ሴት አትሌቶች በሞሮኮ በተደረገ የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል

በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን ከ1 እስከ 4 ደረጃዎችን በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል። ውድድሩን አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 3 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ ከ3 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆናለች።

አትሌት ፍረወይኒ ሃይሉ ደግሞ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ65 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ስትወጣ፥ አትሌት ብርቄ ሓየሎም 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ66 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ደግሞ ውድድሩን 4 ደቂቃ ከ1 ሰከንድ ከ81 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አራተኛ ደረጃን አግኝታለች።

በሌላ ውድድር በወንዶች 3 ሺህ መሰናክል የተሳተፈው አትሌት ጌትነት ዋለ ውድድሩን 8 ደቂቃ ከ5 ሰከንድ ከ15 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

See also  የኪሎገር የሳይበር ጥቃት ምንድነው ? እንዴትስ ይፈጸማል?

Leave a Reply