ETHIOREVIEW

ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው፤ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የኮንትሮባንድ ጉዳይ መላ እንዲበጅለት ዜጎች እየጠየቁ ነው

ዛላንበሳ የኤርትራና ኤትዮጵያ ድንበር መዳረሻ

ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንዳን በመላላክ ወደ ኤርትራ የሚሸጋገሩ ቁሳቁሶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እየጎዳ መሆኑ፣ በሕዝብ የእለት ተእለት ፍጆታ ላይም ተጸዕኖ እያሳደረ መሆኑን የሚያውቁ መንግስት መላ ሊፈልግ እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው። በትግራይ ክልል በህዝብ ቁጥጥር በአንድ አቅጣጫ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ ተገልጿል።

በውጭ ገንዘብ ምንዛሬ፣ በግንባታና በእለታዊ ፍጆታ እቃዎች ላይ በስፋት ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩና የኤርትራ መንግስት ድጋፍ የሚያደርግላቸው ክፍሎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየተፈታተኑት እንደሆነ የሚገልጹ ወገኖች ” ወዳጅነትና የኮንትሮባንድ ዝርፊያ ለየቅል ናቸው” ሲሉ መንግስት መስመር ሊያሲዘው እንደሚገባ አመልክተዋል።

ቀደም ባሉት ወራት በድንገት በተደረገ አሰሳና በክትትል በተሰራ ስራ በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ መያዙን ያስታወሱ፣ ከነማን ላይ እንደተያዘ በስም መጥቀስ ባይፈልጉም ውንብድናው በወዳጅነት ስም ሽፋን የተሰጠውና በኤርትራ መንግስት ደረጃ የሚታወቅ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ሻዕቢያ ጫካ እያለ አዲስ አበባና የተላያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያስነግድ እንደነበር በማስታወስ የአሁኑ መጠኑና ዓይነቱ ከመጨመሩ ውጭ ተመሳሳይ እንደሆነ ያመለክታሉ። መንግስት ይፋ ባይናገርም ጥብቅ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሚያውቁ ” ቡና እየዘረፈ ከአፍሪካ አንደኛ ቡና ላኪ ሆኖ የነበረው የሻእቢያ መንግስት እንዳሻኝ ካልዘረፍኩ በሚል ማኩረፉን እናውቃለን። ምን አልባትም በአማራ ክልል በድንገት የነደደው ጦርነት የዚህ ኩርፊያ ውጤትም ጭምር ሊሆን ይችላል”ብለዋል።

በሰሜን ኦምሃጀር በኩል የቅባት ዕህል፣ የምግብ መርቶች ጤፍን ጨምሮ ወደ ኤርትራ እንደሚጋዝ፣ የጎጃም አካባቢ ነጋዴዎች ምርታቸውን ወደ መሃል አገር ከሚልኩ ወደ ኤርትራ ለሚያጉዝጉዙ እንዲሸጡ ይደረግ እንደነበርና አሁን ላይ ቢቀንስም እንዳልቆመ የሚጠቁሙ ወገኖች በጦርነቱ አማካይነት የፈረሱና የተዘጉ ኬላዎች ዳግም መቋቋም ኮንትሮባንዱን በትሥር ለሚቀበሉት ክፍሎች ደስታን አልፈጠረም።

ቲክቫህ ትግራይ በመሄድ በዛላንበሳ በኩል ብቻ ህዝብ ተባብሮ ቁጥጥር በማድረግ የያዛቸው ወደ ኤርትራ ሊጓጓዙ የነበሩ የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች፣ ከተያዘው በላይ ያልተያዘውን በማስላት ኢትዮጵያ እንዴት እየታለበች መሆኑንን የሚያሳይ ሆኖ ተወስዷል።

በኢትዮጵያ የቀለብ ዕህልና ቁሳቁሶች፣ የግንባታ ግብአትን ጨምሮ በዋጋ መናር ህዝቡን እያሰቃየ ባለበት በአሁኑ ሰዓት፣ ኢትዮጵያ ዶላር የምታፈስበት ነዳጅ፣ ዘይትና የግንባታ ብረትን ጨምሮ ቡናና የምግብ ምርቶች ወደ ጎረቤት አገር በኮንትሮባንድ እንደሚጋዝ መንግስት ማስታወቁ አይዘነጋም። የቲክቫህን የትግራይ ሪፖረት ይከታተሉ።

ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ ” ጉሎመኻዳ ወረዳ ” አቅንቶ ነበር። የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፤ ” የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ሊያዙ የተቻሉት በህዝብ የነቃ ተሳትፎ በመታገዝ ነው ” ብለዋል።

አቶ ሃፍቶም ፤ የትግራይ ኢትዮጵያዋ የጉሎመኻዳ ወረዳ ሰፊ አከባቢ ከሃገረ ኤርትራ የሚዋሰን በመሆኑና በጦርነቱ ምክንያት በዛላኣንበሳ ከተማ የነበረው የቁጥጥር ኬላ በመፍረሱ የተለያዩ እቃዎች በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ኤርትራ ይተላለፋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

” ዛላኣምበሳ ጨምሮ የወረዳው ስድስት ቀበሌዎች በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ” ያሉት አቶ ሃፍቶም ፤ በዚሁ በኩል ወደ ኤርትራ ለማሸጋገር የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመግታት እንዲቻል ህዝቡ ባለቤት በመደረጉ ምክንያት አመርቂ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የዞኑ የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኪዱ ገ/ፃድቃን እንዳሉት ፤ ከግንቦት እስከ ሃምሌ 2015 ዓ.ም  የ4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ መሳሪዎች በህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።

የተያዙት ፦

ጉሎመኸዳና ኢሮብ ከኤርትራ የሚዋሰኑ የምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች መሆናቸው የጠቀሱት አቶ ኪዱ ፤ ብዘት ዳሞ ፣ ፋፂ ዛላኣምበሳ ፣ ሰበያ፣ ደውሃን ዓይጋ የሚባሉት ቦታዎች ዋና የህገወጥ ኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች መሆናቸው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊው ፤ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ንብረቶች በመቆጣጠር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስፍራው ድረስ በመሄድ የአካባቢው ኃላፊዎች ፦
–  የኮንትሮባንድ ዝውውር እንዴት እየተፈፀመ እንዳለ

ityoPya

tikvahethiopia


Exit mobile version