ ክልል በተለይ ወለጋ ውስጥ የተፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ገና አፉ እንደከፈተ ወንጀሎች ሳይቀጡ ከሞት የተረፈው ህዝባችን አሁንም ሜዳ ላይ ተበትኖ ይገኛል። ይህን የመሰለ የዘር ማጥፋት ጭካኔ የፈጸሙ ሰዎች ግን ዛሬ ባለ ጊዜ ሆነው ማለፍ ቢችሉም የነገ ዕጣ ፈንታቸው እንደዚህ ሰውዬ ከመሆን እንደማያልፍ ሊያውቁ ይገባል።

ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ዓለም ነገ የማን ጓደኛ እንደሚሆን አይታወቅምና ወንጀለኞች አንድ በአንድ መዝግበን እንያዝ።

Gran Chico

See also  ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ሰርቀዋል የተባሉ ሃላፊዎች ላይ ፍርድ ተሰጠ

Leave a Reply