Site icon ETHIOREVIEW

በአክሲዮን ሸያጭ ላይ የነበረው “ሰላም ባንክ” በይፋ ተበተነ

አክሲዮን ሲሸጥ የነበረው ሰላም ባንክ አክሲዮን መሸጥ አቁሞ መበተኑን የባንኩ መስራች መካከል አንዷ የሆነችው ወ/ሮ ቤተልሄም ጥላሁን ለሸገር ሬዲዮ መናገሯን ፋስት መረጃ ሰምቷል።

ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ አክሲዮን መሸጥ የጀመረው ባንኩ ለመዘጋቱ ምክንያት የተባሉት የዓለም እና የሀገራችን ሁኔታ አንዳንድ ነገሮች እንዲዘገዩብን ሆኗል የሚሸጠው የሼር ብዛት እና የጊዜው ሁኔታ እየተመጣጠነ ስላልሆነ ለሰላም ባንክ መዘጋት ምክንያት ነው ሲሉ ወ/ሮ ቤተልሄም ገልፇል።

ሼር የገዙ ባለአክሲዮኖች ገንዘብ የሚፈልጉ ገንዘቡ ተመላሽ ይሆናል፣ ሌላኛው አማራጭ ከሌላ ባንክ አክሲዮን መግዛት የሚፈልጉ ወደ ጎህ ቤቶች ባንክ እናስተላልፋን ተብሏል።

Refund የሚሆነው ገንዘብ በወቅቱ የነበረው የብሩ ዋጋ እና አሁን ያለው አይገናኝም ይህ እንዴት ታይቷል ሲል ጋዜጠኛው ላቀረበው ጥያቄ ወ/ሮ ቤተልሄም ሲመልሱ “ባንኩ ስራ የጀመረ ባንክ አይደለም ከየትም አምጥቶ ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ ሊሰጥ አይችልም” ብለዋል።

ባንኩ በ2 አመታት 5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ለማድረስ አስቦ ነበር።

Exit mobile version