የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሕመም ነው።
እንደ ሌሎች የካንሰር ሕዋሳት ሁሉ የጡት ካንሰርም በጡት ዙሪያ ወደሚገኙ ሕዋሳት ውስጥ ገብቶ ሊያድግ እና ሊሰራጭ ይችላል፡፡
ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም በመጓዝ አዳዲስ ዕጢዎችን ሊፈጥር ይችላል።
የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ነው።
የጡት ካንሰር ከቆዳ ካንሰር ቀጥሎ በብዛት ከሚከሰቱ ካንሰሮች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው።
የጡት ካንሰር ብዙውን ጊዜ ከ 50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
ሲጋራ እና አልኮል መጠቀም ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት ፣ የሆርሞን ወሊድ መከላከያ ወይም ሌላ የሆርሞን መድሃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም እና የጨረር ሕክምና ለጡት ካንሰር መከሰት ምክንያቶች ናቸው::
በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር መኖር፣ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጅን ከ30 ዓመት በኋላ መውለድ፣ ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት ፣ ከ12 ዓመት ዕድሜ በፊት የወር አበባ መምጣት እና ከ 55 ዓመት ዕድሜ በኋላ የወር አበባ ዘግይቶ መቆም እንደ መንስዔ ሊወሰዱ ይችላሉ::
የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
በብዛት የሚስተዋሉ የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት መጠን ወይም ቅርጽ ላይ ለውጥ ማየት ፣ የአተር መጠን ያለው እብጠት፣ በጡት ወይም በጡት ጫፍ ላይ የመልክ ወይም የቆዳ ለውጥ፣ ከቆዳው በታች እብነ በረድ የመሰለ ጠንካራ ቦታ መኖር ናቸው፡፡
በተጨማሪም ከጡት ጫፍ ውስጥ በደም የተበከለ ወይም ንጹህ ፈሳሽ መኖር ፣የተሰራጨ ዕጢ ከሆነ ደግሞ የደረት ሕመም፣ የአጥንት ሕመም እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
ሕክምናውን በተመለከተ
የጡት ካንሰር ምርመራ ለማድረግ በዋነኛነት ማሞግራፊ ፣ አልትራሳውንድ ፣ እና ፒኢቲ(PET) የተሰኙት ምርመራዎች የሚታዘዙ ሲሆን አጠራጣሪ ውጤቶች ሲገኙ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረግበታል ::
ሕክምናን በተመለከተም ቀዶ ጥገና ፣ ኪሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ቴራፒን ጨምሮ በርካታ የጡት ካንሰር ሕክምና አማራጮች አሉት።
ሕክምናው የሚወሰነው ዕጢው ያለበት ቦታ እና መጠን፣ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶች እና ካንሰሩ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች መስፋፋቱን ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ይደረጋል።
ሕክምናው ቀደም ብሎ ከተሰጠ የመዳን ዕድሉ ከፍ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ያለበት ሰው በተቻለ ፍጥነት የሕክምና ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ዶክተሮች ይመክራሉ፡፡
ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ + fana
- በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋልበሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል። የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አሕመድ በጎርፉ የተጎዱት ከ600,000 በላይ ሰዎች እንደሚሆኑና ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል። ” ምግብም፣ … Read moreContinue Reading
- የፕሮስቴት እጢ ምልክቶችና ህክምናውፕሮስቴት እጢ በወንዶች ፊኛ በታች የሚገኝ ተፈጥሯዊ የሰውነት አካል ነው ፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ዩሮሎጂ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሀመድ አብዱልሀዚዝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷የፕሮስቴት እጢ ዋነኛ ተግባር የዘር ፈሳሽ በማመንጨት ወደ ፊት ለፊት እንዲወጣ በማገዝ ለመራቢያነት ማገልገል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የበሽታው መንስኤ ብለን የምንጠራቸው ምክንያቶች … Read moreContinue Reading
- ለተማሪዎች መውደቅ ማነው ተጠያቂው ?በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦ ” … ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል Shock … Read moreContinue Reading
- የአጥንት መሳሳት ምንድነው?ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይኖረው ወይንም ምልክቶችን ሳያሳይ ለከፍተኛ የጤና ችግር ብሎም ለሞት ሊዳርገን የሚችለውን የአጥንት መሳሳት ችግር ምንድን ነው? ከሰውነት ክፍሎቻችን አጥንት ጠንካራው እና በቀላሉ የማይጎዳ ነው፤ ነገር ግን አጥንት በመሳሳት ምክንያት ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። አጥንትን ደካማ እና በቀላሉ ተሰባሪ የሚያደርገው የአጥንት መሳሳት ሕመም ነው። ለመሆኑ የአጥንት መሳሳት ምንድነው? አጥንት ሁልጊዜ በለውጥ … Read moreContinue Reading
- የደም ግፊት – ድምጽ አልባው ነብሰ ገዳይስለ ደም ግፊት የሚወጡ መረጃዎች አስደንጋጭ እየሆኑ ነው። ደም ግፊት እጅግ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እየጨረሰ ነው። ደም ግፊት “ድምጽ አልባው ገዳይ” የተባለውም ለዚህ ነው። አሁን አለሁ ሲሉ ድንገት ጭጭ የሚያደርግ የዘመናችን መርዝ ነው። በመላው ዓለም 1,28 ቢሊየን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 79 ዓመት የሆነ ሰዎች ለከፍተኛ የደም ግፊት የጤና ችግር … Read moreContinue Reading